Get Mystery Box with random crypto!

ይህ ሁለት ገፅታ ያለው ሰው ማን ነው?! እጅግ ልብን የሚያደማ የኢራቁ ፕሮፌሰሩ ታሪክ በ | ኡመተ ረሱል

ይህ ሁለት ገፅታ ያለው ሰው ማን ነው?!
እጅግ ልብን የሚያደማ የኢራቁ ፕሮፌሰሩ ታሪክ

በተቀዳደደ ልብስና በቆሸሸ ድሪቶ ሰውነቱን ሸፍኖ በኢራቅ ጎዳናዎች ላይ ይዘዋወራል። ግና ምድር ላይ የሚራመድ ሊቅ በሁለት እግሩ የሚጓዝ የአቶሚክ ቦንብ ሳይንቲስትና ፕሮፌሰር ነበር።

ኢራቃውያን ተማሪዎች የከበዳቸው የትምህርት ዘርፍ ሲኖር ወደ እሱ በማቅናት ይጠይቁታል። እሱም አስፓልት ዳር በጣቱ ሲጋራውን ይዞ ፀጉሩን እየፈተለ ፈትፍቶ ያስረዳቸዋል። ዶክተር ሃሚድ ኸለፍ አል-ኦካይሊ ይሰኛል። ትውልደ ኢራቃዊ ነው። በኮምፕሌክስ አቶሚክ ቦንብ ዶክተር በኒውክለር ኬሚስትሪም ፕሮፌሰር ነው።

የካምብሪጅ ብሪቲሽ ዩኒቨርሲቲ ሌክቸሩ ሃሚድ የቆሸሸውን ልብሱን አጥልቆ ረዥም ፀጉሩ ከመሬት አፈር ጋር ተለውሶ ለሚመለከተው ሁሉ በእጅጉ አግራሞትን ይጭራል። አዋቂው እብድም ይሉታል።

ዕድሜ ለአሜሪካ!
ሙሉ ቤተሰቦቹን በጅምላ ሲገድሉበት በዓይን በብረቱ ተመልክቷል። ለወሬ ነጋሪነት እንኳ አንድም አላስተረፉለትም። እናት አባቱ ልጆቹ ሚስቱ ፊት ለፊቱ ነበር የወደቁት። ይህን ልብ አድሚ ክስተት እያነባ ሲመለከት ቆይቶ ከህመሙ ጋር እንዲኖር በካቴና ተጠፍሮ ወደ እስር ቤት አቀና።

እስር ቤት መኖርያው ሆነ። ዘወትር ጁሙዐ ከሌሎች ቀናቶች በተለየ ሽንት ቤት መቀመጫ ላይ በአፉ ተገልብጦ እርቃኑን ከብረት ጋር ተጠፍሮ የሽንትና የሰገራ ሽታ በአፍ በአፍንጫው እየተጋተ ያሳልፋል። እንደ እንሰሳ አንገቱ ላይ ሰንሰለት ተደርጎ በተከበረ ፊቱ ይጎተታል። መሬት ላይ የወዳደቁ ቆሻሻዎችን በምላሱ እያፀዳ በርካታ ቀንና ለሊቶችን ለረጅም ሰአት እየቆመ አሳለፈ። ትንሽ ከስቃዩ ፋታ ሲያገኝ በሐሳብ ጭልጥ ብሎ ቤተሰቦቹን ያስታውሳል። እናቱ በአሜሪካ ወታደሮች ተጨፍጭፋ ስትገደል ልጆቹ እግሩ ስር እየተወራጩ ሲያነቡ በወታደሮቹ ከስክስ ጫማ እየተረገጡ ሲደፈጠጡና የጥይት እራት ሲሆኑ ያስታውሳል። አዎ መጥፎ ትውስታውና ቶርቸሩ ተደራርቦ በደረሰበት ስቃይ የአዕምሮ በሽተኛ ሆነ። ከእስር ቤት ሲወጣ ቤትና ንብረቱ እንኳ አልተረፈ ሁሉም ተዘርፎ ባዶ ቀረ።

አዎ ማንኛውም ሙስሊም በመስቀላዊያኖች እየተሰራች ባለችው በአዲሲቷ የአለም ስርአት ውስጥ ሳይንቲስት የመሆን መብት የለውም።

ሰምተን ዓይናችን ሳያነባ በዝምታ ያለፍናቸው ብዙ መሰል ታሪኮች ይኖራሉ። እኛ ብንረሳቸውም አላህ ግን ፈፅሞ የማይረሳቸው በእርግጥም የእርሱ ባሮች አሉ። መገን አላህዬ አቻቻልህኮ።

#ሼር
#share #join
Https://t.me/smithhk