Get Mystery Box with random crypto!

ሰሌዳ | Seleda

የሰርጥ አድራሻ: @seledadotio
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 50.39K
የሰርጥ መግለጫ

የመረጃዎች ቁንጮ የሆነውን ሰሌዳ ለሚወዱት ጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያካፍሉ። አንድ ላይ፣ ዘምነን እንቆይ!
@seleda_support ለማንኛውም አይነት ጥያቄ

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-05-18 21:05:26
ልጁን ‘የካንሰር በሽተኛ ነው’ በማለት ሲለምንበት የተገኘ ወላጅና ግብረ-አበሩ ተያዙ
********
ጤናማ ልጁን ‘የካንሰር በሽተኛ ነው’ በማለት ሲለምንበት የተገኘ ወላጅን እና ግብረ-አበሩን ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በወንጀሉ የተጠረጠረው ግለሰብ ልጁን የካንስር በሽተኛ በመሆኑ ለማሳከም ከአዋሽ 7 ወደ አዲስ አበባ መምጣቱንና ልጁን ለማሳከም፣ ለምግብ እንዲሁም ማደሪያ መቸገሩን በመግለፅ ከአንድ ግብረ-አበሩ ጋር በመሆን በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ቦታዎች ሲለምን መቆየቱን ገልጿል።

የህፃኑ አባት አቶ ጃዋር አብዱላሂ እና አህመድ ከሊፋ የተባለው ግብረ-አበሩ ግንቦት 10 ቀን 2016 ዓ.ም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ሰነዓ ሆቴል አካባቢ የማታለል ተግባራቸውን ሲፈፅሙ ፖሊስ በጥርጣሬ ይዟቸዋል።

በዚህም የሀኪም ማስረጃ ሲጠየቁ ምንም አይነት ማስረጃ ማቅረብ ባለመቻላቸው ወደ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደዋል።

ህፃኑ በፖሊስ ጣቢያ ሲጠየቅ ጤነኛ መሆኑን እና ምንም አይነት ቁስል አንገቱ ላይ እንደሌለበት ማረጋገጡን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የደንበል አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ አስታውቋል፡፡

የህፃኑ አባትና ግብረ አበሩ በህጻኑ አንገት ላይ ፕላስተር ለጥፈው ሲለምኑ እንደነበር ለፖሊስ በሰጡት ቃል አረጋግጠዋል ሲል ፖሊስ ገልጿል።

ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር በዋሉበት ወቅት በልመና ያገኙት ከ1 ሺ 240 ብር በላይ በኤግዚቢትነት ይዞ ፖሊስ ምርመራውን መቀጠሉን አመልክቷል።

ፋና
5.6K views18:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-18 20:13:37
አየር መንገዱ ከሰኔ 1 ጀምሮ ወደ አክሱም ዳግም በረራ ይጀምራል ተባለ

ከመጪው ሰኔ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ትግራይ ክልል አክሱም ከተማ ዳግም በረራ እንደሚጀምር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ገለጸ።

የአየር መንገዱ የንግድ ዘርፍ ዋና ኃላፊ አቶ ለማ ያዴቻ፤ አየር መንገዱ ወደ አክሱም ዳግም በረራ ለመጀመር የሚያስችሉትን ቅድመ ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቷል ብለዋል።

በመሆኑም ከመጪው ሰኔ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ታሪካዊ የቱሪዝም መዳረሻ ወደሆነችው አክሱም ከተማ ዳግም በረራ እንደሚጀመር ገልጸዋል።

በረራው መጀመሩ ዓለም አቀፍ ቱሪስቶችና የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች ወደ ሥፍራው የሚያደርጉትን ጉዞ ለማሳለጥ እንደሚያስችልም ተናግረዋል።

በረራው በሣምንት ሰባት ጊዜ የሚደረግ መሆኑንም መጠቆማቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

አየር መንገዱ የደንበኞችን ፍላጎት መሰረት በማድረግ በረራውን በቀን ወደ 3 እንደሚያሳድግም ገልጸዋል።

የበረራው መጀመር የትራንስፖርት እንቅስቃሴውን ለማሳለጥና ማኅበራዊ መስተጋብርን ለማጠናከር ያስችላል ብለዋል።
5.6K views17:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-18 19:31:19
ኖቫ የጂም እቃዎች መሸጫ
https://t.me/fitnesshoppp
5.4K views16:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-18 19:22:46
Semuonlineshopping19

- የሴቶች/የወንዶች አልባሳት እና ጫሞች
- ሂውማን ሄር
- የስፖርት አልባሳት (ስልኮች, ላፕቶፖች) እንዲሁም ማንኛውም አይነት ኤሌክትሮኒክስ  እቃዎች በትእዛዝ እናስመጣለን ። እቃዎችን ለመምረጥ የ ቴሌግራም ገፃችንን Join ያድርጉ።

https://t.me/semuonlineshopping19

0951107944

ባሉበት እናደርሳለን
5.2K views16:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-18 19:19:48
በአሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ የሚመራዉ ባየር ሊቨርኩሰን አንድም ጨዋታ ሳይሸነፍ ወርቃማ ታሪክ ፃፈ

የጀርመን ቡንደስሊጋ ዋንጫን ቀደም ብሎ ማሸነፉን ያረጋገጠው ባየር ሊቨርኩሰን ከኦግስበርግ ጋር ያደረገውን የመጨረሻ ሳምንት ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የባየር ሊቨርኩሰንን የማሸነፊያ ግቦች ቪክቶር ቦኒፌስ እና ሮበርት አንድሪክ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

በአሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ የሚመራው ባየር ሊቨርኩሰን በዘንድሮው የውድድር አመት ምንም ጨዋታ ሳይሸነፍ ዋንጫውን በማሳካት አዲስ ወርቃማ ታሪክ መፃፍ ችለዋል።

ባየር ሊቨርኩሰን በዚህ አመት በቡንደስሊጋው ሰላሳ አራት ጨዋታዎች ሲያደርግ ሀያ ስምንቱን አሸንፎ በስድስቱ አቻ ተለያይቷል ።
5.2K viewsedited  16:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-18 15:35:06
በተቋማት ያለመናበብ ችግር ምክንያት ከባድ ተሸከርካሪዎችንና ማሽነሪዎችን ወደ ሃገር ውስጥ ማስገባት ተከልክለናል አስመጭዎች

የካቢኔ ውሳኔ እያስፈጸምኩ ነው ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር

መንግስት ምንም አይነት መመሪያ ባላወጣበት ከባድ ተሸከርካሪዎችንና ማሽነሪዎችን ወደ ሃገር ውስጥ ማስገባት አትችሉም ተብለናል ሲሉ የመኪና አስመጭዎች ቅሬታቸውን ገልጸዋል፡፡

በተቋማት ያለመናበብ ችግር ምክንያት አገሪቱን ለከፋ ጉዳት እየዳረጉ እንደሚገኙ የሚናገሩት ቅሬታ አቅራቢዎች ሁኔታው ለሙስና እና ብልሹ አሰራር በር የሚከፍት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ጉዳዩን ለሚመለከታቸው አካላት ቢያሳውቅም ምንም አይነት ምላሽ እንዳላገኙ ተናግረዋል፡፡

የትራንሰፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በኩል የመኪና ማስገቢያ ፈቃድ አንሰጥም እንዳሏቸውም ጨምረው ገልጸዋል፡፡

መናኸሪያ ሬዲዮም የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ በርኦ ሁሴን ያነጋገረ ሲሆን ሁለተኛ መቶ ቀናት ግምግማ በተደረገበት ጊዜ ካቢኔው የኤሌክትሪክ መኪና ውጭ ሌሎች መኪናዎች ወደ ሃገር ውስጥ እንዳይገቡ ውሳኔ ማሳለፉን አስታውሰው ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ የካቢኔውን ውሳኔ እያስፈጸመ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

የኤሌክትሪክ መኪናን በተመለከተ የስትራቴጃችን አንዱ አካል በመሆኑ ይሄንን እየተገበርን እንገኛለን ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ የገንዘብ ሚኒስቴር መመሪያን በተመለከተ ቅሬታ አቅራቢዎቹ እዛ ሂደው መጠየቅ ይችላሉ ሲሉ ለመናኸሪያ ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

አሁንም ካቢኔው የተለየ አቅጣጫ ካላስቀመጠ በስተቀር ይህንኑ ውሳኔ ከማስፈጸም ወደኋላ እንደማይሉ አረጋግጠዋል፡፡

መናኸሪያ ሬዲዮ
5.8K views12:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-18 15:25:27
ፊል ፎደን እና  ኮል ፓልመር የአመቱ ምርጥ ተጨዋቾቸ ተባሉ ።

በነገው ዕለት ፍፃሜውን የሚያገኘው የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የ2023/24 የውድድር ዘመን የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ይፋ ተደርጓል።

በዚህም መሰረት እንግሊዛዊው የማንችስተር ሲቲ የፊት መስመር ተጨዋች ፊል ፎደን የፕርሚየር ሊግ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች በመሆን በአብላጫ ድምፅ ተመርጧል።

ፊል ፎደን በዘንድሮው የውድድር አመት በሊጉ ለማንችስተር ሲቱ አስራ ሰባት ግቦችን ሲያስቆጥር ስምንት ለግብ የሆኑ ኳሶችንም አመቻችቶ ያቀበለ ሲሆን ሁለት ሀትሪክም ሰርቷል።

ኮል ፓልመር  የዘንድሮው የፕሪሚየር ሊግ 2023/24 የውድድር ዘመን ምርጥ ወጣት ተጫዋች በመባል ተመርጧል ።
5.7K views12:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-07 20:01:21
ቶኪዮ አዲስ ባበለፀገችው መተግበሪያ የተነሳ ቱሪስቶች እየጎረፉላት ነው ተባለ

ቶኪዮ በሚገኝ ባቡር ጣቢያ ውስጥ የተለያዩ ሀገራት ቋንቋዎችን ከሚናገሩ ቱሪስቶች ጋር ገጽለገጽ በመተያየት የሚተርጉም የስክሪን አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተገልጿል፡፡

በሴቡ ሺንጁኩ ባቡር ጣቢያ ፖሊግሎት የሚል መጠሪያ የተሰጠውና የገጽለገጽ መተያያ የመተርጎሚያ ስክሪን  1ሜትር በ40 ሳንቲሜትር ቁመት ያለው ሲሆን፤ በባቡር ጣቢያው ማዕከላዊ ስፍራ ላይ በምትገኝ አስተናጋጅ ድጋፍ ሰጪነት የውጭ ዜጎች የሚናገሩትን ቋንቋ ወደ ጃፓንኛ፤ የጃፓንኛውን ደግሞ እነሱ ወደሚናገሩት ቋንቋ በድምጽ እያሰማ በጽሁፍ ደግሞ ስክሪን ላይ ተርጉሞ እያሳየ በቀላሉ እንዲግባቡ አስችሏል፡፡

ጃፓን፤ በ12 የተለያዩ ቋንቋዎች የበለፀገውን የመተርጎሚያ ቴክኖሎጂ በባቡር ጣቢያው ውስጥ በመጠቀሟ በተግባቦት ችግር ምክንያት የሚቀሩ ቱሪስቶች እንዳይኖሩ ከማድረጉም በላይ ለጉብኝት የሚሄዱ የውጭ ዜጎችን ቁጥር እንደሚሳድገው የNHK ዘገባ አመልክቷል፡፡
793 views17:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-07 19:16:37
ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ለመሳተፍ ገና ካሁኑ ፍላጎታቸውን እያሳዩ ነው ተባለ

የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሃብቶች በ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት በሚጀመረው የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ውስጥ ለመሳተፍ ከወዲሁ ፍላጎታቸውን እያሳዩ መሆኑን የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን አስታውቋል።

የካፒታል ገበያ ባለሃብቶች፣ ድርጅቶች፣ ግለሰቦች ወይም መንግስት ለሚያስፈልጋቸው ኢንቨስትመንት ካፒታል በጥሬ ገንዘብ አልያም በአይነት የሚያሰባስቡበትና የሚያገኙበት ገበያ ነው፡፡

በተለይም በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ባሉበት ሆነው በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች እንዲሳተፉ ሰፊ እድል ይፈጥራል የተባለ ሲሆን ይህም ካፒታል በማሰባሰብ፣ የገንዘብ ሥርዓቱን በአዲዲስ ፈጠራዎች በመደገፍ እና ኢንቨስትመንትን በማስፋፋት የአገሪቱን ኢኮኖሚ ልማት ያግዛል ተብሏል፡፡

በተጨማሪም በቀላሉ ቢዝነስ ለመጀመር፣ ለማስፋፋት እና የሚያስፈልጉ ጥሬ እቃዎችን በአፋጣኝ ለማግኘት እንዲሁም የውጭ ኢንቨስተሮችን በቀላሉ ለመሳብና ከትናንሽ ቢዝነሶች እስከ ትላልቅ ኮርፖሬሽኖች ለመመስረት እድል ይፈጥራል፡፡

ምንጭ - ኢዜአ
1.9K views16:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-07 18:50:21
ገና ሊለቀቅ ጥቂት ቀናት የቀረውን "ባርቢ" የተሰኘውን ፊልም ቬትናም በሃገሪቷ እንዳይታይ ከልክላለች።

ለምን ሲባል:-

ይህ ምናባዊ-አስቂኝ ፊልም ሊለቀቅ የታሰበው ሐምሌ 14, 2015 ነበር ነገር ግን ከ ፊልም ማስታወቅያው ላይ ባለው አንድ ትእይንት ሊከለከል ችሏል።

ታዲያ ይህ ትእይንት የሚያሳየው የ ቻይናን ካርታ ነበር እናም በካርታው ላይ ዘጠኝ ሰረዞች በቻይና ባህር ላይ አርፈው ይታያሉ እነዚህም ዘጠኝ ሰረዞች የሚያመለክቱት 3 ሚሊዮን ካሬ ኪሎሜትር የሚሸፍን ሃሌታው "ሀ" ቅርጽ ያለው የባህር ክፍል ሲሆን ይህ አካባቢ በ ነዳጅ እና በ ተፈጥሮ ጋዝ የበለጸገ ነው፤ ሆኖም ይህንኑ አከባቢ ቬትናም፣ ፊሊፒንስ፣ ብሩኔይ፣ ማሌዥያ እና ታይዋን ይገባኛል ጥያቄ ለረጅም ጊዜ ሲያቀቡ የቆዩ ቢሆንም ጉልቤዋ ቻይና ግን ጥያቄያቸውን ችላ በማለት በተለያዩ ታላላቅ ሚዲያዎች ላይ እነዚህ መሰመሮች እንዲታዩ እና የቻይና ባለቤትነቱን እንዲለመድ ግፊት እያደረገች ትገኛለች።

በዚህ ትእይንት ደስተኛ ያልሆነው የ ቬትናም ባህልና ቱሪዝም ሚንስቴር ይህ ፊልም በሃገሪቷ ውስጥ ጨርሶ እንዳይታይ አግዷል።
2.3K views15:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ