Get Mystery Box with random crypto!

Mezmur Legeta Lyrics

የቴሌግራም ቻናል አርማ songlegetalyrics — Mezmur Legeta Lyrics M
የቴሌግራም ቻናል አርማ songlegetalyrics — Mezmur Legeta Lyrics
የሰርጥ አድራሻ: @songlegetalyrics
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 907
የሰርጥ መግለጫ

This is the only full album amharic gospel songs lyrics channel.

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-06 22:29:00 Gospel Singers : Kenesssa and Solomon Bula



ርስታችን

1. የወደድካቸውን ሁሌም ትወዳለህ
ወረት አያዉቅህም አንተ ሰው አይደለህ
ሁሉም ቢለዋወጥ አንተ ያዉ አንተ ነህ
አመታትህ አያልቁም አያረጅም ፍቅርህ | 4×|

ርስታችን እድል ፈንታችን
ሁሉም ቢቀር ከቶ ምን አጣን
አንተ አለኸን ከበቂም በላይ
ክበርልን በምድር በሰማይ

2. ግራ ቀኙን አየን ሁሉን ተመለከትን
የኛ የመሰለን እንዳልሆነ አወቅን
ከአመጣጡ ይልቅ አካሄዱ ፈጥኗል
ሁሉም ግን ቢከዳን ፍቅርህ ቀርቶልናል |4×|

ርስታችን መኖርያችን የዘላለም አምላክ እግዚአብሄር ነው | 2× |
ምርኩዛችን መመኪያችን የዘላለም አምላክ እግዚአብሔር ነው| 2×|

YouTube Video under comments
70 viewsedited  19:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 09:52:32
Gospel singer : Azeb Hailu Full album lyrics
181 views06:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 14:31:46 Live stream started
11:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-15 11:07:47 Gospel singer : በረከት ተስፋዬ



በዓለም ፍቅር እንዳልነደፍ
ከሚጠፉት ጋር እንዳልሰለፍ
አረማመዴን አቅናውና
የራስህ አድርገኝ ቀይረኝና

አዝ:- ከሚጠፉት እንዳልሆን ጠብቀኝ
ጌታ ሆይ ምህረትህን አብዛልኝ (፪x)

አንተ የሌለህበት
የዓለም ዝና የዓለም ዕውቀት
ኢሄ ሁሉ ከንቱ ነዉ
ንፋስን እንደመከተል ነው

አዝ:- ከሚጠፉት እንዳልሆን ጠብቀኝ
ጌታ ሆይ ምህረትህን አብዛልኝ (፪x)

በአንደበቴ እንዳልረክስ
ወንድሜንም እንዳልተነኩስ
አቤቱ ማስተዋልን ስጠኝ
መንፈስ ቅዱስ ና አስተምረኝ

አዝ:- ከሚጠፉት እንዳልሆን ጠብቀኝ
ጌታ ሆይ ምህረትህን አብዛልኝ (፪x)

ዓይኔን ወደ አንተ እንዳቀና
መንፈስ ቅዱስ ናልኝና
ፈውሰኝ ቀድሰኝ
መጠቀሚያ ገንዘብህ አድርገኝ

አዝ:- ከሚጠፉት እንዳልሆን ጠብቀኝ
ጌታ ሆይ ምህረትህን አብዛልኝ (፪x)
291 views08:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-15 11:05:27 ፓስተር ታምራት ፡ ሃይሌ
#ታሪኬ_የጀመረው

ታሪኬ የጀመረው በቀራኒዮ ነው
በመስቀሉ ግርጌ በአጋጣሚ አይደለም መወለድ ማደጌ
ሠይጣን ሲቀጠቀጥ እራሱን ሲመታ
ባርነቴ ሲሻር ሰንሰለት ሲፈታ
ጠላት ሲመሽበት ለእኔ ግን ሲነጋ
ኢኸው በታሪኬ ተጀመረ እዚያጋ
ምሥጋናዬ ምሥጋናዬ ይኼው ለጌታዬ
ምሥጋናዬ ምሥጋናዬ ይኼው በዜማዬ (፪x)


ከወህኒ ከፍርድ እኔኑ ሊያወጣ
ከድንግል ማርያም ሥጋ ለብሶ መጣ
መልክ ውበቱን ተወ የባርያን መልክ ያዘ
እስከ መስቀል ሞት በፍቅር ታዘዘ
ከአደረገው በቀር ኢየሱሴ ምንም ታሪክ የለኝ የእራሴ

ታሪኬ የጀመረው በቀራኒዮ ነው
በመስቀሉ ግርጌ በአጋጣሚ አይደለም መወለድ ማደጌ
ሠይጣን ሲቀጠቀጥ እራሱን ሲመታ
ባርነቴ ሲሻር ሰንሰለት ሲፈታ
ጠላት ሲመሽበት ለእኔ ግን ሲነጋ
ኢኸው በታሪኬ ተጀመረ እዚያጋ
ምሥጋናዬ ምሥጋናዬ ይኼው ለጌታዬ
ምሥጋናዬ ምሥጋናዬ ይኼው በዜማዬ (፪x)


በቃሉ እውነተኛ በተግባሩም ደግ
ከፋት የሌለበት የእግዚአብሔር በግ
እኔን ሊያዘምረኝ እርሱ አለቀሰ
እኔን ሊያከብረኝ ወረትን ለበሰ
ከሥም ሁሉ በላይ ሥም አለው
ዛሬም ምሥጋናዬ ለእርሱ ነው

ታሪኬ የጀመረው በቀራኒዮ ነው
በመስቀሉ ግርጌ በአጋጣሚ አይደለም መወለድ ማደጌ
ሠይጣን ሲቀጠቀጥ እራሱን ሲመታ
ባርነቴ ሲሻር ሰንሰለት ሲፈታ
ጠላት ሲመሽበት ለእኔ ግን ሲነጋ
ኢኸው በታሪኬ ተጀመረ እዚያጋ
ምሥጋናዬ ምሥጋናዬ ይኼው ለጌታዬ
ምሥጋናዬ ምሥጋናዬ ይኼው በዜማዬ (፪x)


ብዙ የነበረውን እዳዬን ሻረልኝ
ኃጢአቴን ሁሉ ከኋላው ጣለልኝ
በመስቀል ጠርጐ ከእኔ አስወግዶ
ጨካኙን ከሳሼን ባዶ እጁን ሰደደው
እዛጋ ጀመረ ታሪኬ ምሥጋና ይብሳለት አምላኬ

ታሪኬ የጀመረው በቀራኒዮ ነው
በመስቀሉ ግርጌ በአጋጣሚ አይደለም መወለድ ማደጌ
ሠይጣን ሲቀጠቀጥ እራሱን ሲመታ
ባርነቴ ሲሻር ሰንሰለት ሲፈታ
ጠላት ሲመሽበት ለእኔ ግን ሲነጋ
ኢኸው በታሪኬ ተጀመረ እዚያጋ
ምሥጋናዬ ምሥጋናዬ ይኼው ለጌታዬ
ምሥጋናዬ ምሥጋናዬ ይኼው በዜማዬ (፪x)
229 views08:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-24 08:51:33
461 views05:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 11:01:39 Gospel singer : Meskerem Getu ( NEW )

ከሰማይ ሰማያት ከዙፋኑ ወርዶ
ከድንግል ማርያም በበረት ተወልዶ
እንደ ፋሲካ በግ ስለ'ኛ ታረደ
ሞታችንን ሞተ ፍዳችንም ሄደ
ፍርድ ተወገደ!
አዎ ይወደናል! አዎን ያፈቅረናል
ነፍስን እስከ መስጠት
ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር የታል?
ኢየሱስ ያድናል! አዎን አድኖናል!
ከፊት እየመራ ወደ ጽዮን ያደርሰናል!
መልካም እረኛ ነው እጅግ የሚራራ
በለመለመ መስክ ህዝቡን የሚመራ
ከአብ ጋር ያስታረቀን ያደረገን ዘመድ
የህይወት በር ነው እውነት ነው መንገድ
አቤቱ ፍቅሩ ነው ብርቱ
አቤቱ አቤቱ ብዙ ቸርነቱ
አቤቱ አቤቱ ምህረቱ
አቤቱ አቤቱ እልፍ ቸርነቱ አቤቱ!
የተጠላነውን እንዲሁ ወደደን
ሰው ሆኖ የዓለምን ኃጢአት አስወገደ
ፍቅሩ ውቅያኖስ ነው በዘመናት ሁሉ
የወንጌል ማህበራት ለእርሱ እልል በሉ
ለጌታ ዘምሩ!
አዎ ቤዛችን ነው አዎ ተቤዥቶናል
ከኃጢአት ባርነት ነፃ አውጥቶ
የራሱ አድርጎናል
ኢየሱስ ያድናል! አዎን አድኖናል!
ከፊት እየመራ ወደ ጽዮን ያደርሰናል
አዎ ብርሃናችን ነው አዎ በርልቶልናል
ከአስፈሪው ጨለማ ከድቅድቁ ታድጎናል
ኢየሱስ ያድናል! አዎን አድኖናል!
ከፊት እየመራ ወደ ጽዮን ያደርሰናል!

YouTube Link and audio under comments
536 viewsedited  08:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-11 20:50:44
Gospel singer : Addisu Worku
Full album Vol. 2
436 views17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ