Get Mystery Box with random crypto!

🤓 ሰው ሲኖር-Sew Sinor‍

የቴሌግራም ቻናል አርማ sewsinor — 🤓 ሰው ሲኖር-Sew Sinor‍
የቴሌግራም ቻናል አርማ sewsinor — 🤓 ሰው ሲኖር-Sew Sinor‍
የሰርጥ አድራሻ: @sewsinor
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.23K
የሰርጥ መግለጫ

💟 እንኳን በደህና መጡ። 🙏 ቸር አይለፋችሁ ክፉ አያግኛችሁ
😊😍 ገፁን ከተቀላቀሉበት ሰከንድ አንስቶ እጅጉን ጠቃሚ ነገሮችን ያገኙበታል።
በተጨማሪ📚 በpdf ማግኘት የሚፈልጉት ማንኛውም መፅሐፍ ካለ 👉 @Sewsinor1_bot ይጠቀሙ።
ማስታወቂያ ለማሰራት፣ማንኛውም ጥያቄ ፣ ሀሳብ ፣ አስተያየት ለመስጠት👇 Inbox 👇
👉 @Sewsinorbot
👉 @CheramlakT

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-12-11 04:22:14 https://www.tiktok.com/@cheramlakt/video/7175656496930245893?_r=1&u_code=d1l11g5i4c4km7&preview_pb=0&language=en&_d=e24j5kk57fa3ij&share_item_id=7175656496930245893&source=h5_m×tamp=1670700156&user_id=6594440834879864837&sec_user_id=MS4wLjABAAAAmdkyx5WWFnUpKPNafJCTRNS9H8sr9PdesxKu9fkrYH27AP1Z5Zm67FbWZHg1YTYE&utm_source=copy&utm_campaign=client_share&utm_medium=android&share_iid=7173768189230761733&share_link_id=af6b61f9-ce70-48c9-876d-0daaef7d1ed3&share_app_id=1233&ugbiz_name=Main&ug_btm=b8727%2Cb2878
13 viewsCheramlak Ŧ, 01:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-10 20:14:58 ​​ርዕስ #ያልነገርኩሽ_ነገር
#ሰውሲኖር
ክፍል-፪


ሚናን ለመጀመሪያ ጊዜ ያያት እሱ በሚያስተምርበት ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለመምህርነት ቅጥር ለቃለ መጠይቅ ቀርባ ነው፡፡ የቅጥር ኮሚቴ ውስጥ ነበረበት፤ ቃለ መጠይቅ ከሚያደርጉ አራት ሰዎች አንዱ እሱ ነበር፡፡ ጥያቄዎቹ ተደጋጋሚ ስለነበሩ እና ተወዳዳሪዎቹም ብዙ ስለነበሩ ሰልችቶት፣ አቋርጦ ሲጋራ ሊያጨስ ወጣ፤ ሲመለስ ሚና እየተጠየቀች ደረሰ፡፡ ስታየው ደነገጠች፤ ሲያያት ደነገጠ፡፡ እርጋታዋ ገርሞታል፤ በጣም ተረጋግታ ነው የምትመልሰው፡፡
ፍርሃትም የለባትም፤ ለመመሰጥም አትሞክርም፤ ትጠየቃለች፤ በእርጋታ ትመልሳለች፡፡
“ሚና ጥያቄዎቻችን አልቀዋል፤ እናመሰግናለን፤ ውጤቱን ደውለን እናሳውቅሻለን፡፡” አለ የኮሚቴው ሰብሳቢ፡፡
“ቆይ፤ ቆይ እኔ አንድ ጥያቄ አለኝ፤ ለሚና፡፡” አለ ሀሌሉያ፡፡
“ጥሩ እንግዲህ፡፡” አለ የቅጥር የኮሚቴው ሰብሳቢ፤በቅሬታ፡፡
“ሚና?”
“እህ?”
“የወንድ ተማሪሽ የፍቅር ጥያቄ ቢያቀርብልሽ ምን ታደርጊያለሽ?”
ያልተጠበቀ ጥያቄ ነበር፡፡ መገረም እና ፈገግታ ሰፈነ፡፡ሁሉም የሚናን መልስ እየጠበቁ ነው፡፡ ከረዥም ፀጥታ በኋላ፤ “የወንድ ተማሪዬ የፍቅር ጥያቄ ቢያቀርብልኝ ምን አደርጋለሁ ነው አይደል ጥያቄው?”
“አዎ፡፡” አሉ አራቱም አንድ ላይ፡፡
“በመጀመሪያ ጆሮውን እቆነጥጠዋለሁ፡፡” ሁሉም ሳቁ፡፡
“እሺ ከዛስ?” አላት ሀሌሉያ ሲስቅ ያነባውን እንባ ከአይኑ እየጠረገ፡፡
“ከዚያ ባልቆነጠጥኩት ጆሮው በኩል አርፎ እንዲማር እነግረዋለሁ፡፡” ሳቅ፡፡
አሁን ሚና የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የህግ የትምህርት ክፍልን ተቀላቅላ የመምህር ሀሌሉያ የስራ ባልደረባ ሆናለች፡፡ ሚና ስትቀጠር ሀሌሉያ ካቀረበላት አስቂኝ ጥያቄ ወዲህ አውርተው አያውቁም፡፡ ያኔ መጠየቅ የፈለገው ጥያቄ “ተማሪሽ የፍቅር ጥያቄ ቢያቀርብልሽ መልስሽ ምን ይሆናል?” ሳይሆን “የስራ ባልደረባሽ የፍቅር ጥያቄ…” እንደሱም አይደለም፡፡ መጠየቅ የፈለገው “እኔ፣ ሀሌሉያ የፍቅር ጥያቄ ባቀርብልሽ መልስሽ ምን ይሆናል?” ብሎ ነው፡፡ ሁለቱም ተግባብተዋል፤ ሁለቱም ተዋደዋል፡፡
እሷ “ሀሌሉያ የፍቅር ጥያቄ ቢያቀርብልኝ፤ በሀሴት ይህን ጥያቄ ያቀረበውን አፉን ድብን አድርጌ እስመዋለሁ፡፡” ብትለው ነበር ፍላጐቷ፤ ግን - “ጆሮውን እቆነጥጠዋለሁ፡፡” ብላ አሾፈችበት፡፡ የሚገርመው ይህን መልሷን ሲሰማ ሀሌሉያ እየሳቀ በግራ እጁ፤ ቀኝ ጆሮውን ሲያሽ ነበር፡፡ ይህ ፍቅር ይሉት ነገር ሁሌ ይገርማል፡፡ ሁለቱም ልጆች በዚያ ቅጽበት ተዋደዋል፤ በጣም የሚገርመው ደግሞ እንደተዋደዱ ማወቃቸው ነው፡፡ ብዙ ጊዜ በመጀመሪያ እይታ የሚከሰት ፍቅር ጣዕሙም፤ ጥልቀቱም፤ እርቀቱም፣ አንደኛ ነው፡፡
ከመላመድ የሚመጣ ፍቅር፣ ፍቅር አይደለም፤ ኑሮ ነው፡፡ ሚና ሥራ ከጀመረችበት ቀን አንስታ ተስፋ ነበራት፡፡ ይህ ዋዘኛ የስራ ባልደረባዋ አንድ ቀን፣ በቅርብ ቀን ጥያቄውን እንደሚያቀርብላት እርግጠኛ ነበረች፡፡
እንዲያውም መልሷን አዘጋጅታለች፤ ምን እንደምትል ብቻ ሳይሆን እንዴት እንደምትለውም ተለማምዳለች፤ ግን...
ይቀጥላል


ሌሎችም እንዲያነቡት በቅንነት ሼር አድርጉት
@Sewsinor @Sewsinor
91 viewsቸርአምላክ ታምሩ, 17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-10 18:15:30 ∞∞ አልሞተችም ∞∞
    
``
እንደ አምና ካቻምና
ለፌሽታ ለተድላ ለሳቅ ባትመችም
በምድሯ ሰቀቀን
እንግልት ለቅሶ ሙሾ ቢሰ'ለችም
    ተስፋ አትቁረጡባት
ተኝታ ይሆን እንጂ ሀገሬ አልሞተችም !

kiyorna

@Sewsinor
@Sewsinor
@Sewsinor
120 viewsCheramlak Ŧ, 15:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-10 18:13:07 "አልሰማም ሙት ወሬ
አልሰማም ግርግር
እንኳን ሰው ይቅርና
ይጋጫል አንድ እግር"
ብለን ንቀናቸው ሴረኞችን ሁሉ
ሊያጠፉን ተነሱ ሰው እየገደሉ

መጀገን መስሏቸው የሰው ነብስን መብላት
ልታገስ ባለ ክር ቃልኪዳኔን በሏት

ሁለት አይነት ኑሮ በምትኖረው አለም
የጊዜ ነው እንጂ የሰው ጀግና የለም።

#ጊዜ_ርዕስ_ነው

ዮኒ ኣታን

@Sewsinor
@Sewsinor
@Sewsinor
126 viewsCheramlak Ŧ, 15:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-09 23:14:56 ​​ርዕስ #ያልነገርኩሽ_ነገር
#ሰውሲኖር
ክፍል-፩


ሁለቱም ፍቅር ይይዛቸዋል ተብለው የሚጠረጠሩ አይነት አይደሉም፡፡ ‘እንዲህ የሚባል ነገር አለ እንዴ?’ ሊል ይችላል አንዳንድ ሰው፡፡ አዎ እንዲህ የሚባል ነገር አለ፡፡ ለምሳሌ ፡- “እከሌ እኮ ፍቅር ይዞታል፡፡”
ሲባል” “ተዉት እባካችሁ እሱ ልማዱ ነው፡፡” የሚል መልስ ይሰማል፡፡ አንዳንዴም፡- “እከሊት እኮ ፍቅር ያዛት፡፡” ሲባል “እሷን?! እንዴት ተደርጐ?! እሷ እኮ ጀግና ቢጠበስ አይሸታትም!” የሚባልላትም አለች፡፡
ሁለቱም “እንዴት ተደርጐ” የሚባልላቸው ናቸው፤ ግን ሁለቱም እንዴት ተደርጐዎች ፍቅር ያዛቸው፡፡
ሚና እና ሀሌሉያ ተፋቀሩ፡፡
ይህ የሚና እና የሀሌሉያ እውነተኛ የፍቅር ታሪክ ነው፡፡ ሚና ፀይም ናት፡፡ ፊቷ ክብ ነው፡፡ ፀጉሯ አጭር ሆኖ ከርዳዳ ነው፤ በደንብ የማይታይ የተፈጥሮ ስስ ከርል አለው፡፡ የአይኖቿ ቅንድቦች ያምራሉ፤ ከአንደበቷ ይልቅ ብዙ ነገር የምትናገረው በአይኖቿ ነው፤ በአይኖቿ
ማድነቅ - መናቅ፣ መቆጣት - ማባበል፣ መጥራት - መግፋት፣ ማቀፍ - መገፍተር፣ ማመስገን - ማንኳሰስ… በአይኖቿ፤ ተራ ስሜቶች አታስተናግድም፡፡
አጭር ናት፤ ግን አያስታውቅባትም፤ የትከሻዋ ቀጥ ማለት፤ የአካሄዷ ስክነት እና ፍሰት ረዥም ያስመስላታል፡፡
የቆዳዋ ቀለም ይገርማል፤ ስም የለውም፤ አንዱ አንዴ “ቀለምሽ…” ብሎ ጀምሮ…ምን እንደሚል ግራ ገብቶት “ቆቅማ ነው፡፡” ብሏታል፡፡ ከዚያ በኋላ “ቆቅማ ቀለም፡፡” ይሏታል፡፡
ሚና ነፃ፣ ግለኛ እና ምክንያታዊ ሰው ናት፤ ያለ ምክንያት የምታደርገው አንድም ነገር የለም፤ ሁሉ ነገሯ በምክንያት እና በእቅድ የተቀነበበ ስለሆነ ሰዎች ይፈሯታል፡፡ ብዙ ጊዜ ሰዎች የባህሪ ድክመት ያለባቸውን ሰዎች ባያደንቋቸውም ይወዷቸዋል፤ እንደ ሚና አይነቶቹን ፍፁማውያኖች ግን ፈጽሞ አይወዷቸውም፤ ወይ ያከብሯቸዋል ወይ ይፈሯቸዋል፤ ጠና ሲል ይጠሏቸዋል፡፡ ሚናን ብዙዎች ያከብሯታል፤ የሚፈሯትም አሉ፤ የምር የሚጠሏትም ትንሽ አይባሉም፡፡ ሲወቅሷት፤ ሊያሟት ሲጀምሩ፡- “ሠው፤ ሠው አትሸትም…” ብለው ይጀምራሉ፡፡…
ሀሌሉያ ሰው፣ ሰው ይሸታል፡፡ አልኮል ይወዳል፤
የሚጠጣው ከዊንስተን ቸርችል በላይ ነው፡፡ በሲጋራ ይመሰጣል፤ ከሲግመንድ ፍሮይድ በላይ ነው የሚያጨሰው፤ ለማያጨሱ ጓደኞቹ በሲጋራ ጦስ በመጣ ካንሰር የሞተውን የፍሮይድን አባባል ይነግራቸዋል ፡- “ሠው ሳያጨስ እንዴት ላለማጨስ ይወስናል?” ሴቶች ይወዳል፤ ሴቶችም ይወዱታል፤ ሲዘሙት እንደ ንጉስ ሠለሞን ነው፤ አምስት መቶ ሲደመር እቁባቶች አሉት፡፡ አይፈራም፤ እንደ ሄምንግዌይ ወንድ ተኩል ነው፡፡ ሙዚቃ ይወዳል፤ ሲደንስ አለም ሁሉ አብሮት ይደንሳል፡፡
ሚናን ለመጀመሪያ ጊዜ ያያት ...
ይቀጥላል


በቅንነት ሼር አድርጉት
@Sewsinor @Sewsinor
186 viewsቸርአምላክ ታምሩ, 20:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-09 21:04:35 ​​የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በምስራቅ ወለጋ ፣ በአርባ ምንጭ እና በትግራይ ዓዲ ዳዕሮ የተፈፀመውን ግድያ አወገዘች

ብፁዕ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በዛሬዉ እለት መግለጫ ሰጥተዋል።ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው በሀገራችን ኢትዮጵያ ጦርነቱ በመቆሙ ሰላሙን ለፍጻሜ እንዲደርስ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መልእክት አስተላልፋ እንደነበር አስታውሰዋል።

ነገር ግን ከዛ በኋላ በአርባ ምንጭ አባያ እስር ቤት የደረሰው ሞት ፣ በትግራይ ሽሬ አዲ ዳዕሮ ከተማ የደረሰው እልቂት እንዲሁም በምሥራቅ ወለጋ እየተሰማ ያለው የንጹሐን ግድያ የብዙዎችን ልብ የሚሰብር ቤተ ክርስቲያንንም የሚያሳዝን ነው ብለዋል ሲል የተዋህዶ ሚዲያ ማዕከል ዘግቧል።

አክለውም ለሀገራችን መኖር የሚያስፈልገው ፍቅርና ሰላም መሆኑን ገልጸው ይህንን የሚያደርጉ አካላት  ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እንዲሁም መንግሥትም ሕግ የማስከበር ተግባሩን እንዲያከናውን ቅዱስነታቸው አሳስበዋል።በመጨረሻም በ5ተኛው የኤርትራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ በብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ቀዳማይ ዕረፍት የተሰማቸዉን ሐዘን ገልጸዋል። ለመላው ሕዝበ ክርስቲያንም መጽናናትን እመኛለሁ ብለዋል።

@Sewsinor @CheramlakT
226 viewsቸርአምላክ ታምሩ, 18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-09 06:50:23 https://vm.tiktok.com/ZMFbsAxaQ/
257 viewsCheramlak Ŧ, 03:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ