Get Mystery Box with random crypto!

የዘመናችን ነሺዳህ በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። 31፥6 ከሰዎ | Sami Habib

የዘመናችን ነሺዳህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

31፥6 ከሰዎችም ያለ ዕውቀት ሆኖ ከአላህ መንገድ ሊያሳስትና ማላገጫ አድርጎ ሊይዛት አታላይ ወሬን የሚገዛ አለ፡፡ እነዚያ ለእነርሱ አዋራጅ ቅጣት አላቸው፡፡ وَمِنَ النَّاسِ مَن يَشْتَرِي لَهْوَ الْحَدِيثِ لِيُضِلَّ عَن سَبِيلِ اللَّهِ بِغَيْرِ عِلْمٍ وَيَتَّخِذَهَا هُزُوًا ۚ أُولَـٰئِكَ لَهُمْ عَذَابٌ مُّهِينٌ

የዘመናችን ነሺዳህ በሙዚቃ እና በመሳሪያ የታጀቡ እንጉርጉሮ ነው፥ ዘፈን ሙዚቃ፣ የሙዚቃ መሳሪያ እና እንጉርጉሮ የታጀበት ስለሆነ ከሸይጧን ነው፦
31፥6 ከሰዎችም ያለ ዕውቀት ሆኖ ከአላህ መንገድ ሊያሳስትና ማላገጫ አድርጎ ሊይዛት ”አታላይ ወሬን የሚገዛ አለ”፡፡ እነዚያ ለእነርሱ አዋራጅ ቅጣት አላቸው፡፡ وَمِنَ النَّاسِ مَن يَشْتَرِي لَهْوَ الْحَدِيثِ لِيُضِلَّ عَن سَبِيلِ اللَّهِ بِغَيْرِ عِلْمٍ وَيَتَّخِذَهَا هُزُوًا ۚ أُولَـٰئِكَ لَهُمْ عَذَابٌ مُّهِينٌ
ተፍሢሩል ኢብኑ ከሲር 31፥6
“ኢብኑ መሥዑድ እንደተናገረው፦ *”ከሰዎችም ከአላህ መንገድ ሊያሳስት ማላገጫ አድርጎ ሊይዛት አታላይ ወሬን የሚገዛ አለ” የሚለው ወሏሂ እርሱ “ዘፈን” ነው”*። كما قال ابن مسعود في قوله تعالى : ( ومن الناس من يشتري لهو الحديث ) قال : هو – والله – الغناء .

“ለህወል ሐዲስ” لَهْوَ الْحَدِيث ማለትም “አታላይ ወሬ” ማለት ሲሆን “ጊናእ” ነው፥ “ጊናእ” غِنَاء የሚለው ቃል “ገና” غَنَّى‎ ማለትም “ዘፈነ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ዘፈን” ማለት ነው። አምላካችን አላህ ኢብሊሥ የሚከተሉትን በድምጹ እንደሚያታልላቸው ተናግሯል። ይህም ድምጹ መደበሪያ፣ ዘፈን፣ ላግጣ እና ስላቅ ነው፦
17፥64 *ከእነርሱ የቻልከውንም ሰው በድምጽህ አታል*፡፡ وَاسْتَفْزِزْ مَنِ اسْتَطَعْتَ مِنْهُم بِصَوْتِكَ
ተፍሢሩል ኢብኑ ከሲር 17፥64
*”ከእነርሱ የቻልከውንም ሰው በድምጽህ አታል” የተባለው እርሱ ዘፈን ነው፥ ሙጃሒድም አለ፦ “ድምጽ የተባለው መደበሪያ፣ ዘፈን፣ ላግጣና ስላቅ ነው”*። واستفزز من استطعت منهم بصوتك قيل هو الغناء قال مجاهد باللهو والغناء أي استخفهم بذلك

"ሐላል” حَلَال ማለት “የተፈቀደ” ማለት ሲሆን “ሐራም” حَرَام ማለት “የተከለከለ” ማለት ነው። ዝሙት እና አስካሪ መጠጥ ሐራም እንደሆነ ሁሉ ሙዚቃም ከዝሙት እና ከአስካሪ መጠጥ ጋር ተያይዞ ክልክል መሆኑ በነቢያችን”ﷺ” ሐዲስ ተነግሯል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 74, ሐዲስ 16
አቡ ዐሚር ወይም አቡ ማሊኩል አሽዐሪይ እንደተረከው፦ “ወሏሂ አልዋሸውም! ነቢዩ”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰምቷል፦ *”ከኡመቴ ውስጥ ጥቂት ሰዎች ለራሳቸው ዝሙትን፣ ሐር ልብስን፣ አስካሪ መጠጥን እና የሙዚቃ መሣሪያ ሐላል የሚያደርጉ ይሆናሉ”*። قَالَ حَدَّثَنِي أَبُو عَامِرٍ ـ أَوْ أَبُو مَالِكٍ ـ الأَشْعَرِيُّ وَاللَّهِ مَا كَذَبَنِي سَمِعَ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ “‏ لَيَكُونَنَّ مِنْ أُمَّتِي أَقْوَامٌ يَسْتَحِلُّونَ الْحِرَ وَالْحَرِيرَ وَالْخَمْرَ وَالْمَعَازِفَ

የዘመናችን ነሺዳህ ከፕሮቴስታንት መዝሙር የተኮረጀ ፈሣድ ነው፥ ትተን የመጣነው የጴንጤ እምነት ትዝ ያስብሉኛል። ዜማው፣ የሙዚቃ መሣሪያው እና ጭፈራው ምንም ልዩነት የለውም፥ ከዚህ ፈሣድ እራሳችንን መጠበቅ አለብን። አሏህ በሙዚቃ መሣሪያ የሚነሽዱትን ሰዎች ሂዳያህ ይስጣቸው! አሚን።

"ይህ ፈሣድ መጋለጥ አለበት፥ ለሌሎች ሠበቡል ሂዳያህ ይሆናል" ካላችሁ እንግዲያውስ ሼር ማድረግ ግድ ይላል።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ

http://t.me/Sami_Habib
http://t.me/Sami_Habib