Get Mystery Box with random crypto!

Gospel singer : Meskerem Getu ( NEW ) ከሰማይ ሰማያት ከዙፋኑ ወርዶ ከድንግ | Mezmur Legeta Lyrics

Gospel singer : Meskerem Getu ( NEW )

ከሰማይ ሰማያት ከዙፋኑ ወርዶ
ከድንግል ማርያም በበረት ተወልዶ
እንደ ፋሲካ በግ ስለ'ኛ ታረደ
ሞታችንን ሞተ ፍዳችንም ሄደ
ፍርድ ተወገደ!
አዎ ይወደናል! አዎን ያፈቅረናል
ነፍስን እስከ መስጠት
ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር የታል?
ኢየሱስ ያድናል! አዎን አድኖናል!
ከፊት እየመራ ወደ ጽዮን ያደርሰናል!
መልካም እረኛ ነው እጅግ የሚራራ
በለመለመ መስክ ህዝቡን የሚመራ
ከአብ ጋር ያስታረቀን ያደረገን ዘመድ
የህይወት በር ነው እውነት ነው መንገድ
አቤቱ ፍቅሩ ነው ብርቱ
አቤቱ አቤቱ ብዙ ቸርነቱ
አቤቱ አቤቱ ምህረቱ
አቤቱ አቤቱ እልፍ ቸርነቱ አቤቱ!
የተጠላነውን እንዲሁ ወደደን
ሰው ሆኖ የዓለምን ኃጢአት አስወገደ
ፍቅሩ ውቅያኖስ ነው በዘመናት ሁሉ
የወንጌል ማህበራት ለእርሱ እልል በሉ
ለጌታ ዘምሩ!
አዎ ቤዛችን ነው አዎ ተቤዥቶናል
ከኃጢአት ባርነት ነፃ አውጥቶ
የራሱ አድርጎናል
ኢየሱስ ያድናል! አዎን አድኖናል!
ከፊት እየመራ ወደ ጽዮን ያደርሰናል
አዎ ብርሃናችን ነው አዎ በርልቶልናል
ከአስፈሪው ጨለማ ከድቅድቁ ታድጎናል
ኢየሱስ ያድናል! አዎን አድኖናል!
ከፊት እየመራ ወደ ጽዮን ያደርሰናል!

YouTube Link and audio under comments