Get Mystery Box with random crypto!

የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ በብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት ቅጥር ጊቢ ውስ | Prosperity Party - ብልፅግና

የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ በብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት ቅጥር ጊቢ ውስጥ እየተሰሩ ያሉ የአረንጓዴ አሻራ እንቅስቃሴዎችን ጎብኝተዋል፡፡
አቶ አደም በጉብኝቱ ወቅት የተተከሉ ችግኞች ለምግብነት የሚውሉ እና በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚደርሱ መሆናቸው በበጎ የሚታይ እንደሆነ ገልፀው የተጀመሩ እንቅስቃሴዎች አበረታች እንደሆኑ እና ይበልጥ ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
ፅ/ቤቱም ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት በመስጠት ተጨማሪ ባለሙያዎችን ጭምር በመመደብ የተጀመሩ እንቅስቃሴዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡
በጅምር ላይ ያሉ ተግባራትም በሳይንሳዊ መንገድ እየዳበሩ መቀጠል እንደሚገባቸውና የዋና ፅ/ቤቱ ተሞክሮዎች በሁሉም ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ውስጥ መስፋፋት እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡