Get Mystery Box with random crypto!

ቀና~ትውልድ

የቴሌግራም ቻናል አርማ positive_brains — ቀና~ትውልድ
የቴሌግራም ቻናል አርማ positive_brains — ቀና~ትውልድ
የሰርጥ አድራሻ: @positive_brains
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 745

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-08-02 08:08:33

ፈገግታን የማይችል ሰው
ሱቅ መክፈት የለበትም!

Faysul
54 viewsedited  05:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 02:38:25
56 views23:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 02:10:01 "የተረጋጋ ህይወት እንዲኖርህ"

... መፅሀፍትን አንብብ ብዙ አታውራ ማውራት ሲኖርብህ ግን ዝም አትበል ፣ ምክር እና አስተያየት ለመቀበል አትፍራ ለተደረገልህ ጥሩ ነገር አመስግን

የማታውቀውን ጠይቅ በየወሩ ካለህ ገቢ ላይ ትንሹንም ቢሆን ቆጥብ ዛሬ መስራት የምትችለውን ዛሬውኑ ስራ

የሰው ልጅ ሲቸግረው ልብሱን ፣ የቤቱን ዕቃ ፣ ኩላሊቱንም ሳይቀር ሊሸጥ ይችላል ህሊናውን ከሸጠ ግን በጠና ቸግሮታል ማለት ነው።

ዶ/ር ምህረት ደበበ
57 views23:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 21:37:14 የዛሬው ሀገር አቀፋዊ ዝናብ ይሄው ከቤት ሳያስወጣን ውሏል
65 views18:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 19:27:26
እንደ ብጤነታችን ቅኝት፣ እንደ መሻታችን ውጤት፣ እንደ ማሰባችን ፍኖት....
የሆነው ሁሉ የሆነው ከሕይወት ኢፍትሐዊነት አይደለም… ከእኛ የሕይወት ግንዛቤ ችግር እንጂ፣

ሕይወት የበጎነታችን በጎ ምስልና የክፋታችን ክፉ እሳቤ የሚያጠላባት ግለሰባዊ ትርጉም ሆናለች።

ግና አምናለሁ፣

ክፋት ከቆለፈው… የፍቅር እጦት ካዛገው የስብዕናችን አስኳል ውስጥ የመልካምነታችን ልምላሜ ሰብሮ እንደሚወጣ !!

ደምስ ሰይፉ

ስብዕናችን
71 views16:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 00:09:03
96 views21:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 00:08:22 ችግሩ ከመማር ሳይሆን መማር ያለብንን ካለማወቅና አስቀድሞ የሚያማክረን፣ በተጨባጩ የሥራው ዓለም ማርኬቱ ላይ የሚያስፈልገውን የትምህርት መስክና አካሄዱን የሚጠቁመን ስለሌለና በተማርንበት መስክ ላይም ተግባር ተኮር ክህሎት ይዞ ከመውጣት ይልቅ ለወረቀት ውጤት ይበልጥ ትኩረት መስጠት ላይ ነው።


አንዳንድ ጊዜ ከረፈደ በኋላ ሚስጥሩ ይገባንና «ምነው ይሄን ነገር ያኔ አውቄ በነበር?» ብለን የምንቆጭበት አጋጣሚ ብዙ ነው።


ለማንኛውም ከታች ታዳጊ ልጆችን እያስተማራችሁ ያላችሁ ወላጆች ነገ የእናንተም ልጆች እጣ ፈንታ ይህ ከመሆኑ በፊት ከወዲሁ ምን መማር እንዳለባቸው አስቡበት።

ዋንጫ ሁላ ተሸልመው ሥራ ያጡ ሰዎችን እየታዘብን ያለበት ሁኔታ ነው ያለው። በዚሁ ኋላቀር ቀር አካሄድ ከቀጠልን ገና ብዙ እናያለን።

murad
100 views21:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 18:33:04
ሁሉም ሰው ሊወድህ አይችልም ።
ያለ ምክንያትም ሚጠሉህ ሰዎች ይኖራሉ። ሳያውቁህም የሚጠሉህ ሰዎች አይጠፉም።

ህይወት እንዲህ ናት
ፈገግ እያልክ ጉዞህን ቀጥል
96 views15:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 15:00:20 ገንዘብ የማይገዛው ለሽያጭ ያልዋለ፣

ከሃብታም ተነጥቆ ለኛ የታደለ፣

ሽ ፍቅር ሽ ጤና ከድሃ ቤት አለ።

Copy
113 views12:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 12:54:38 #ነፃ_ጥቅል_ከኢትዮ_ቴሌኮም !

ኢትዮ ቴሌኮም በ2014 በጀት አመት 61.3 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

ይህም የእቅዱን 87.6 በመቶ ነው ብሏል።

ይህን በማስመልከት ለሦስት ቀናት የሚቆይ ነጻ ጥቅል ስጦታ ማቅረቡን ገልጿል።

ኢትዮ ቴሌኮም ያስመዘገበውን ስኬት አስመልክቶ ከህብረተሰቡ ጋር ለመጋራት ሲል የዳታ፣ ድምፅ እና የመልዕክት ጥቅል ስጦታዎችን ማቅረቡን ነው ዛሬ ያሳወቀው።

በዚህም፦

1.5 ጌጋባይት ዳታ በቀን 512 ሜባ፤

45 ደቂቃ በቀን 15 ደቂቃ፤

100 መልዕክት በቀን 33 መልዕክቶችን፤

የ10 ደቂቃ አለምአቀፍ ጥሪ በቀን 3 ደቂቃ ለተጠቃሚዎች በነጻ አቅርቧል።

ስጦታው ከዛሬ ሐምሌ 21 ከሌሊቱ 06:00 ሰአት - እስከ ምሽቱ 12 ሰአት ድረስ ለ3 ቀናት ይቆያል።

@positive_brains
@positive_brains
132 views09:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ