Get Mystery Box with random crypto!

ልዩ ውድርድር! ወሀቢያዎች ሊመልሱት የማይችሉት ጥያቄ ነው፡፡መውሊድን ለመከልከል የሚያስቀምጧቸው ት | ሻሚል - shamil

ልዩ ውድርድር! ወሀቢያዎች ሊመልሱት የማይችሉት ጥያቄ ነው፡፡መውሊድን ለመከልከል የሚያስቀምጧቸው ትክክል ያልሆኑ ጥያቄዎች አሉ፡፡አንዱ "መውሊድ አክብሩ የሚል አንቀጽ ወይም ሐዲስ ወይም የሶሐባ ንግግር ቃል በቃል አሳየኝ አራቱ መዝሀቦች ያሉትን አምጣ" የሚል ነው፡፡ እናንተ ጠማማ ወሀቢያዎች ሆይ አንድ ሰው እንዲህ ብሎ ቢጠይቃችሁ ወለም ዘለም ሣትሉ ምን ልትመልሱ ይሆን?

#ቁርኣን ውስጥ #ቃል_በቃል "ተውሒድ ለ 3 ይከፈላል"የሚል አለ ወይ?
#መልሱ_የለም!
1)
ነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በየትኛው ሐዲስ ላይ ነው ቃል በቃል "ተውሒድ በ 3 ይከፈላል እነሱም ተውሒድ አል ኡሉሂያ፣አሩቡቢያ፣አልአስማእ ወሲፋት"ያሉት?ኩቱቡ ሲታ ውስጥ ካለ የሐዲስ ቁጥር መጥቀስ እንዳይረሳ?
#መልሱ_አንድም_ሐዲስ_የለም
2)#ሰዪና_አቡበክር ረዲየሏህ ዐንሁ
#ሰዪዱና_ዑመር_ኢብኑል_ኸጧብ ረዲየሏህ ዐንሁ
#ሰዪዱና_ዑስማን ረዲየሏሁ ዐንሁ
#ሰዪዱና_አሊይ_ኢብኑ_አቢጧሊብ ረዲየሏህ ዐንሁ በየትኛው ንግግራቸው ላይ ነው ቃል በቃል ያሉት?የዘጋቢውን ስም ከነሰነዱ ማስቀመጥ እንዳይረሳ?
#መልሱ_አላሉም
3)ሰዪደቱና ዓኢ
ሻ ረዲየሏሁ ዐንሀ በየትኛው ንግግሯ ላይ ነው #ቃል_በቃል ያሉት?ዘጋቢውን ከነሰነዱ ማስቀመጥ እንዳይረሳ?
#መልሱ_አላሉም
4)#አል_ኢማም_አቡሐኒፋ ረዲየሏህ ዐንሁ;
#አል_ኢማም_ማሊክ ረዲየሏህ ዐንሁ;
#አል_ኢማም_አሻፊዒይ ረዲየሏህ ዐንሁ;
#አል_ኢማም_አሕመድ_ኢብኑ_ሐንበል ረዲየሏህ ዐንሁ በየትኛው ንግግራቸው ላይ ነው ቃል በቃል ያሉት? የኪታባቸውን ስም ከነገጹ ማስቀመጥ እንዳይረሳ?
#መልሱ_አላሉም ነው።

በነገራችን ላይ አንድም መልስ ማምጣት አይችሉም፡፡ይህ #ኢብኑ_ተይሚያ እና #ሙሐመድ_ኢብኑ_ዐብዲል_ወሃብ(ላዕናቱሏሂ አል ሙተታሊያቱ ዐለይሂማ) ያመጡትን ተውሒድን ወደ ሶስት የመክፈል እና ተወሱል የሚያደርጉ ሙስሊሞችን የማስከፈሪያ መንገዳቸው መጥፎ ቢድዐ ሆኖ ሳለ ስለ መውሊድ ተነስተው ሊቀባጥሩ ይነሳሉ፡፡ለኛ ጊዜ ሲሆን ነብዩ ብለውታል?ሶሐባ ሰርተውታል?አራቱ መዝሀቦችስ? ይላሉ ለነሱ ሲሆን ግን እነዚህ ጥያቄዎች መነሳት የለባቸውም...ሃሃሃሃ ሲፈልጉ ቢድዐ ሲፈልጉ ሐላል ሲፈልጉ ሐራም እያሉ ጥቅማቸውን በማይጎዳ መልኩ ፍርዶችን ይሰጣሉ።ትላንት እኛን ሲወቅሱባቸው እና በሽርክ ሲፈርጁብን የነበሩ ነገራቶችን ዛሬ ላይ መሪዎቻቸው ሲሰሩት ይስተዋላል።ይህን ልብ ብሎ እንዚህ ሰዎች ልቦናቸውን ተከታይ ጠማሞች እንጂ ወደሐቅ መሪ አለመሆናቸውን የሚገነዘበው ግን ጥቂት ነው።ቡዙው በጭፍን ሳያስተነትን የሚከተል ነው።ስንት ቢድዐዎችን እየሰሩ መውሊድ ሲሆን ይንጨረጨራሉ።

ትንሽ እንጨምርላቸው ምን ይላሉ"መውሊድ ቢቻል ኖሮ ሶሐቦች ባደረጉት በተናገሩት ነበር አንተ ከእነሱ የበለጠ ስለ እስልምና አውቀህ ነው?እነሱ ያላሉትን ያልሰሩትን……መውሊድ የምትለው"

እስኪ ጥያቄውን እናዙረው እና መውሊድ ማክበራችን በእናንተ ቤት ስለ እስልምና ከሶሐቦች ከሰለፎች የበለጠ እኛ እናውቃለን ማለትን ያሲዛል የምትሉ ከሆነ(እውነታው ግን ጭራሽ አያሲዝም ነው።) እናንተ ተውሒድን ስትከፋፍሉ ከሶሐቦች ከሰለፎች የበለጠ ተውሒድን እናቃለን ማለታችሁ ነው ወይ?ብለን እንላቸዋለን።መልስ የላቸውም!

በእርግጥ የጥመታቸው ድርብርብ ሶሐባን እስከማስከፈር እንደደረሰ በኪታቦቻቸው ላይ ተቀምጧል።አሏህ ከጥመት ይጠብቀን!

ኧረ ረቢዑ ሊገባ ነው ሞቅ ሞቅ አድርጉት!

በ ኢብኑ ሀበሺይ

tg.me/shamilunkamil