Get Mystery Box with random crypto!

'በሰማያት ላለው አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ እርሱ ለክፉዎችና ለደጎች ፀሀይን ያወጣልና። ለፃድቃን | ቅድስት ፌብሮኒያ

"በሰማያት ላለው አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ እርሱ ለክፉዎችና ለደጎች ፀሀይን ያወጣልና። ለፃድቃን ፣ለኃጥአንም ዝናብን ያዘንማልና። የሚወዱአችሁን ብትወዱ ዋጋችሁ ምንድን ነው? እንዲህማ ቀራጮችስ ያደርጉ የለምን? ወንድሞቻችሁን ብቻ እጅ ብትነሱ ምን ብልጫ ታደርጋላችሁ? አሕዛብስ ይህንን ያደርጉ የለምን? እንግዲህስ ሰማያዊ አባታችሁ ፍፁም እንደሆነ እናንተም ፍፁማን ሁኑ"
ማቴ 5፥45-48
አንድ ሰው ቢበድለን እግዚአብሔር ለእኛ እንደራራልን እኛም ልንራራለት ይገባል።ለዚህ ሰው ማዘን ያስፈልጋል ምክንያቱም ጊዜው በከንቱ እያለቀ እንደሆነ ስለምንረዳ ነው። እግዚአብሔር እኛን እንደሚወደን እኛም እርስ በርሳችን እንዋደድ። አንድ ሰው ሕይወቱን ለጓደኛው ከመስጠት በላይ ፍቅር የለም።ይህ ጌታ ለእኛ ያደረገው ነው።ከእኛ የሚጠበቀው ሕይወትም ይህን ነው። አምላካችን እግዚአብሔር ለሁላችን ንፁህ ልብን ይፍጠርልን።
ምስጋና ይሁን አንድ አምላክ ለሚሆን ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሜን።

@Slehiwetwe ይቀላቀሉን።