Get Mystery Box with random crypto!

ጤንነት ሲጣላህ ሲያሳስርህ በሽታው የሚያሽርህ ጌታህ መሆኑን ሳትስተው « ሃኪም ቤት አድርሱኝ፤ መድ | ሻሚል - shamil

ጤንነት ሲጣላህ ሲያሳስርህ በሽታው
የሚያሽርህ ጌታህ መሆኑን ሳትስተው
« ሃኪም ቤት አድርሱኝ፤ መድሃኒት አቅምሱኝ»
የሚባል ቅኔህን እስኪ አንተው ፍታው

አሏህ ነው የሚያድን ስትል እንዳልነበር
  በመሸም በነጋ
ምነው ታየህሳ ክኒን ስትወስድ መርፌም ስትወጋ
 
እውነተኛው ፈዋሽ አሏህ ነው አምናለሁ  
ግንስ ሰበብ ላደርስ ክኒን እወስዳለሁ
ሲል ሰጠኝ ምላሹን

ታዲያ እኔን ሲያመኝ በሽታ ሲያፍነኝ
ከልቤ እያመንኩኝ እርሱ እንደሚያድነኝ
  የመሻሬ ሰበብ እንዲሆኑኝ ብዬ
  በክኒኑ ፈንታ ነቢዬን መጥራቴ
  አሽሮኝ ተገኝቷል ሆኖኝ መድኀኒቴ
 
በኡስታዝ ሰዒድ አህመድ

:¨·.·¨: ❀
 `·. ሻሚል-shamil
https://t.me/shamilunkamil