Get Mystery Box with random crypto!

#ሰለፍይ_ወንድሜ_ሆይ_አደራህን_!! #ይህችንስ_አታግባት_!#በኑር ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ የወንድ ልጂ | Sami Habib

#ሰለፍይ_ወንድሜ_ሆይ_አደራህን_!!

#ይህችንስ_አታግባት_!#በኑር
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
የወንድ ልጂ ክብር ትልቁ ገፅታ፡
ነውና ሚስጥሩ የትዳር ጨዋታ፡
የፈጣሪ ፀጋ የቤተሰብ ፌሽታ፡
የባለቤት ሀሴት የጓደኛ ደስታ፡
የፍቅር ተምሳሌት ውብ ገፀ በረከት፡
ተግባር የሚገልፀው እውነተኛ ስብከት፡
ደስታን የሚለግስ ወደር የታጣለት፡
ነውና ውብ ግርማ ትዳር ብሎ ማለት፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
የትዳር ምርጫህን አስተካክለህ ምረጥ፡
ከመጥፎ አስተያየት ፍጠን ተስፋ ቁረጥ፡
ማንም ስለጮኸ ማንም ስለገፋህ፡
ሐሳብክን አትቀይር አስተውል አይክፋህ፡
መልካም መካሪያችን መልካም ሰው ቢሆንም፡
ውስጥህ ካላመነ የማይሆን አይሆንም፡
ጯሒ ድምፅን ሁሉ ወደህ ተቀብለህ፡
ስህተት አትፈፅም ለቤተሰብ ብለህ፡
ሳትፈልግ አግብተህ ከመደነጋገር፡
ከመግባትህ በፊት እውነትን ተናገር፡
የማትወዳትን ሴት ከቶ እንዳታገባ፡
ትዳር ጌም አይደለም ግራ እንዳትጋባ፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ከመግባትህ በፊት አስተውል አስተንትን፡
ከደረቅ መሬት ላይ ዘርክን እንዳትበትን፡
የተውሒድ የሱና #ንሽ የሌላትን ሴት፡
ተዋት አትፈልጋት አትሰጥህም ሀሴት፡
የሱና ምርኮኛ በተውሒድ ያበበች፡
ሀያዕ ቁጥብነት የተከናነበች፡
አቋሟም ውበቷም ኒቃቧም የሚያምር፡
ውጯም ሆነ ውስጧ ተውሒድ የሚዘምር፡
ሌሎቹን ተዋቸው እርሷን አግባ ከምር?
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ፀንታ የምትጓዝ በመንሀጀ ሰለፍ፡
በአዳድስ ጥመቶች የማትዝለፈለፍ፡
በችግር ጊዜና የምትሆን ፅናት፡
ሰለፍይ ምረጥ እውነተኛ እርሷ ናት፡
ላንተ እምትጨነቅ የምታስብልህ፡
አዕምሮዋ ምጡቅ እቅዷም የብልህ፡
የተውሒድ ደረሳ የሱና ተማሪ፡
የሰላም የፍቅር የመውደድ ዘማሪ፡
ማዕበልን ሰንጥቃ እንደ አሳ ነባሪ፡
ሱና ላይ የፀናች ቢዲዐን ቀባሪ፡
እናት አባትህን አንተንም አክባሪ፡
ስኬትን ከፈለክ ጀግናው ይህችን ምረጥ፡
አጥብቀህ ዱአእ አድርግ ተስፋ ባለመቁረጥ፡
ከእንዲህ አይነቷ ጋር ትዳር ነው ረመጥ፡
ከእንድህ አይነት ትዳር ለብቻ መቀመጥ፡
አወ ላጤነትህ ሳይሻል አይቀርም፡
እውነትን እያወቅክ ባጢል ከምትፈርም፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
#ስለዚህ_ይህችንስ_አታግባት__!!
ሐቅን የማትፈልግ ጥመት ያሰከራት፡
ቁርአንና ሐዲስ ደሊል የማይመራት፡
ሽርክ እየጣፈጠ ተውሒድ የመረራት፡
ሸይጧን ሰውነቷን ተብትቦ ያሰራት፡
ፊትና የምትናፍቅ ስሟን ለማስጠራት፡
ሽርክን እንደገና ጠፍጥፎ ለመስራት፡
ከእግር እስከራሷ ድርቀት የወጠራት
የምታሳንስህ በንቀት በኩራት፡
ይህችን አይነት ፍጡር በሩቁ ነው መፍራት፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
የአህባሽን ጥመት ወዳ ከተጋተች፡
ሀቅን እየተወች ጥመት ካሸተተች፡
ኢኽዋን ከጋለበት በቁሟ ከሞተች፡
ከሰለፎች መስመር ከተንሸራተተች፡
ሁሉም ሹብሀውን የሚቀረሽባት፡
ማንም መጥፎ ጠረን የተነፈሰባት፡
አድስ ፊትና ሁሉ ግራ የሚያጋባት፡
ሱፍያና ተግሊግ ምራቅ የተፋባት፡
ሀዳድዩ ሁሉ የተጫወተባት፡
ተውሒድ ሱና ሲባል ግራ ከሚገባት፡
ሌላ ፈልግ እንጂ ይህችንስ አታግባት፡

http://t.me/Dr_Sami_Habib
http://t.me/Dr_Sami_Habib