Get Mystery Box with random crypto!

አሳዛኝ ዜና የመውሊዱን ፕሮግራም መሰረዝን ስለማሳወቅ ••••••••••••••••••••• ህገወጡ | ሻሚል - shamil

አሳዛኝ ዜና
የመውሊዱን ፕሮግራም መሰረዝን ስለማሳወቅ
•••••••••••••••••••••
ህገወጡ የአዲስ አበባ መጅሊስ የሚሊኒየሙን መውሊድ አስቁሙልን ብሎ ለአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት በፃፈው ደብዳቤ መሰረት፣ መስከረም 4/2015 ከንቲባ ፅህፈት ቤቱ በደብዳቤ የፈቀደውን የመውሊድ ፕሮግራም ሰላምና ፀጥታ ፅህፈት ቤቱ በቃል ደረጃ የጸጥታ ችግር ስላለ አቁሙ የሚል ትእዛዝ ሰጥቷል። ነጃሺ እስላማዊ ማህበር እስከዚህ ሰአት ድረት በደብዳቤ የተፈቀደ ፕሮግራም በደብዳቤ ከልክላችሁ አሳውቁን ብሎ እየጠየቀ ያለበት ሁኔታ ላይ ቢሆንም ከሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ምላሽ ማግኘት አልተቻለም።

በመሆኑም አገሪቱ ያለችበትን ሁኔታ በማየት እና ማህበረሰባችን ላይ ሊደርስ ከሚችለው ጉዳት አንፃር በጥልቀት በማየት እና በመወያየት የነገው የመስከረም 15/2015 የሚሊኒየም መውሊድ ፕሮግራም መሰረዙ ለማህበረሰባችን ደህንነት የተሻለ መሆኑን ስላመንን በአስገዳጅ ሁኔታ የነገውን የመውሊዱን ፕሮግራም መሰረዛችንን ለመግለፅ ተገደናል።

ስለሆነም በነገው እለት ወደ ሚሊኒየም አዳራሽ ባለመሄድ ከፀጥታ አካላት ጋር በሚደረግ ግጭት በማህበረሰባችን ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ማስቆም ግዴታችን በመሆኑ የአሽረፈል ኸልቅ ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ወዳጆች ነገ ጠዋት ወደ ሚሊኒየም አዳራሽ ባለመሄድ እንድትተባበሩን በእጅጉ እንማፀናለን።

የተሰረዘው የመውሊድ ፕሮግራም የረቢእ አልአወል ወር ሳይወጣ በተለዋጭ ቀን ማድረግ የምንችልበትን መንገድ ሁሉ የምንሞክር ሲሆን ተለዋጭ ቀኑ ካልተሳካ ከማህበረሰባችን በቲኬት ሽያጭ የተሰበሰበው ገንዘብ ተመላሽ የምናደርግ መሆኑን እናሳውቃለን። ቀጣይ ሂደቶችን በትእግስትና፣ በዱዓ እና በተጠናከረ የትግል ወኔ ፀንታችሁ እንድትጠብቁን አጥብቀን እንጠይቃለን።

በረሱል ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ፍቅር እና በዑለማኦቻችን መንገድ ሕያው ነን!

ሷሊህ አስታጥቄ

@shamilunkamil