Get Mystery Box with random crypto!

ወሀቢያዎች መውሊድን በተለያዪ መንገዶች ለመቃረን ጥረዋል ከአመት አመት የተለያዪ እዚህ ግባ የማይባ | ሻሚል - shamil

ወሀቢያዎች መውሊድን በተለያዪ መንገዶች ለመቃረን ጥረዋል ከአመት አመት የተለያዪ እዚህ ግባ የማይባሉ ጥያቄዎችን በማሰራጨት እውቀት የሌለውን ከመውሊድ ከማራቅም ሞክረዋል።

በርግጥ ጥያቄዎቻቸውን ካየን ካለፉት መሪዎቻቸው የያዟቸውና ለነሱም የኢስላም ልሒቃኖች በማያዳግም ሁኔታ መልስ ሰጥተውባቸው ያለፉባቸው ሆነው እናገኛቸዋልን።ከነዚህ ጥያቄዎቻቸው መካከል የሞቱበትን ነው ምታከብሩት ብለው ግግም የሚሉበት ይገኛል።

አጂብ ነው ሰይዳችን ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም በረቢዕ አል አወል በ12ኛው ቀን በመወለዳቸው ደስታችንን ለመግለፅና ቀኑን አስበን ለአሏህ ምስጋናን እያቀረብን የምናሳልፈውን አይ የሞቱበትን ነው ብለው ሲሞግቱ ማግኘት ይደንቃልም ያስገርማልም።እስኪ ከታላላቅ የኢስላም ምሁራን አንዱ የሆኑት የፊቅህ የተፍሲር የቋንቋ የሐዲስ እና የሌሎች ብዙ ፈኖች ምጡቅ እውቀት ባልተቤት የሆኑት አልሓፊዙ አሲዩጢይ ወሀቢያዎች ዛሬ ላይ ለሚያነሱት ጥያቄ ከዛሬ 500 አመት በፊት ገደማ የሰጡትን መልስ እንመልከት……

አል ሓፊዙ አሲውጢይ ሑስኑል መቅሲድ ፊ ዐመሊል መውሊድ የሚል ስያሜን የያዘ ኪታባቸው ላይ በመውሊድ ዙሪያ ተጠይቀው የመለሷቸውን መልሶች ሲጠቅሱ የሞቱበትን ነው ወይስ የተወለዱበትን የምታከብሩት የሚለው ጥያቄ መነሳቱን ጠቅሰው እንዲህ ሲሉ ይናገራሉ:
#"የነብዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም መወለድ ለኛ እጅጉን ታላቅ ፀጋ ነው የእርሳቸው ሞት ደግሞ በኛ ላይ እጅጉን ከባድ ሙሲባ ነው ሸሪዐ ደግሞ ለጸጋዎችና ለረሕመቶች አሏህን እንድናመሰግንና እንድንደሰት ያነሳሳን ሲሆን ሐዘንና ሙሲባ ባጋጠመን ሰዐት ግን ሶብር ማድረግና ቻል ማድረግን አስተምሮናል!"