Get Mystery Box with random crypto!

ሲራራ ጋዜጣ

የቴሌግራም ቻናል አርማ sirara789 — ሲራራ ጋዜጣ
የቴሌግራም ቻናል አርማ sirara789 — ሲራራ ጋዜጣ
የሰርጥ አድራሻ: @sirara789
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 432
የሰርጥ መግለጫ

በየሳምንቱ ቅዳሜ እየታተመች ለአንባቢያን ትደርሳለች።

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-06-22 16:16:13
አምባሳደር መለስ ዓለም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ሆነው ተሾሙ

ላለፉት ሦስት ዓመታት በኬንያ የኢትዮጵያ በባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደርነት ያገለገሉት መለስ ዓለም ሚኒስቴሩ በቅርቡ ባካሄደው ማሻሻያ እንደ አዲስ የተዋቀረውን ይህን ዳይሬክተር ጄኔራል እንዲመሩ ተሹመዋል።

ቀደም ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የነበሩት አምባሳደር ዲና ሙፍቱ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሆነው መሾማቸው ታውቋል።
213 views13:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 11:05:51
ማዕድን ሚኒስቴር 972 ፈቃዶችን መሠረዙን አስታወቀ

116 የማዕድን ፍለጋ ፈቃዶች ተሠርዘዋል።

የማዕድን ሚኒስቴር  የማዕድናት ፍለጋ ፈቃድ ወስደው ለረጅም ጊዜያት በገቡት ውልና አቅርበው ባፀደቁት መርሀ ግብር መሠረት መስራት ባልቻሉ ኩባንያዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስተወቀ።

ኩባንያዎቹ ሚኒስቴሩን ጨምሮ በየደረጃው ባሉ ባለድርሻዎች ማስጠንቀቂያ ቢሰጣቸውም በሚገባው መልኩ ወደ ልማት ባለመግባታቸው የ116 ኩባንያዎች የማዕድን ፍለጋ ፈቃድ መሠረዙን የማዕድን ሚኒስትሩ ኢ/ር ታከለ ኡማ ተናግረዋል።

በተጨማሪም በማዕድናት ምርት ፈቃድ ወስደው ነገር ግን በአግባቡ አልሰሩም የተባሉ የ6 ኩባንያዎች ፈቃድ ተሰርዟል ።

ከወርቅ ማዕድናት ውጪ ያሉ ሌሎች ማዕድናት ወደ ውጪ ለመላክ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ወስደው ፈቃድ የተሠጣቸው ነገር ግን በህጋዊ ሽፋን  በኮንትሮባንድ ንግድ ላይ ተሠማርተው የተገኙ 850 የማዕድን ላኪዎች ፈቃድ መሠረዙን ሚኒስትሩ ተናግረዋል ።

በአጠቃላይ 972 በማዕድን ምርመራ ፤ ምርትና ኤክስፖርት ዙሪያ ፈቃድ የወሰዱ ኩባንያዎች ፈቃድ ተሰርዟል ።

በክልሎች በኩል የተሠጡ ፈቃዶች በዚህ ወር መጨረሻ ተገምግሞ ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ ከስምምነት መደረሱን ገልጸዋል ።
216 views08:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-20 16:48:31
የውጭ አገራት ባንኮች ወደ አገር ውስጥ ሲገቡ የሚተገበር የአሰራር ሥርዓት እየተዘጋጀ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ።

የኢትዮጵያን የባንክ ኢንዱስትሪ ለውጭ አገራት ክፍት ለማድረግ የፖሊሲ ማሻሻያ በማድረግ ወደ ሥራ ለመግባት በሂደት ላይ ይገኛል።

በመሆኑም ዘርፉ ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆን በተወሰኑ ተዋናዮች ብቻ ታጥሮ የቆየው የባንክ ኢንዱስትሪ ለውጭ ባንኮች ክፍት የማድረግ እንቅስቃሴ ተጀምሯል።

በዚህም መሰረት ባንኮቹ ወደ አገር ውስጥ ሲገቡ ዘርፉ የሚመራበት የአሰራር ሥርዓት እየተዘጋጀ መሆኑን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የባንክ ቁጥጥር ዳይሬክተር ፍሬዘር አያሌው ገልጸዋል።

የባንኮች ወደ አገር ውስጥ መግባት ለእውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ የውጭ ምንዛሪ ፍሰትን ለመጨመር፣ የብድር አገልግሎትን ለማስፋትና ሌሎችም ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታዎች አሉት።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ የሚደረገውን የምጣኔ ሃብት እንቅስቃሴ በፋይናንስ መደገፍና አዳዲስ አሰራሮችን ያመጣሉ ተብሎም ይጠበቃል ብለዋል።

የባንኮቹ ወደ አገር ውስጥ መግባት ከሚኖረው ጠቀሜታ ባለፈ በሂደቱ ሊያስከትል የሚችለውን ስጋት ሊቀንስ የሚችል የህግ ማዕቀፍና የአሰራር ሥርዓት እየተዘጋጀ መሆኑን ተናግረዋል።

የአገር ውሰጥ ባንኮች ይህንን ታሳቢ በማድረግ በሰው ኃይል፣ በአቅም እና በቴክኖሎጂ ጭምር በመጎልበት ለውድድር ዝግጁ እንዲሆኑ ዳይሬክተሩ አስገንዝበዋል።

የተጠናከረና የተደራጀ ባንክ ከመፍጠር አንጻር በራሳቸው ፈቃድ አንዱ ከሌላው ጋር የመዋሃድ አማራጭን መከተልም ወሳኝ መሆኑን መክረዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክን የህግ ማዕቀፉ በሚፈልገው ልክ ጠንካራ፣ ብቁና አስፈላጊውን መስፈርት የማያሟሉ ባንኮች ካጋጠሙ በመዋሃድ መሥራት በአማራጭነት የሚወሰድ ስለመሆኑም ጠቁመዋል።

#ኢዜአ
1.1K views13:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-20 10:40:01
የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ምክር ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ዛሬ ሊወያይ ነው

የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ላይ ዛሬ ሰኞ ሰኔ 13 ሊወያይ ነው። የህብረቱ የውጪ ግንኙነት ኃላፊ ጆሴፕ ቦሬል በሊቀመንበርነት የሚመሩት የዛሬው ስብሰባ፤ በሶማሊያ ወቅታዊ ሁኔታ እና በሱዳን ዲሞክራሲያዊ ሽግግር ላይ የሚወያይ ቢሆንም የኢትዮጵያ ጉዳይም ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶታል።

በሉግዘምበርግ በሚካሄደው በዚሁ የህብረቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያ ጉዳይ በአጀንዳነት የተያዘው፤ በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ጉዳዮች ስር ነው። የአውሮፓ ካውንስል ለዚሁ ስብሰባ ያዘጋጀው እና “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የተመለከተችው ማብራሪያ፤ የኢትዮጵያ ሁኔታ “የተወሰነ መሻሻል” እንደታየበት ቢጠቅስም አሁንም ተግባራዊ ሊደረጉ የሚገባቸው ጉዳዮች እንዳሉ ጠቁሟል።

ዘላቂ የተኩስ አቁም፣ የኤርትራ ወታደሮች መውጣት፣ የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት እና የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች የፈጸሙን ተጠያቂ በማድረግ ረገድ መሳካት የሚኖርባቸው በርካታ ጉዳዮች እንደሚቀሩ በዚሁ ሰነድ ላይ ሰፍሯል። በዛሬው ስብሰባ ላይ የህብረቱ የሰብዓዊ መብቶች ልዩ መልዕክተኛ ኤይሞን ጊልሞር ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የዲፕሎማቲክ ምንጮች ገልጸዋል።

(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
198 views07:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 14:16:27

217 views11:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 09:48:54
#አማራ_ባንክ
የ#72 ቅርንጫፎች ዝርዝር!
*******
የአዲስ አበባ ቅርንጫፎች
1. አዲሱ ገባያ
2. አድዋ ድልድይ
3. አራት ኪሎ
4. አያት አደባባይ
5. በቅሎ ቤት
6. ቦሌ 24
7. ቦሌ ቡልቡላ
8. ቦሌ መድሃኒዓለም
9. ቦሌ ሚካኤል
10. ኮሜርስ
11. ዱባይ ተራ
12. እህል በረንዳ
13. ፈረንሳይ ለጋሲዮን
14. ጎጃም በረንዳ
15. ጎተራ
16. ሃና ማርያም
17. ጀሞ
18. ላፍቶ
19. ለም ሆቴል
20. ልደታ
21. ሳርቤት
22. ሸማ ተራ
23. ጦር ኃይሎች
24. ለገሀር (ዋና መስሪያ ቤት)

የባህርዳር ቅርንጫፎች
1. ባህርዳር
2. ደ/አዝማች በላይ ዘለቀ
3. ደንገል
4. ፋሲሎ
5. ግዮን
6. ሸምብጥ
7. ዘንባባ

የጎንደር ቅርንጫፎች
1.ጎንደር
2.አባ ሳሙኤል
3.አራዳ
4.ማራኪ
5.አፄ ፋሲለደስ

የደሴ ቅርንጫፎች
1.ደሴ
2.ጦሳ

የደብረታቦር ቅርንጫፎች
1.ደብረታቦር
2.ጉና

የደብማርቆስ ቅርንጫፎች
1.ደብረማርቆስ
2.መንቆረር

የሌሎች ከተሞች ቅርንጫፎች
1. ገንዳ ውሃ
2. ሸዋ ሮቢት
3. ሆሳህና
4. ቢሾፍቱ
5. ይርጋለም
6. ዳባት
7. ሀይቅ
8. ዳንግላ
9. ቢቸና
10. ዳንሻ
11. ወሊሶ
12. ደብረ ብርሃን
13. ፍኖተ ሰላም
14. አረርቲ
15. ኮምቦልቻ
16. ሐዋሳ
17. ሎጊያ
18. ከሚሴ
19. መካነሰላም
20. ሞጣ
21. ማክሰኝት
22. ደብረወርቅ
23. መራዊ
24. ደጀን
25. ሰቆጣ
26. ወልድያ
27. ወልቂጤ
28. ድሬዳዋ
29. አዳማ
30. እንጅባራ
****
ሰኔ 11፣ 2014 ዓ.ም
፩ ሚሊዮን ደብተር፣ በ፩ ጀንበር

አማራ ባንክ-ከባንክ ባሻገር!
186 views06:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-17 17:47:16
ኢሰመኮ በጋምቤላ የፀጥታ ኃይሎች ሕይወት ሊያጠፋ ከሚችል ተመጣጣኝ ያልሆነ የኃይል እርምጃ እንዲቆጠቡ አሳሰበ

ኮሚሽኑ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ሰኔ 7፣ 2014 በጋምቤላ ከተማ፣ ጋምቤላ ክልል ከጧት እስከ ምሽት የቀጠለ ግጭት እና የፀጥታ እና የደኅንነት ችግርን ተከትሎ ለአንድ ቀን የከተማዋ የመንግሥት አገልግሎቶች፣ የንግድ እንቅስቃሴዎች እና ሌሎችም አገልግሎቶች ተቋርጠው መዋላቸውን አስታውቋል፡፡

ጥቃቱ በኦሮሞ ነጻነት ግንባር (በተለምዶ ኦነግ ሸኔ) እና በጋምቤላ ነጻነት ግንባር ታጣቂዎች የተከፈተ እንደነበር እና ክስተቱ በቁጥጥር ሥር እንደዋለ የክልሉ መንግሥት ማስታወቁን ያመለከተው ኢሰመኮ፤ በዕለቱ የመንግሥት የፀጥታ አካላት በወሰዱት ርምጃ የከተማዋ ፀጥታ የተረጋጋ እና በአሁኑ ወቅት የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት በከተማው የሚገኝ ቢሆንም እስከ አሁንም ድረስ የተሟላ መረጋጋት አለመስፈኑን፣ የነዋሪዎች የእለት ተዕለት እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ አለመጀመሩን፣ እንዲሁም በተለይም የንግድ አካባቢዎችን ጨምሮ በአንዳንድ ስፍራዎች ዘረፋ እንደተፈጸመ ከነዋሪዎች መስማቱን ጠቁሟል፡፡
178 viewsedited  14:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-17 12:23:33
በጸጥታ ችግሮች ምክንያት ለኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ የታቀደው የጥጥ መጠን ከግማሽ በታች መቀነሱ ተነገረ

ባለፉት አስር ወራት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ከታቀደው 35 ሺህ ቶን ጥጥ ውስጥ ማሳካት የተቻለው ከግማሽ በታች መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ። በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ያሉ “የጸጥታ ችግሮች”፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጥጥን ጨምሮ ሌሎች ግብዓቶችን ባቀደው ልክ ለኢንዱስትሪዎች እንዳያቀርብ ምክንያት እንደሆነበት ገልጿል።

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ይህን የገለጸው የመስሪያ ቤቱን የአስር ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ትላንት ሐሙስ ሰኔ 9፤ 2014 ባቀረበበት ወቅት ነው። አሁን በስራ ላይ ያሉት አምራች ኢንዱስትሪዎች እየገጠማቸው ካለው ችግር መካከል 55 በመቶ የሚሆነው ከግብዓት አቅርቦት ጋር የተያያዘ መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ለፓርላማ አባላት ተናግረዋል።

ይህ የግብዓት አቅርቦት ችግር የተፈጠረው በሀገር ውስጥ የሚመረቱ የግብርና እና የማዕድን ጥሬ ዕቃዎች “በመጠን፣ በአይነት እና በጥራት በቂ” ባለመሆናቸው ምክንያት እንደሆነ ሚኒስትሩ አስረድተዋል። ከውጭ ምንዛሬ ጋር በተያያዘም የግብዓት አቅርቦት ችግሮች እንደሚታዩ አቶ መላኩ ጨምረው ገልጸዋል።

(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
189 views09:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-16 12:04:18
ባንኮች በብሔር በጎጥ እና በሃይማኖት እሳቤ ከመነገድ እንዲወጡ ማሳሰቢያ ተሰጠ

የኢትዮጵያ ባንኮች ዋነኛ ተግባራቸው የሆነውን የፋይናንስ ንግድ ሥራ ረስተው በጎጥ፣ በዘርና በሃይማኖት ማሰብ ከጀመሩ የንግድ ሥራ እየሠሩ እንዳልሆነና ከዚህ ዓይነት ሐሳብ እንዲወጡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) አሳስበዋል፡፡

ዶክተር ይናገር ይህን የተናገሩት የወጋገን ባንክ አክሲዮን ማኅበር 25ኛ ዓመት ክብረ በዓል ላይ ተገኝተው ለሁሉም ባንኮች ብለው ባስተላለፉት መልዕክት ነው፡፡
631 views09:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ