Get Mystery Box with random crypto!

አየር መንገዱ ከሰኔ 1 ጀምሮ ወደ አክሱም ዳግም በረራ ይጀምራል ተባለ ከመጪው ሰኔ 1 ቀን 20 | ሰሌዳ | Seleda

አየር መንገዱ ከሰኔ 1 ጀምሮ ወደ አክሱም ዳግም በረራ ይጀምራል ተባለ

ከመጪው ሰኔ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ትግራይ ክልል አክሱም ከተማ ዳግም በረራ እንደሚጀምር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ገለጸ።

የአየር መንገዱ የንግድ ዘርፍ ዋና ኃላፊ አቶ ለማ ያዴቻ፤ አየር መንገዱ ወደ አክሱም ዳግም በረራ ለመጀመር የሚያስችሉትን ቅድመ ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቷል ብለዋል።

በመሆኑም ከመጪው ሰኔ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ታሪካዊ የቱሪዝም መዳረሻ ወደሆነችው አክሱም ከተማ ዳግም በረራ እንደሚጀመር ገልጸዋል።

በረራው መጀመሩ ዓለም አቀፍ ቱሪስቶችና የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች ወደ ሥፍራው የሚያደርጉትን ጉዞ ለማሳለጥ እንደሚያስችልም ተናግረዋል።

በረራው በሣምንት ሰባት ጊዜ የሚደረግ መሆኑንም መጠቆማቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

አየር መንገዱ የደንበኞችን ፍላጎት መሰረት በማድረግ በረራውን በቀን ወደ 3 እንደሚያሳድግም ገልጸዋል።

የበረራው መጀመር የትራንስፖርት እንቅስቃሴውን ለማሳለጥና ማኅበራዊ መስተጋብርን ለማጠናከር ያስችላል ብለዋል።