Get Mystery Box with random crypto!

Gospel singer : በረከት ተስፋዬ በዓለም ፍቅር እንዳልነደፍ ከሚ | Mezmur Legeta Lyrics

Gospel singer : በረከት ተስፋዬ



በዓለም ፍቅር እንዳልነደፍ
ከሚጠፉት ጋር እንዳልሰለፍ
አረማመዴን አቅናውና
የራስህ አድርገኝ ቀይረኝና

አዝ:- ከሚጠፉት እንዳልሆን ጠብቀኝ
ጌታ ሆይ ምህረትህን አብዛልኝ (፪x)

አንተ የሌለህበት
የዓለም ዝና የዓለም ዕውቀት
ኢሄ ሁሉ ከንቱ ነዉ
ንፋስን እንደመከተል ነው

አዝ:- ከሚጠፉት እንዳልሆን ጠብቀኝ
ጌታ ሆይ ምህረትህን አብዛልኝ (፪x)

በአንደበቴ እንዳልረክስ
ወንድሜንም እንዳልተነኩስ
አቤቱ ማስተዋልን ስጠኝ
መንፈስ ቅዱስ ና አስተምረኝ

አዝ:- ከሚጠፉት እንዳልሆን ጠብቀኝ
ጌታ ሆይ ምህረትህን አብዛልኝ (፪x)

ዓይኔን ወደ አንተ እንዳቀና
መንፈስ ቅዱስ ናልኝና
ፈውሰኝ ቀድሰኝ
መጠቀሚያ ገንዘብህ አድርገኝ

አዝ:- ከሚጠፉት እንዳልሆን ጠብቀኝ
ጌታ ሆይ ምህረትህን አብዛልኝ (፪x)