Get Mystery Box with random crypto!

የራያ ቆቦ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት በዓሉን ከነሃሴ 16-18 2014 ዓ.ም በራያ በድምቀት ለማክበር | Raya kobo communication

የራያ ቆቦ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት በዓሉን ከነሃሴ 16-18 2014 ዓ.ም በራያ በድምቀት ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡

ሶለል- በራያ ቆቦ ሶለለ ሶለለ ይሄ የማነው ቤት ሶለለ የኮራ የፀዳ ሶለለ.....

የራያ ቆቦ ህዝብ የበርካታ ቱባ ባህሎች ባለቤት ነው፡፡ ከነዚህ ቱባ ባህሎች መካከል በየዓመቱ ከነሃሴ 16-18 በድምቀት የሚከበረው የልጃገረዶች በዓል ሶለል አንዱ ነው፡፡

ሶለል ማለት በራያ ቆቦ አካባቢ ባሉ ልጃገረዶች ዘንድ የሚከበር ሀይማኖታዊና ባህላዊ የልጃገረዶች የጭፈራ ስርዓት ነው፡፡ ይህ ባህላዊ ክዋኔ በላሊበላ አሸንድዬ፣ በሰቆጣ፣ ሻደይ እንዲሁም በራያ ቆቦ ደግሞ ሶለል በመባል በተመሳሳይ መንገድ ይከወናል፡፡

የአከባበሩም ሂደት በመጀመሪያ ደረጃ አሸንዳ የሚባል ቅጠሉ ሰፋፊ የሆነ የሳር ዘር ይነቀልና እሱን በገመድ ላይ በመደርደርና በማሰር በወገባቸው ዙሪያ በመታጠቅና ዳሌያቸውን ከግራ ወደ ቀኝ በማወዛወዝ የሚጨፈር የልጃገረዶች ባህላዊ ክዋኔ ነው፡፡

ከዚያም የባህል አልባሳትን እንደ ትፍትፍ፣ ማይማየ…የመሳሰሉትን በመልበስ፤ ባህላዊ የፀጉር አሰራሮችን እንደ አፈሳሶ፣ ሹሩባ፣ አንድእግራና ሌሎች የፀጉር ስሪት አይነቶችን በመሰራት ቀኑን ደምቀው ያደምቁታል።