Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያ በጠየቀችው የተራዘመ የብድር አቅርቦት ላይ በመስከረም ድርድር እንደሚጀመር አይ ኤም ኤፍ | ሲራራ ጋዜጣ

ኢትዮጵያ በጠየቀችው የተራዘመ የብድር አቅርቦት ላይ በመስከረም ድርድር እንደሚጀመር አይ ኤም ኤፍ ፍንጭ ሰጠ

ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) በጠየቀችው የተራዘመ የብድር አቅርቦት (Extended Credit Facility) ላይ በ2015 ዓ.ም. የመጀመሪያ ወራት ድርድር ሊጀመር እንደሚችል ተቋሙ ፍንጭ ሰጠ። ድርጅቱ በሳምንቱ መጀመሪያ ከኢትዮጵያ አበዳሪዎች ኮሚቴ ጋር በተደረገ ስብሰባ ላይ ለሀገሪቱ “አዲስ የተራዘመ የብድር አቅርቦት ስምምነት ለማጽደቅ ያስፈልጋሉ” ያላቸውን ቅድመ ሁኔታዎች ዘርዝሯል።

ፈረንሳይ እና ቻይና በተባባሪ ሊቀመንበርነት በሚመሩትን ባለፈው ሰኞ ሐምሌ 11፤ 2014 በተካሄደው የኢትዮጵያ አበዳሪዎች ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የተገኘው፤ በሀገሪቱ የኢኮኖሚ ሁኔታ ላይ ማብራሪያ ለማቅረብ ነበር። “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ያነጋገረቻቸው ድርድሩን በቅርበት የሚከታተሉ የፋይናንስ ባለሙያ፤ ባለፈው ሰኞ በተካሄደው የአበዳሪዎች ኮሚቴ ስብሰባ ላይ አይ ኤም ኤፍ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ይዞታ በተመለከተ ያቀረበው ማብራሪያ ለሂደቱ “አዎንታዊ ሚና” ሊኖረው ይችላል ይላሉ። ባለሙያው እንደሚሉት ሶስተኛው የኢትዮጵያ አበዳሪዎች ኮሚቴ ስብሰባ ተጨባጭ ለውጥ የሚታይበት ሊሆን ይችላል።

(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)