Get Mystery Box with random crypto!

ሲራራ ጋዜጣ

የቴሌግራም ቻናል አርማ sirara789 — ሲራራ ጋዜጣ
የቴሌግራም ቻናል አርማ sirara789 — ሲራራ ጋዜጣ
የሰርጥ አድራሻ: @sirara789
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 432
የሰርጥ መግለጫ

በየሳምንቱ ቅዳሜ እየታተመች ለአንባቢያን ትደርሳለች።

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-27 11:51:53 ህብረተሰቡ የዶሮ ስጋ እና እንቁላልን ያለ ስጋት መጠቀም እንደሚችል ተገለጸ

የኢትዮጲያ ዶሮ አርቢዎች እና አቀናባሪዎች ማህበር ለሲራራ ጋዜጣ በላከው መግለጫ በአሁኑ ሰአት ህብረተሰቡ የዶሮ ስጋ እና እንቁላልን ያለ ስጋት መጠቀም እንደሚችል አስታውቋል፡፡

በቅርቡ በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች በጥቂት የዶሮ እርባታ ማዕከላት ውስጥ የዶሮ በሽታ ተከስቶ እንደነበር ያስታወሰው ማህበሩ በሽታውን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ከግብርና ሚኒስቴር ጋር ሲሰራ መቆየቱን አስታውቋል፡፡

በሽታውን ለመቆጣጠር ያስችል ዘንድ በጊዚያዊነት በዶሮና እንቁላል ምርቶች ላይ የግብይት እንቅስቃሴ ገደብ መጣሉን ያስታወሰው ማኅበሩ፡፡
አሁን ላይ በሽታውን በቁጥጥር ስር ማዋል በመቻሉ እና የግብርና ሚኒስቴርም ጥሎት የነበረውን ገደብ በማንሳቱ ህብረተሰቡም ሆነ ዶሮ አርቢዎች ምርቶቹን ያለ ስጋት መገበያየት እንደሚችሉ ማህበሩ በመግለጫው ላይ አመላክቷል፡
136 views08:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 09:51:50
ኢትዮጵያ በጠየቀችው የተራዘመ የብድር አቅርቦት ላይ በመስከረም ድርድር እንደሚጀመር አይ ኤም ኤፍ ፍንጭ ሰጠ

ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) በጠየቀችው የተራዘመ የብድር አቅርቦት (Extended Credit Facility) ላይ በ2015 ዓ.ም. የመጀመሪያ ወራት ድርድር ሊጀመር እንደሚችል ተቋሙ ፍንጭ ሰጠ። ድርጅቱ በሳምንቱ መጀመሪያ ከኢትዮጵያ አበዳሪዎች ኮሚቴ ጋር በተደረገ ስብሰባ ላይ ለሀገሪቱ “አዲስ የተራዘመ የብድር አቅርቦት ስምምነት ለማጽደቅ ያስፈልጋሉ” ያላቸውን ቅድመ ሁኔታዎች ዘርዝሯል።

ፈረንሳይ እና ቻይና በተባባሪ ሊቀመንበርነት በሚመሩትን ባለፈው ሰኞ ሐምሌ 11፤ 2014 በተካሄደው የኢትዮጵያ አበዳሪዎች ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የተገኘው፤ በሀገሪቱ የኢኮኖሚ ሁኔታ ላይ ማብራሪያ ለማቅረብ ነበር። “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ያነጋገረቻቸው ድርድሩን በቅርበት የሚከታተሉ የፋይናንስ ባለሙያ፤ ባለፈው ሰኞ በተካሄደው የአበዳሪዎች ኮሚቴ ስብሰባ ላይ አይ ኤም ኤፍ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ይዞታ በተመለከተ ያቀረበው ማብራሪያ ለሂደቱ “አዎንታዊ ሚና” ሊኖረው ይችላል ይላሉ። ባለሙያው እንደሚሉት ሶስተኛው የኢትዮጵያ አበዳሪዎች ኮሚቴ ስብሰባ ተጨባጭ ለውጥ የሚታይበት ሊሆን ይችላል።

(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
856 views06:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 13:03:48 "በኢትዮጵያ በሕይወት የመኖር መብት እጅግ የከፋ አደጋ ውስጥ ወድቋል" ኢሰመኮ

የኢትዮጵያ ሰብዊ መብቶች ኮሚሽን ከሰኔ 2013 እስከ ሰኔ 2014 ዓ.ም በሀገሪቱ በተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ዓመታዊ ሪፖርት ላይ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) አንዳሉት ባለፉት 12 ወራት በሕይወት የመኖር መብት እጅግ በከፋ ሁኔታ ውስጥ እንዳለ ቀጥሏል ብለዋል። በዓመቱ የትግራይ ጦርነት ወደ አማራ ክልል መስፋፋቱን ተከትሎ ሆን ተብሎ በትግራይ ኀይሎች በተወሰዱ ርምጃዎች 346 ሲቪል ሰዎች መገደላቸውን ተናግረዋል።

በኦሮሚያ ክልል በተለይ በወለጋ ዞኖች ከነሐሴ 2013 ዓ.ም ጀምሮ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በተደጋጋሚ በተፈፀመ ጥቃት በአብዛኛው በአማራ ብሔር የገጠር እና የከተማ ነዋሪዎች ላይ ያነጣጠረ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ሕፃናት ሴቶችን ጨምሮ ሲቪል ሰዎች ተገድለዋል ብለዋል።

ዶ/ር ዳንኤል ወንጀሉ በሰብአዊነት ላይ የተፈፀሙ ግፎች፣ የጦር ወንጀሎች እና ሌሎች ወንጀሎች አንደኾኑ ገልጸው ጉዳዩ የዘር ማጥፋት አንደኾነ ገና ጥናት ተደርጎ የሚረጋገጥ መኾኑን ጠቅሰዋል፡፡ ኮሚሽነሩ ጥቃቱ ግን ብሔር ተኮር መኾኑን አረጋግጠናል ብለዋል። ጥናት ለማድረግ አካባቢው ገና አመች ያልኾነ እና ከባድ ወታደራዊ አንቅስቃሴ ያለበት በመኾኑ ጥናቱ ይቆያል ነው ያሉት።

ከዘፈቀደ እስር እና ጠለፋ አንዲሁም አስገድዶ ከመሰወር ጋር በተገናኘ በዓመቱ በተለይ በሰሜኑ ጦርነት የተሳተፉ ሁሉም ኀይሎች በሰላማዊ ዜጎች ላይ በዘፈቀደ እስር ጠለፋ እና አስገድዶ መሰወር ፈጽመዋል ብለዋል። ይህም በሰበዓዊነት ላይ የተፈፀመ ወንጀል ሲኾን ዓለም አቀፍ የጦር ወንጀል ሊኾን በሚችል መልኩ ተፈጽሟል ብለዋል።

በዓመቱ በአማራ ክልል ብቻ ሕግን እና ሰላምን ለማስከበር በሚል ምክንያት ከ10 ሽሕ ሰዎች በላይ በኢመደበኛ ኀይሎች ታጣቂዎች አባል ናችሁ በሚል እና የተፎካከሪ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ጭምር ከፍርድ ቤት ትእዛዝ ውጭ ታስረዋል ብለዋል።

ከአመለካከት እና ሐሳብን በነጻነት ከመግለጽ መብት ጋር በተገናኘ በተለያዩ ወቅቶች 39 የሚዲያ ሠራተኞች ተይዘው ከቀናት እስከ ወራት በእስር እንዲቆዩ መደረጋቸውን አስረድተዋል። በትግራይ ክልል ይህ ሪፖርት ይፋ አስከተደረገበት ጊዜ ድረስ 15 የሚዲያ ሠራተኞች በክልሉ ባለስልጣናት ትእዛዝ እንደታሰሩም አስረድተዋል።

በእስር ላይ ያሉ እና የተያዙ ሰዎችን መብቶች በተመለከተ ፖሊስ ጊዜውን ጠብቆ ለፍርድ ቤት አለማቅረብ፣ የዋስ መብት የተፈቀደላቸውን ተጠርጣሪዎችን ከእስር አለመልቀቅ፣ በታሳሪዎች ላይ ያለአግባብ አያያዝ፣ ለኮሚሽኑ ባለሙያዎች በቂ መረጃ አለመስጠት እና ተባባሪ አለመኾን። የፍርድ ቤት ትእዛዝን አለማክበር እና ሌሎችም ተፈጽመዋል ብለዋል።

በግጭት እና የፈጥሯዊ አደጋ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ከቀያቸው እና ከመደበኛ መኖሪያው መፈናቀላቸውንም ጠቅሰዋል። በዚህም በተጠለሉበት ቦታ በከፍተኛ ችግር ውስጥ አንደሚኖሩ ጠቅሰው መሰረታዊ ፍላጎቶች ማቅረብ ላይም ከፍተኛ ችግር መኖሩን አመላክተዋል። ተበዳዮችን ከመካስ እና አጥፊዎችን ተጠያቂ ከማድግ አንጻርም ብዙ ሥራ እንደሚቀር ገልጸዋል።
281 views10:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 12:49:37 https://fb.watch/e7JO9zFBQH/
189 views09:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 16:24:42
አሐዱ ባንክ አ.ማ. ሥራ መጀመር

አሐዱ ባንክ ሐምሌ 9 2014 ዓ.ም በይፋ ሥራ ሊጀመር መሆኑን አስታወቀ።

ባንኩ ከምርቃቱ ዕለት አንስቶ እስከ መስከረም 30 2015 ዓ.ም ድረስ የቅርንጫፎቹን ቁጥር ሐምሳ እንደሚያደርስ አሳውቋል።

በርካታ አዳዲስ ጽንስ ሐሳቦችን ይዤ መጥቻለሁ የሚለው ባንኩ በየዓመቱ ከሚያቀርበው ብድር እስከ 15 በመቶ የሚሆነውን የፋይናንስ አቅርቦት ለስራ ፈጣሪዎች እና ለአነስተኛ ኢንተርፕራይዞች አመቻቻለሁ ብሏል፡፡ብዛት ያላቸው የባንክ አገልግሎት ወኪሎችንም ይዞ ወደ ገበያ ይገባል ተብሏል።

አሐዱ ባንክ ማኅበራዊ ግዴታውን ከመወጣት አንጻርም የተለያዩ ተግባራትን እንደሚያከናውን በሰጠው መግለጫ ላይ አጽንዖት ሰጥቷል፡፡ባንኩም የሎጎ ለውጥ ማድረጉንም በመድረኩ ላይ ዕወቁልኝ ብሏል፡፡የሎጎ ለውጡ ኢትዮጵያዊነትን እና ዓለም አቀፋዊነትን የያዘ ነው ተብሎለታል፡፡በቀላሉ ሊረዱት የሚችሉት ዓይነት ስለመሆኑም በዘገባው ላይ ተነስቷል፡፡

ባንኩ በ17 አደራጅ ኮሚቴ ዓባላት 2012 ዓ.ም ተጠንስሶ 10ሺሕ የሚደርሱ ባለአክሲዮኖችን አሰባስቦ በ5መቶ64 ሚሊዮን የተከፈለ ካፒታል እና በ702 ሚሊዮን የተፈረመ ካፒታል ስራውን እንደሚጀምር ተነግሯል።

በኢትዮጵያ የብድር ስርጭቱ መዛባት ግምት ውስጥ ሲገባ መበደር ከሚችለው ዜጋ የብድር ተጠቃሚ የሆነው ከ1በመቶ በታች ነው የሚለው ባንኩ ከተደራሽነት አንጻርም በርካታ ስራዎችን እሰራለሁ ብሏል፡፡

ዜጎች ባሉበት ቦታ ሆነው ራሳቸውን የባንኩ ደንበኛ ማድረግ የሚችሉበትን አሰራር ይዘን መጥተናልም ብሏል ባንኩ።ደንበኞች ከተለመደው በሰራተኛ የታገዘ የቅርንጫፍ አሰራር አገልግሎት በተጓዳኝ ደንበኞች በራሳቸው የዲጂታል አገልግሎት የሚያገኙበት የቅርንጫፍ ውስጥ አገልግሎት አደረጃጀት ተመቻችቷልም ተብሏል።

#አሐዱ
917 views13:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 12:43:53
የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰሞኑ የተፈፀሙ ግድያዎችን የሚያጣራ ኮሚቴ እንዲቋቋም ውሳኔ አሳለፈ

በኢትዮጵያ በኦሮሚያ እና ጋምቤላ ክልሎችን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች በዜጎች ላይ የተፈጸሙ ኢ-ሰብዓዊ ጭፈጨፋዎችን የሚያጣራ ልዩ ኮሚቴ እንዲቋቋም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወሰነ። በፓርላማው የበላይ አመራር የሚሰመው ይህ ልዩ ኮሚቴ “ለቀጣይ እርምጃዎች የሚረዳ ምክረ ሃሳብ” እንዲያቀርብ ኃላፊነት ተጥሎበታል።

የተወካዮች ምክር ቤት ይህን ውሳኔ ያሳለፈው ዛሬ ረቡዕ ሰኔ 29፤ 2014 ባካሄደው 6ኛ ልዩ ስብሰባ ላይ ነው። በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በዜጎች ላይ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ እና የዜጎችን ጸጥታ እና ደህንነት ለማስጠበቅ በተንቀሳቀሱ የጸጥታ አካላት ላይ የደረሰውን የህይወት መጥፋት “እጅግ የሚኮነን” መሆኑን ፓርላማው አስታውቋል። ምክር ቤቱ በዚህ መሰረት ካካሄደው ውይይት በኋላም ስድስት ውሳኔዎችን አሳልፏል።
204 views09:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-25 19:41:00
301 views16:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-25 19:40:56 የአዲስ ቻምበርን ታሪክ የሚዘክር መጽሐፍ ታተመ

ማክሰኞ፣ ሰኔ 21 ቀን 2014ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት በስካይላይት ሆቴል ይመረቃሉ


በ1939ዓም በቻርተር የተቋቋመው የአዲስ አበባ ንግድ ም/ቤት ዛሬ ላይ የ75 አመት አረጋዊ ሆኗል፡፡

75ኛ የምሥረታ በዓሉን ባማረ ሥነስርዓት ለማክበር በአብይ ኮሚቴ አና ሌሎች 16 ንዑሳን ኮሚቴዎች ተቋቁመው ልዩ ልዩ ተግባራትን ሲያከናውኑ ቆይተዋል፡፡ ከእነዚህ መካከል የም/ቤቱን ወጥ ታሪክ የሚያወሳ አዲስ መጽሐፍ ማዘጋጀት ይገኝበታል፡፡

መጽሐፉ በገለልተኛ እና ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች የተጻፈ ሲሆን ንግድ ም/ቤቱ በእነዚህ ረጅም አመታት ውስጥ በትውልድ የቅብብሎሽ ሰንሰለት ላይ ያለፈባቸውን መልካም እና ፈታኝ ሁኔታዎችን የሚዘክር ሲሆን የወደፊቱን የጉዞ አቅጣጫ የሚጠቁም ጭምር ነው ተብሏል፡፡

‘የ75 ዓመቱ እንደራሴ፡ የአዲስ ቻምበር ጉዞ’ በሚል ርዕስ በም/ቤቱ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀው ይኸው ወጥ የታሪክ መጽሐፍ ከሃሳብ ጥንስስ ጀምሮ እስከ ዛሬው የም/ቤቱ ተቋማዊ አደረጃጀት እና የወደፊት ራዕይ በተደራጀ መልኩ ዝርዝር መረጃዎችን አካትቷል፡፡

ይኸው መጽሐፍ ለአሁኑ እና ለሚመጣው ትውልድ ስለ ምክር ቤቱ ታሪክ የሚያስረዳ ቋሚ ሠነድ ሆኖ የሚያገለግል ሲሆን በተጨማሪም በአገሪችን የዘመናዊ ንግድ ታሪክ ላይ ጥናት እና ምርምር ለሚያደርጉ ተመራማሪዎች ሁነኛ የመረጃ ምንጭ ሆኖ አንደሚያገለግል ተነግሯል፡፡

መጽሐፉ በውስጥ ይዘቱ ም/ቤቱ ያለፈባቸው ምልካም እና ፈታኝ ሁኔታዎችን የሚዳስሱ፤ የንግዱ ሕብረተሰብ መብት እና ጥቅሞች እንዲከበሩ ስለተደረጉ ጥረቶች፤ እንዲሁም የነጋዴውን እንቅስቀሴ የሚያውኩ የፖሊሲ ሕፀፆች አንጻር የተደረጉ የአድቮከሲ ጥረቶች ይዳስሳል፡፡

የአገራችን የአለማቀፍ ንግድ ግንኙነት እንዲጎለብት መንግስት ከሚያደርገው ጥረት ጎን ለጎን ም/ቤቱ ለአመታት ሲያከናውናቸው የቆየውን የንግድ ማስፋፊያ እና የፕሮሞሽን ሥራዎች በተለይም በውጪ እና በአገር ውስጥ ነጋዴዎች መካከል የንግድ-ለንግድ ውይይት መድረኮች በማዘጋጀት፤ በየአመቱ ዓለማቀፍ የንግድ ትርዒቶችን በማዘጋጀት ያደረገውን አስተዋጽኦ ያስነብባል፡፡

ምክር ቤቱ ለአባላቱ ሲሰጥ ከቆየው አገልግሎቶች መካከል በንግዱ ሕብረተሰብ መካከል በሚፈጠሩ ውዝግቦች ሳቢያ በጋዴዎች ላይ የሚደርሰውን እንግልት፤ተጨማሪ ወጪ እና ጊዜ ለማስቀረት በራሱ የግልግል ዳኝነት ተቋም በኩል የሚያደገውን ድጋፍ ፤የአባላት ልማት ፤ የሥልጠና እና ንግድ ነክ የሆኑ መረጃዎችን በራሱ የሕትመት ውጤቶች አማካኝነት መረጃዎችን ሲያቀርብ መቆየቱን የሚዘክሩ እና ሌሎች ታሪካዊ ክንውኖች ይገኙበታል፡፡

የንግድ ም/ቤቱ የተሳተፈባቸው የማሕበራዊ ኃላፊነት ሥራዎች ጭምር በዚሁ መጽሐፍ በሥዕላዊ ማስረጀዎች ታጅበው እንደተሰነዱ ተነግሯል፡፡

መጽሐፉ በ19 ምዕራፎች የተዋቀረ ሲሆን 359 ገጾች አሉት::

‘‘ራዕያችን’’ የተሰኘው የም/ቤቱ ሕብረዝማሬ ተሻሽሎ ተዘጋጀ

በ1993 ዓም የተዘጋጀው እና ዘወትር የአዲስ ቻምበር የሬድዮ ፕሮግራም መክፈቻ ሆኖ ሲያገለግል የቆየው እና በሕዝብ ጆሮ የተለመደው ‘ ራዕያችን’ የተሰኘው ዝማሬ መሠረቱን ሳይለቅ በተሻለ የድምጽ ጥራት እና ባማረ ሙዚቃዊ ቅንብር እንደገና ተዘጋጅቶ ወጣ፡፡

የፊተኛው መዝሙር (ጅንግል) በማርሽ ባንድ ታጅቦ የተቀነባበረ ሲሆን ለሬዲዮና ቴሌቪዥን ማስታወቂያዎች እንዲሁም ለዶክመንተሪዎች በማጀቢያነት እያገለገለ ይገኛል።

አሁን ተሻሽሎ የወጣው ቅጂ የዘማሪዎቹን ድምጽ በጥራት እንዲሰማ ተደርጎ በነፍስወከፍ የሙዚቃ መሣሪያዎች ታጅቦ ለጆሮ እዲስማማ በአማካሪ ባለሙያዎች ( Abiy Arka and etal) እንደተቀናበረ ተነግሯል፡፡

የዚሁ መዝሙር ግጥም ሃሳቡና መልእክቱ ዘመን ተሻጋሪ የሆነ እና ዛሬም ድረስ በግጥሙ ውስጥ የተነሱት ጉዳዮች የቻምበሩ ጉዳዮች እነደሆኑ ለምክርቤቱ የ75ኛ የምሥረታ በአል በተዘጋጀው የታሪክ መጽሐፍ ላይ ተገልጿል።

የመዝሙሩ ስንኞች ሕዝብን ለሥራ የሚያነሳሱ፤ እድገትን የሚሰብኩ፤ስንፍናን የሚኮንኑ፤ ሰርቶ ማግኘትን የሚያወድሱ፤ነጋዴው ለወገኑ ችግር ደራሽ መሆኑን እና ባንዲራ እና ጠንካራ የሀገር ፍቅር ያለው ሕብረተሰብ እንዲሆን የሚያንጹ፤ አገራችን በልጆቿ ሕብረት በልምላሜ እና በሰላም ደምቃ አንድትኖር በሚመኙ በብሩሕ ተስፋ ባዘሉ መልዕክቶች ለትውልድ እንዲያስተላለፉ በጥንቃቄ የተጻፉ እንደሆኑ አዘጋጆች ተናግረዋል፡፡

የግጥሙና የዜማ ደራሲው አቶ ዘገየ ኃይሌ ጀማነህ የተባሉ ሰው አንደሆኑ በመጽሐፉ ተወስቷል፡፡

የም/ቤቱ የሬድዮ ዝግጅት ዘወትር ሐሙስ ከቀኑ 6፡40 – 7፡00 ሰዓት በኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ሬዲዮ ጣቢያ በሚያዝያ ወር 1993 ዓ.ም ማስተላለፍ እንደተጀመረ ለማወቅ ተችሏል፡፡

በአሁኑ ወቅት ደግሞ በአዲስ ሚዲያ ኔትዎር FM 96.3 በማስተላለፍ ላይ ይገኛል::
418 views16:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 19:33:01
ኢትዮጵያ እና የዓለም ባንክ የ600 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የፋይናንስ ድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ

የገንዘብ ሚኒስቴር ከዓለም ባንክ ጋር የ600 ሚሊየን ዶላር የድጋፍና የብድር ስምምነት ተፈራረመ።

ከ600 ሚሊየን ዶላር ውስጥም 200 ሚሊየን ዶላሩ በድጋፍ መልክ ሲሆን፥ 400 ሚሊየን ዶላሩ በብድር መልክ ነው።

ስምምነቱ በኢትዮጵያ ያለውን የስርአተ ምግብ ለማሻሻል እና የምግብ እጥረት አደጋን ለመቀነስ የሚውል መሆኑ ተገልጿል።

ገንዘቡ የምግብ እጥረት አለባቸው ተብለው በተለዩ የሃገሪቱ ክፍሎች የምግብ እጥረት አደጋን ለመቀነስ ብሎም የስርአተ ምግብን ለማሻሻል የሚውል ይሆናል።

ከዚህ ባለፈም የአርብቶ አደሮችን የኢኮኖሚ ልማት በማሳደግ የድርቅ ተጋላጭነታቸውን ለመቀነስ እንደሚውል ተገልጿል።
204 views16:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 15:38:58
ዳሸን ባንክ ዘመናዊ የመረጃ ማዕከል አስመረቀ

በኢትዮጵያ የባንክ አገልግሎት ታሪክ ውስጥ የአዲስ ዘመን ጅማሮ ተደርጎ ሊወሰዱ የሚችሉትን የኤሌክትሮኒክ ክፍያ እና የሞባይል ካርድ አገልግሎቶች በማስተዋወቅ ረገድ ፈር ቀዳጅ የሆነው ዳሸን ባንክ፣ ዘመናዊና በግል የፋይናንስ ተቋም ደረጃ የመጀመሪያ የሆነውን Tier III የመረጃ ማዕክል አስመረቀ፡፡

የመረጃ ማዕከሉ ከፍተኛ ኃይል ያላቸውን ከ1,000 ያላነሱ ሰርቨሮችና ሌሎች ተያያዥ የኔትወርክ መሳሪያዎችን የማስተናገድ አቅም ያለው ነው፡፡ በጥገና ወቅትም መደበኛ የባንኩን ስራ ሳያቋርጥ አመቱን ሙሉ አገልግሎት መስጠት የሚችል ነው፡፡

የመረጃ ማዕከሉ በአካባቢው የሚስተዋሉ የተለያዩ ክስተቶችን በመለየት ለማዕከሉ ዋና የመቆጣጠሪያ ክፍል መረጃ ማስተላለፍ የሚችል ሲሆን፣ ችግር ሲከሰትም ችግሩን በመለየት ስጋቶችን ለማስቀረት በሚችል ዓለማቀፋዊ ደረጃውን የጠበቀ ቴክኖሎጂ የተሟላ ነው፡፡
ይህ የመረጃ ማዕከል ዘመናዊ የባንክ አገልግሎትን ከየትኛውም ቦታ ማግኘት የሚያስችልና ባንኩ የተለያዩ አዳዲስ አገልግሎቶችን ያለምንም ችግር ወደ ስራ ለማስገባት የሚያግዘው ይሆናል።
በተጨማሪም ባንኩ በዲጂታል ዘርፍ አዳዲስ አገልግሎቶችን በማስተዋወቅና የአገልግሎቱንም ደህንነትና ጥራት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ ሁነኛ ሚና ይኖረዋል።

ይህ ማዕከል የዳሸን ባንክን ፍላጎት ከማሟላት ባሻገር በስራ ላይ ለሚገኙ እና ወደ አገሪቱ የባንክ ኢንዱስትሪ ለሚቀላቀሉ የአገር ዉስጥም ሆነ የዉጭ ባንኮች እንዲሁም ለሌሎች ተቋማት አገልግሎት መስጠት የሚችል አቅም ያለዉ ነዉ፡፡

በዳታ ማዕከሉ ምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ የብሔራዊ ባንክ ገዢ፣ የባንኮች ስራ አስፈፃሚዎች፣ የተለያዩ ድርጅት ኃላፊዎች፣ የባንኩ የስራ አመራር ቦርድ አባላት፣ የባንኩ የበላይ አመራሮች፣ ተገኝተዋል።

ሰኔ 16/2014
194 views12:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ