Get Mystery Box with random crypto!

#ዜና ድንቃ ድንቅ! ታህሳስ 24 ቀን 2015 ዓ/ም ጦራ ኮሚዩኒኬሽን አንዲት ዶሮ ባልተለመደ | ዶሮ እርባታ ለጀማሪዎች doro erbta be Ethiopia

#ዜና ድንቃ ድንቅ!
ታህሳስ 24 ቀን 2015 ዓ/ም ጦራ ኮሚዩኒኬሽን

አንዲት ዶሮ ባልተለመደ መልኩ በአንድ ቀን ሁለት እንቁላል ጣለች።

ዶሮዋ በአንድ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ሁለት እንቁላል የጣለችው በስልጤ ዞን ጦራ ከተማ አስተዳደር ሚሊኒዬም ቀበሌ አቶ ሚፍታ ዘይኔ የተባለ ግለሰብ ቤት ነው።

የዶሮዋ ባለቤትና የጦራ ሚሊኒዬም ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አቶ ሚፍታ ዘይኔ ባልተለመደ መልኩ በአንድ ቀን ሁለት እንቁላል የጣለችዋ ዶሮ በትናንትናው ዕለትም ሁለት አስኳል ያለው አንድ እንቁላል እንደጣለች ነግረውናል፡፡

አቶ ሚፍታ አግራሞት የፈጠረባቸውን ይህን ክስተት ከተመለከቱ ወዲህ ዶሮዋን በመከታተል ላይ እያሉ በዛሬው ዕለትም በግምት ከቀኑ 8፡00 አካባቢ በተመሳሳይ ሰአት ሁለት እንቁላሎችን ልትጥል እንደቻለች በአይናቸው መመልከት ችለዋል፡፡
ዶሮዋ እስከ አሁን ድረስ በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚትገኝም ከደረሰን መረጃ መረዳት ችለናል።
ይህ አስገራሚ ክስተት የተከሰተው በዛሬው ዕለት ማለትም ዕለተ ሰኞ ታህሳስ 24/2015 ዓ/ም


አስተያየት ስጡበት