Get Mystery Box with random crypto!

ችግሩ ከመማር ሳይሆን መማር ያለብንን ካለማወቅና አስቀድሞ የሚያማክረን፣ በተጨባጩ የሥራው ዓለም ማ | ቀና~ትውልድ

ችግሩ ከመማር ሳይሆን መማር ያለብንን ካለማወቅና አስቀድሞ የሚያማክረን፣ በተጨባጩ የሥራው ዓለም ማርኬቱ ላይ የሚያስፈልገውን የትምህርት መስክና አካሄዱን የሚጠቁመን ስለሌለና በተማርንበት መስክ ላይም ተግባር ተኮር ክህሎት ይዞ ከመውጣት ይልቅ ለወረቀት ውጤት ይበልጥ ትኩረት መስጠት ላይ ነው።


አንዳንድ ጊዜ ከረፈደ በኋላ ሚስጥሩ ይገባንና «ምነው ይሄን ነገር ያኔ አውቄ በነበር?» ብለን የምንቆጭበት አጋጣሚ ብዙ ነው።


ለማንኛውም ከታች ታዳጊ ልጆችን እያስተማራችሁ ያላችሁ ወላጆች ነገ የእናንተም ልጆች እጣ ፈንታ ይህ ከመሆኑ በፊት ከወዲሁ ምን መማር እንዳለባቸው አስቡበት።

ዋንጫ ሁላ ተሸልመው ሥራ ያጡ ሰዎችን እየታዘብን ያለበት ሁኔታ ነው ያለው። በዚሁ ኋላቀር ቀር አካሄድ ከቀጠልን ገና ብዙ እናያለን።

murad