Get Mystery Box with random crypto!

የትግራይ ሰራዊት ከመንግስቱ የተሰጠውን ግዳጅ በብቃት ለመፈፀም በሚችልበት አስተማማኝ ቁመና ላይ ይ | መንፈሳዊነት እንማርበት የተዋህዶ ፍሬዎች እንሁን

የትግራይ ሰራዊት ከመንግስቱ የተሰጠውን ግዳጅ በብቃት ለመፈፀም በሚችልበት አስተማማኝ ቁመና ላይ ይገኛል
— ታጋይ ገብረ ገ/ፃድቃን


የትግራይ ህዝብን ከዘር ማጥፋት እና ከሰው ሰራሽ ረሃብ ለመታደግ ወደ አፋር እና አማራ ክልል ተንቀሳቅሶ የነበረው የትግራይ ሰራዊት አላማውን በሚገባ አሳክቶ ለሰላም ቅድሚ በመስጠት ተቆጣጥራቸው የነበሩትን አካባበከዎችን ለቆ ወደ ትግራይ ተመልሷል።

ይህንን ተከትሎ የፋሽስቱ ቡድን የትግራይ ሰራዊት በአፋር እና በአማራ ክልል ግፍ እንደፈፀመ አስመስሎ በሚዲያዎቹ በውሸት ስሙን እያጠፋ ይገኛል። ታጋይ ገብረ የትግራይ ሰራዊት ህዝባዊ እና በስነ ምግባር የታነፀ ስራዊት ነው ሲሉ ገልፀዋል።

የትግራይ ሰራዊት ለሰላም ቅድሚያ በመስጠት ወደ ትግራይ ከመጣ ብኋላ ሰራዊቴን ወደ ትግራይ እንዳይገባ አዝዥሎህ ሲል የነበረው የፋሽስቱ ቡድን ወደ ትግራይ ለመግባት ተደጋጋሚ ሙከራ እንዳደረገ እና በትግራይ ሰራዊት እንደተመከተ የገለፀ ተጋይ ገብረ አሁን ላይ የትግራይ ሰራዊት በከፍተኛ ዝግጁነት እና አስተማማኝ ቁመና ላይ ይገኛል ሲሉ ገልፀዋል።

ሰዎችን የፋሽስቱ ቡድን የደረሰበትን ሽንፈት እና የሞራል ውድቀት ለመሸፈን እና ሌላ እልቂት ለመደገስ በማሰብ ለከፍተኛ መኮንኖች ያደረገው የሽልማት ስነ ስርዓት በኢትዮጵያ ህዝብ ማፌዝ ነው ያለው ተጋይ ገብረ በርካታ ታንኮችን እና ከባድ መሳርያዎችን አስረክቦ ፍሽስታውያን እየደመሰሰ ከትግራይ እስከ ደብረብርሃን የሸሸ ሰራዊት ሽልማት ሳይሆን ተጠያቂ መሆን ነበረበት ብሏል።

በመጨረሻም በውጭም ይሁን በውስጥ ያለ የትግራይ ህዝብ ነፃ ያልወጡ አካባቢዎችንም ነፃ ለማውጣት ወደ ትግራይ ለመግባት የሚያደርጉት እንቅስቃሴም ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጠላቶቻችን ለማጥፋት ከሌላው ጊዜ በተለየ ትግላችን ማጠናከር አለብን ሲል መልእክቱን አስተላልፋል።





https://t.me/r00M3mF3Zhw2YzE0