Get Mystery Box with random crypto!

አገራችን ኢትዮጵያ በታሪክ መዝገብ ውስጥ በደማቅ ቀለም ተጽፋ የምትገኝ፤ ከአለም ስልጣኔ በፊት የስ | Prosperity Party - ብልፅግና

አገራችን ኢትዮጵያ በታሪክ መዝገብ ውስጥ በደማቅ ቀለም ተጽፋ የምትገኝ፤ ከአለም ስልጣኔ በፊት የስልጣኔ ባለቤት የነበረች የመቻቻል እና የብዝሃነት አገር ናት፡፡ ኢትዮጵያ ታላቅ አገር ናት ሲባልም እንደው በቃል ብቻ ለማለት ሳይሆን በተጨባጭ ታላቅነቷን የሚመሰክሩ በርካታ መገለጫዎች ስላሏት ጭምር ነው።

ኢትዮጵያን በማንም ሃይል ፍላጎትም ሆነ ንግግር ዝቅ ማድረግ እንዳይቻል አድርገው ከፍ ያደረጓት አባቶቻችንን ስብዕና ተላብሰን እና አገር ከፍ ስትል ከፍ የሚለው የዜጎቿ ክብር መሆኑን በመገንዘብ ሁሌም ቢሆን እንደታሪካችን ንግግራችንም ተግባራችንም ኢትዮጵያን የሚመጥን ሊሆን ይገባል፡፡

ኢትዮጵያን ለማሻገር በሚደረገው የትግል ምዕራፍ የሚገጥሙ ችግሮች ሁሉ በጽናታችን ልክ የምንሻገራቸው እንጂ ወደፊት ከመገስገስ የሚያቆሙን ሊሆኑ አይገባም፡፡ የትናንት ታሪካችን የሚያስተምረን ይሄንኑ ነውና፡፡ በመሆኑም ዛሬም፣ ነገም፣ ወደፊትም በጽናት በመቆም ትኩረታችን ችግሮቻችንን ከስር ከስር እየነቀሉ ኢትዮጵያን ማጽናት ላይ ሊሆን ይገባል፡፡

የኢትዮጵያን ብልጽግና ማረጋገጥ የሚቻለውም ችግር የማይበግረውና በአገራዊ ጥቅሙ የማይደራደር ጽኑ ትውልድ በመገንባት ብቻ ነው፡፡