Get Mystery Box with random crypto!

እጸልያለሁ ∞ ቃሉን አነባለሁ። እጸልያለሁ ∞ ቃሉን አጠናለሁ። አንድ ክርስቲያን በመንፈሳዊ ሕይወ | ቅኔ እና ዜማ / QINE ENA ZEMA official

እጸልያለሁ ∞ ቃሉን አነባለሁ።
እጸልያለሁ ∞ ቃሉን አጠናለሁ።

አንድ ክርስቲያን በመንፈሳዊ ሕይወቱ እንዲያድግ (እድገት የሚለውን ቃል እያስተዋልን "እድገት ማለት ከአንድ ዝቅተኛ ደረጃ ወደ ሌላ ከፍተኛ ደረጃ ለማደግ የሚደረግ ግስጋሴ ነው።") መጸለይና ቃሉን ማንበብ መሠረታዊ ነገር ነው።

መንፈሳዊ እድገት ክርስቶስን ወደ መምሰል ማደግ ነው። ልክ አንድ ሰው ሌላውን ወዳጁን ለመምሰል እለት እለት ከእርሱ ጋር መዋል እና ወዳጁ ምን እንደሚያደርግ ፣ ምን እንደሚያስብ፣ አነጋገሩን እና ሁሉ ነገሩን ማጥናት እንዳለበት እለት እለትም እርሱን ለመምሰል መለማመድ እንዳለበት ሁሉ ክርስቶስንም ለመምሰል እለት እለት ድምጹን ለመሰማት ከእርሱ ጋር መነጋገር (መፀለይ) ስለ እርሱ በድንብ ለማወቅ ቃሉን ማንበብ ግዴታ ነው።
በዚህ ላይ መዘንጋት የሌለብን ኢየሱስን ሙሉ ለሙሉ መስለን ወይንም አውቀን ስለማንጨርስ እርሱን መምሰልም ሆነ እርሱን ማወቅ የዘወትር ስራችን ሊሆን ይገባል፤ እርሱን ለመምሰል የምናደርገው የእድገት ግስጋሴ የሁል ጊዜ ነው።

ስለዚህ “ጌታ ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እንደ ሆነ፥ ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ተንኰል የሌለበትን የቃልን ወተት ተመኙ።”
(1ኛ ጴጥሮስ 2፥2-3)

አስተውሉ “ሰውነትን ለሥጋዊ ነገር ማስለመድ ለጥቂት ይጠቅማልና፤ እግዚአብሔርን መምሰል ግን የአሁንና የሚመጣው ሕይወት ተስፋ ስላለው፥ ለነገር ሁሉ ይጠቅማል።”
— 1ኛ ጢሞቴዎስ 4፥8

ስለሆነም በመንፈሳዊ ህይወቴ ለማደግ፦ #እጸልያለሁ_ቃሉን_አጠናለሁ
#እጸልያለሁ_ቃሉን_አነባለሁ_Challenge!!
---
ይሄን ቻሌንጅ በመቀላቀል ሁሉም ሰው እንዲጸልይ እና ቃሉን እንዲያነብ ቻሌንጅ ያድርጉ

---
nazrawi_tube
Pleas share