2022-06-07 21:36:24
ብሉይ ኪዳን ይተርጎም፡-
‘’…..ጳውሎስም እንደ ልማዱ ወደ እነርሱ ገባ፤ ሶስት ሰበትም ያህል ከእነርሱ ጋር ከመጽሀፍት እየጠቀሰ ይናገር ነበረ፤ ሲተረጉምም ክርስቶስ መከራ እንዲ ቀመልና ከሙታን እንዲነሳ ይገባው ዘንድ እያስረዳ፡፡ ይህ እኔ የምሰብክላቹ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ነው ይል ነበረ፡፡ ‘’ሐዋ.17፡1-3
ጳውሎስ ሶስት ሰበት ከነሱ ጋር ሲያሳልፍ መጽሀፍትን ይነገራቸው ነበር፤ የሚነግራቸው መጽሀፍ ሌላ እንዳይመስልህ ሰላሳ ዘጠኙን የብሉይ ኪዳን ክፍል ነው፡፡ ይህን ክፍል ሲያስረዳቸው እየተረጎመላቸው ነበር፡፡
ለምን አንብቦላቸው ሳይተረጉም አላለፈውም፡-
ምክንያቱም፡-
1. ብሉይ ኪዳን ሲነበብ መጋረጃ ይጋረድባቸዋል፡፡
2. ብሉይ ኪዳን ሲነበብ ህይወት አይሆናቸውም፡፡
3. ብሉይ ኪዳን ሲነበብ ህይወት የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ይጠፋል፡፡
4. ብሉይ ኪዳን ሲነበብ የእግዚአብሔር ጽድቅ ችላ ይባላል፡፡
5. ብሉይ ኪዳን ሲነበብ አሁንም ባርነት አለ፡፡
ታዲያ ብሉይ ኪዳን ሲተረጎም ምን ይፈጠራል፡-
1. ብሉይ ኪዳን ሲተረጎም መጋረጃው ከፊታቸው ዘወር ይላል፡፡
2. ብሉይ ኪዳን ሲተረጎም ህይወት ይሆንላቸዋል፡፡
3. ብሉይ ኪዳን ሲተረጎም ህይወት የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ይበራላቸዋል፡፡
4. ብሉይ ኪዳን ሲተረጎም የራስ ጽድቅ ችላ ይባላል፡፡
5. ብሉይ ኪዳን ሲተረጎም አሁንም በነጻነት ውስጥ አለህ፡፡
አግዚአብሔር የብሉይ ኪዳን ትርጉም ይጨምርልን፡፡ አይኖቻችን በኢየሱስ ክርስቶስም የተከፈተ ይሁን፡፡ አሜን!!!
መጽሀፍት ሁሉ ስለ ኢየሱስ ያወራሉ!!!!! ሀ….ሌ….ሉ….ያ
76 views𝕕'ርሻዬ, 18:36