Get Mystery Box with random crypto!

ጾመ ትግራይ! በትግራይ ላይ እየተፈጸመ ያለዉ ግፍ እና መከራ እንዲቆም ለሶስት ቀናት የሚቆይ የጾ | መንፈሳዊነት እንማርበት የተዋህዶ ፍሬዎች እንሁን

ጾመ ትግራይ!

በትግራይ ላይ እየተፈጸመ ያለዉ ግፍ እና መከራ እንዲቆም ለሶስት ቀናት የሚቆይ የጾም እና ጸሎት መርሀ ግብር ማወጇን የትግራይ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስትያን አስታወቀች።

የመቐለ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ኢሳያስ በሰጡት መግለጫ ከታህሳስ 18 እስከ ታህሳስ 20 /2014 ዓ/ም ድረስ የሚቆይ የጸም እና የጸሎት መርሀ ግብር የትግራይ የሃይማኖት አባቶች እና ሊቃዉንት ተመካክረዉ ዉሳኔዉ እንደተወሰነ ተናግረዋል።

ብጹዕነታቸዉ በትግራይ ህዝብ ላይ ጄኖሳይድ እየተፈጸመ ነዉ ያሉ ሲሆን ፀሓይም ከፈጣሪ ባትሆን ኖሮ ወደ ትግራይ እንዳትወጣ ይከለከሉን ነበር በማለትም ያለውን ከበባ አውግዘዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን በትግራይ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለውን የህዝብ ማጥፋት ወንጀል ከማስቆም ይልቅ ራሷም ተባባሪ እየሆነች መሆንዋን በመግለጫው ተመላክቷል።


https://t.me/r00M3mF3Zhw2YzE0