Get Mystery Box with random crypto!

የተጠና እርምጃ በመውሰድ በአሸባሪው ሸኔ ላይ ኪሳራ ማድረስ ተችሏል - የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገል | Prosperity Party - ብልፅግና

የተጠና እርምጃ በመውሰድ በአሸባሪው ሸኔ ላይ ኪሳራ ማድረስ ተችሏል - የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

የተጠና እርምጃ በመውሰድ በአሸባሪው ሸኔ ላይ ኪሳራ ማድረስ መቻሉን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ፡፡

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸውም፥ የአሸባሪው ሸኔን ጥቃትን የመከላከልና ቡድኑን የማስወገድ ዘመቻዎች ሲካሄዱ መቆየታቸውን አንስተዋል፡፡

በተለይ በኦሮሚያ ክልልና አዋሳኝ አካባቢዎች የሽብር ቡድኑ እየረበሸ እንደሚገኝ አንስተው፥ በፌዴራልና ኦሮሚያ ክልል የጸጥታ ሃይሉ ጥምረት ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ዘመቻው ሲካሄድ መቆየቱን ገልጸዋል፡፡

በዘመቻውም ትልልቅ ስኬቶች ተመዝግበዋልም ነው ያሉት፡፡

ሲወሰዱ የነበሩ ዘመቻዎች በተጠኑ ቦታዎች ላይና የተወሰኑ ቦታዎች ዒላማ በማድረግ የሽብር ቡድኑን እንቅስቃሴ ከግምት ውስጥ በማስገባት ሲካሄድ መቆየታቸውን አመልክተዋል፡፡

እንደአብነት ከጥቂት ቀናት በፊት የተወሰደውን እርምጃ አስመልክቶ እንዳሉት ፥ በሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን የሱሉላ ፊንጫ ወረዳ ላይ በተፈጸመው እርምጃ በርካታ የሸኔ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ ተወስዷል ነው ያሉት፡፡

በአካባቢው የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ይዞታ የሸንኮራ አገዳ ማሳ ውስጥ በመሸሸግ የተከፈተባቸውን እርምጃ ለመሸሽ ሲሞክሩ እንደነበር አንስተዋል፡፡

በዚህም የተጠና እርምጃ በመውሰድ በአሸባሪው ሸኔ ላይ ኪሳራ ማድረስ ተችሏል ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ፡፡