Get Mystery Box with random crypto!

#ቆይ_ግን_ላሚቷ_የፈለግነውን_ባትወልድስ? “ድል ድል ይሸተኛል ኦሆሆ አሃሃ” ባይሸተንስ ግን? | ቅኔ እና ዜማ / QINE ENA ZEMA official

#ቆይ_ግን_ላሚቷ_የፈለግነውን_ባትወልድስ?

“ድል ድል ይሸተኛል ኦሆሆ አሃሃ”
ባይሸተንስ ግን?

“ተራራዬን ናደው”
ባይንደውስ ግን?

“በዚህ ስል በረኩቱ በዚያ ስል በረከቱ ከበበኝ”
ቆይ ባይከበንስ?

“ተራው የኔ ነው የኔ”
ቆይ ግን ባይሆንስ?

“የለመንኩትን በሙሉ ሰጠኝ”
ባይሰጠንስ ግን?

ባንጠረምሥስ ግን?
ባንሰባብርስ ግን?
ባናፈራርሥስ ግን?
ባንበዘብዝስ ግን?

በእኛና በፈጣሪ መካከል ያለውን ግንኙነት ፈጽሞ በ “አምጣና እንካ” ቀመር ላይ መመስረት የለብንም፡ እርሱ የሕይወት ቃል አለው ስለዚህ ከምንምና ከማንም በላይ ተመራጭ ነው።
ጠረመስንም አልጠረምስንም NO WHERE TO GO.

ቆይ ቆይ ግን ላሚቷ የምንፈልገውን ባትወልድስ?
ግድ የለም ላሚቷስ ለምትወልደው ሲባል ትፈለግ ፈጣሪ ግን ለምንድር ነው የሚፈለገው?
ለሚሰጠን ወይም ለሚያደርግልን ነገር ነው ወይስ በራሱ ተፈላጊና ተመራጭ ስለሆነ ነው?
#እነዚህ_ሁሉ_አምነው_ሞቱ
___
yilu danu
@nazrawi_tube