Get Mystery Box with random crypto!

አንድ ቀን አንድ ሰውዬ ባርያውን ወደ ገበያ ይልከዋል ባርያውም በጣም ከቆየ ቡሀላ እንዲገዛ ከተላከ | 1 ነት ጀምአ

አንድ ቀን አንድ ሰውዬ ባርያውን ወደ ገበያ ይልከዋል ባርያውም በጣም ከቆየ ቡሀላ እንዲገዛ ከተላከው ሁለት ነገር አንዱን ብቻ ገዝቶ ይመጣል አለቃውም በጣም ከገረፈው ቡሀላ እንዲህ የሚል መመሪያ ሰጠው ከዚህ ቡሀላ አንድ ነገር ስልክህ ለሌላም ነገር እንደሚያስፈልግ አውቀህ ገዝተህ ና ለምሳሌ ደብተር ብልክህ እስክሪብቶ እንደሚያሳፈልግ አውቀህ ገዝተህ ና አለው።ባርያውም የአለቃውን ትእዛዝ ከተቀበለ ቡሀላ ወደስራው ተመለሰ።ከብዙ ጊዜ ቡሀላ አለቃው ይታመምና እኔ ሀኪም ቤት መሄድ ስለማልችል ሀኪም ይዘህ ና ብሎ ላከው።አገልጋዩም እንደለመደው በጣም ከቆየ ቡሀላ ሀኪሙንና ሌላ ተጨማሪ አንድሰው ይዞ መጣ።አለቃው ሀኪሙን ካየው ቡሀላ ሌላ ሰው ለምን አመጣህ ብሎ ጠየቀው አገልጋዩም ባለፍው ጊዜ ስትልከኝ አንድ ነገር ስልክህ ሁለተኛውም እንደሚያስፈልግ አውቀህ ገዝተህ ና ብለሀኝ ነበር እኔም ሀኪሙ አክሞህ ከዳንክ ማሻ አሏህ ደስ ይላል ምናልባት ግን ህመምህ ጠንቶብህ ከሞትክ ይሄ ሰውዬ መቃብርህ ይቆፍራል አለው ይባላል።ፈገግታ ሱና ነው