Get Mystery Box with random crypto!

ሩሖች ከስጋ ሳይዋኃዱ፣ ስጋዎች ከአፈርም ከፍትወት ጠብታም ሳይገነቡ፣ ምድርን ሰፋሪዎች ሳይሰፍሯት | ኡመተ ረሱል

ሩሖች ከስጋ ሳይዋኃዱ፣ ስጋዎች ከአፈርም ከፍትወት ጠብታም ሳይገነቡ፣ ምድርን ሰፋሪዎች ሳይሰፍሯት ምድር ሳትዋቀር በልዕላነ-አለሙ እንዲህ ሆኖ ነበር።

በሩሆች መከማቻ ስፍራ ህልቆ መሳፍርት ሩሆች ከሚገኙበት መንፈሰ-አለም ውስጥ አላህ 124 ሺህ
ሩሆችን መርጦ ከችሎተ - መለኮት ፊት አቆማቸው።

የዙፋኑ ጌታ ችሎቱን ያስደምጥ ጀመር።

«እናንተ ነብያት ሆይ! ወደ ምድር ወርዳችሁ ከኔ የሚመጡትን ትዕዛዛት ለባሮቼ ለማስተላለፍ መፃሕፍትን እና ጥበብን በሰጠኋችሁ ግዜ ሙሐመድ የተሰኘው ነብይ በእናንተ ዘመን ቢመጣ በሱ አምናችሁ ልትተባበሩትም ትገደዳላችሁ።»

ስፍራው በዝምታ ተውጧል።

የዙፋኑም ባለቤት ንግግሩን ቀጥሏል፦«ተስማምታችኋልን....? አሁን ባልኳችሁም በሙሀመድ ጉዳይ ቃል ኪዳንን ያዛችሁን? »

«ተስማምተናል፤ ታዛዦች ነን» ብለው ለነቢ ደረሳ ለመሆን እጅ ነሱ።
«እንግድያውስ ለመስማማታቹ ማስረጃ ይሆን ዘንድ በነፍሶቻችሁ ላይ መስክሩ፤ እኔም ከመስካሪዎች ነኝ» አለ።

«ነገር ግን...» የዙፋኑ ባለቤት ንግግሩን ቀጠለ።
«ይህን ቃል ኪዳን ከገባችሁ በኋላ ከእናንተ ውስጥ ሙሀመድን ከመታዘዝ የሚያፈነግጥ ካለ እሱ ወራዳ ይሆናል»

ነብያት ቃል ኪዳን ገብተው ሙሀመድንም አልቀው ለመታዘዝ ተስምተው የቃል ኪዳን ስፍራውን ለቀቁ።

ምድር ተዋቅራ ነዋርያኑን ማስተናገድ በጀመረችበት ግዜም ነብያቱ በየተራቸው ይተካኩ ጀመር። ሁሉም ነቢያት ያላዩትን ሙሀመድ ሰዐወ ሲናፍቁ የናፍቆት ጥማቸውን ሳይቆርጡም ዱንያን ተሰናበቱ።

ከሱ በፊት የነበሩትም ሆኑ ከሱ በኋላ የሚመጡ ህዝቦች ሲናፍቁት የሚኖሩለት ክቡር ስብዕና።

ቁጥር ማያካብበው የሰለዋት እና የተብሪካት አይነቶች በመለኮት መአዛ ታውደው እስከ እለተ ቂያማ ድረስ በነቢያቱ ንጉስ ላይ ይሁኑ።

#ሼር
#share #join
Https://t.me/smithhk