Get Mystery Box with random crypto!

ሰሜን ምድር ዔጁ!!በኑር!!! የጀግንነት ሞገድ መፍለቂያ የወንዶች፡ የቆራጥ እናት | Sami Habib

ሰሜን ምድር ዔጁ!!በኑር!!!

የጀግንነት ሞገድ መፍለቂያ የወንዶች፡
የቆራጥ እናት ልጅ የፍቅር ዘመዶች፡
ይሔ የኤጁ ልጅ አንድ ነው አቋሙ፡
ሀገሩን አይሸጥም ቢፈስ እንኳን ደሙ፡
ይናገር ይመስክር የራያ ተራራ፡
በጀግና ልጆቹ ምን ገድል እንደሰራ፡
ይጠዬቅ ወልድያ ዶሮ ግብር ሐራ፡
ስንቴ እንዳከሸፈ የጠላትን ሴራ፡
ይጠየቅ አረባል ይናገር ኩልባይኔ፡
ምን እንደፈፀመ ያ ጀግና ወገኔ፡
ወራሪውን ጠላት ሞቱን እንዳበጁት፡
ያንን ባንዳ ጁንታ ለጉድ እንደ ፈጁት፡
ጠላትን ያሮጠው በግር ያለጫማ፡
ያ ሰላም ወዳድ ህዝብ ያ የፍቅር አርማ፡
ይመስክር ይናገር ትጠየቅ ሰዶማ፡

የማይከፈተው የፀናው ውብ ሳንቃ፡
በእጁ የጨበጠው የጠላትን ላንቃ፡
ያ ገበሬ ተኳሽ መገን ዱሬ ሮቃ፡
ወራሪውን ጠላት የሚለው በል በቃ፡
ሐራ እና ወርጌሳ ሀብሩና ሲሪንቃ፡
ጠላትን መክቶ ፆሙን የሚያሳድር
የጀግኖች ሀገር ነው ይሔ ኤጁ ምድር፡
የሙስሊሞች ውህደት የገበሬ ተኳሽ፡
ጠላትን የሚፈጂ እንደ እሳት ትርኳሽ፡
አሏሁ አክብር ብሎ ወስኖ ሲነሳ፡
ይደለቃል ልቡ እንደ ደልግ አንበሳ፡
ለሀገሩ ሲባል መሞት የማይሳሳ፡
አኩሪ ታሪክ ሰርቷል ሁሌም የሚወሳ፡
ሽርጡን ሸብ አርጎ ሲስብ ያንን ቃታ፡
በጨለማም ቢሆን አልሞ እሚመታ፡
ይህ ነው የኤጁ ልጂ ገበሬው ወታደር፡
የወገን አለኝታው ያገር አንባሳደር፡
አምሳያ የለውም ምን ወንድ ቢሰደር፡

ያምርበታል ኤጁ ሲለብስ ጀበርና፡
ክላሹን ሲሸከም ሆኖ በፅሞና፡
ዝናሩን ሲታጠቅ አጊጦ በጥምጣም፡
የሰሜኑ ልዑል ያ ባለ ሽርጣም፡
በህይወት እስካለሁ ከውስጤ ባትወጣም፡
ይድረስህ መልዕክቴ ወድሀለሁ በጣም፡
ወራሪውን ቡድን አድርገሀል እንክት፡
ተዋድቀሀል ለኛ ብቻህን ስትመክት፡
ልዩ ሀይልም ፋኖ አልደረሰልህም፡
ብቻህን ታግለሀል እኛ አንረሳህም፡
እውነትም ጀግና ነህ የሀበሻ አርበኛ፡
አልተንበረከክም ለዚያ ለሴሰኛ፡
መውዜርህን ታጥቀህ ከጫካ ገብተሀል፡
ሽርጣሙ ኮከብ ክብር ይገባሀል፡

የያዝከው መሳሪያ ከተኮሰ አይስትም፡
ጠላቶቹን ያውቃል ፈፅሞ አይሰስትም፡
ደቡብ ወሎ ሆኘ ገድልህን ብሰማ፡
ተደሰትኩኝ ባንተ ኮራሁኝ እኔማ፡
እግረኛህ መሆንን በልቤ ብመኝም፡
የት ሔጀ ላግኝህ አማራጭ የለኝም፡
ያን የጋራ ጠላት ቀጥቅጠህ አሶጣ፡
ወይ እዛው ጨርሰው ወደኛ እንዳይመጣ፡

ወሎ ላይ ቢዘምትም ያ የናት ጡት ነካሽ፡
ሰው በላው ወራሪ ያ የሰው ርካሽ፡
ጨካኝ አረመኔው ውሻ ጁብ ተናካሽ፡
አንተ ተዋድቀሀል ባለህ ሰሜን ክላሽ፡
#ጀግናዬ__!!
ታሪክህ በዝርዝር ባይፃፍልህም፡
ጀግንነትህ ላንተ ባይታወቅህም፡
በዜና መፅሔት ባያቀርቡልህም፡
ሰበር ዜና ብለው ባያካብዱህም፡
ልባችን ውስጥ ነህ እኛ አንረሳህም፡
አብሽር ጀግናችን ሆይ ፈፅሞ እንዳይከፋህ፡
ሞራልህ እንዳይጓሽ እንዳይወይብ ተስፋህ፡
ታንክም ስናይፐር ዶሽቃንም ማርከሀል፡
ጠላትህን ደፍረህ ታግለህ አታግለሀል፡
ኢቲቪ ባይዘግብ ምን ያደርግልሀል፡
ጀግንነትህ ማርኮን ልባችን ፅፎሀል፡
ቀጥቅጠህ ገርፈኸው ጠላትህ አውቆሀል፡

ይሔ የኤጁ ልጅ አይስትም ጥይቱ፡
ሲተኩስ ይለያል ሲወጣ ካፎቱ፡
መሪ መሪውን ነው የሚወጋው ቀስቱ፡
የሚኒሽር ጥይት ከቶ አያባክንም፡
ባንዴ ሁለቱን ኑው ምቱ አያስኮንንም፡
ዜናህን ሲሰማ ጠላትህ ይፈራል፡
ዝናህ የቆዬ ነው ዛሬም ይከበራል፡
ሁሌም ትኖራለህ ሆነህ ለኛ ሞራል፡
ባንተ ላይ ነውኮ ወራሪው የመጣው፡
አንተን አጥቅቶ ነው ወደኛ ያጣው፡
እያለ ወሬኛ ወሬውን ቢነዳም፡
የጦርነቱን ልክ ፈፅሞ አልተረዳም፡
ባሉባልታ ወሬ አትረበሽ ከቶ ፡
ጆሮህን አትስጠው ለዘረጦ እንኩቶ፡
ማንም ሆነ ምንም ሳያግዝህ ብፊት፡
ወጥረኽው ነበር ልክ እንደ ንፋፊት፡
ይህንን እውነታ ሁሉም ፍጥረት ያውቃል፡
ለጀግንነትህ ልክ ይህ ብቻ ይበቃል፡
ሰላም ሰፍኗል አሉኝ ሁሉም በዬ ፈርጁ፡
ኢንሻ ኣሏህ ብዬ ሆንኩልህ ዝግጁ፡
መጥቼ አይሀለሁ ሰሜን ምድር ኤጁ፡

አንት የጦር ገበሬ የሰሜኑ ጀግና፡
የወሎ ሸቂቅ ልጂ የአብስኒያው ሳተና፡
አንተን ለመዘዬር ልቤ ቋምጧልና፡
በሰንሰለታማው በራያ ሸንተረር፡
የጠላት ሰራዊት ደም ባለበት ቆረር፡
ወይም ድሬሮቃ ወልዲያ ጎብዬ፡
አይንህን ለማዬት በፍቅር አባብዬ፡
እንድትቀበለኝ መጣሁ አንተን ብዬ፡
#ባይሆን____!!
ምንም እንኳ እንዳንተ አልሜ ባልመታም፡
ጠላት ከመጣብኝ ግን አላመነታም፡
እናማ አንተኑ ፈልጌ ወዳንተ ከመጣሁ፡
አብሬህ በልቼ አብሬህ ከጠጣሁ፡
የሰሜኑ ተኳሽ ለስምህ መጠሪያ፡
ገና ሳትተኮስ ጠላት ማስፈራሪያ፡
ታጣፊ ክላሿን እንድትሸልመኝ፡
እርሷን እስታጥቅና በፈገግታ ሳመኝ፡
አቦ እወዳችኋለሁ
ጉዞ እጀምራለሁ ሁኛለሁ ዝግጁ፡
ካረፈበት ቦታ ክላሹና ፈንጁ፡
ሔጄ ልመለከት ሰሜን ምድር ኤጁ፡

http://t.me/Sami_Habib
http://t.me/Sami_Habib