Get Mystery Box with random crypto!

የኔ' ማስታወሻ ...✍️

የቴሌግራም ቻናል አርማ poethaymi — የኔ' ማስታወሻ ...✍️
የቴሌግራም ቻናል አርማ poethaymi — የኔ' ማስታወሻ ...✍️
የሰርጥ አድራሻ: @poethaymi
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.20K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል የማይዳሰስ ጉዳይ የለም የተለያዩ አስገራሚ ታሪኮችን፣ ግጥሞችን፣ መጣጥፎችን፣ ወጎችን እንዲሁም በጥበባዊ እይታ የተቃኙ ሁሉ አይነት ጉዳዮችን እናይበታለን ሼር በማድረግ ቤተሰብ እናብዛ... እወዳችኋለሁ❤️
for any comment :-
👉 @haymihabeshawit

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-27 12:13:35 የጠላሁሽ ለታ

(ልዑል)
የጠላሁሽ ለታ....
ዓለም ትዙርብኝ
ፀሐይም አትውጣ ጨለማው ይምጣብኝ
ጨረቃዋም ትጥፋ ከዋክብት ይርገፉ
ውቅያኖሶች ደርቀው ዕፅዋቶችም ይጥፉ
........……………………
የጠላሁሽ ለታ…
ለክህደቴ ዋጋ ይሁዳ ይበሉኝ
ለጭካኔዬ ልክ ሂትለርን ያድርጉኝ
ነፍስ እንዳጠፋ ሰው ሰዎች ይጠየፉኝ
……………………………………
የጠላሁሽ ለታ…
እግሮቼም እጆቼም
ዓይኖቼም ጆሮቼም ለኔ አይታዘዙ
አፍ ከነፍሴ ጋራ
ተባብረው ተስማምተው
የክህደቴን ቃላት ለዓለም ይናዘዙ
…………………………………
የጠላሁሽ ለታ…
በበድን አካሌ በጨቀየው ነፍሴ
በተነጨው ፀጉሬ በረገፈው ጥርሴ
ባስቀያሚነቴ ሚደርስብኝ ልጣ
በቁሜ ልሰቃይ ልታሰር ልቀጣ
…………………………………
ፍቅሬ……
የጠላሁሽ ለታ እርግማኖች ሁሉ
ወደኔ ይቅረቡ ብዬ የምመኘው
አንቺን የማልጠላ ፍፁም ሆኜ ሳይሆን
ካላንቺ ለመኖር ስለማላስብ ነው
………………………………
ፍቅሬ……
እኔም አንቺም ውዴም ካንድ ወንዝ ተቀድተን
ከስሜቴ ስሜት
ከእምነትሽ እምነት በፅናት ተጋርተን
የተግባባነው ቃል በኑሯችን ፀንቶ
ካኖረን በፀጋው ሁሌም አበርትቶ
………………………………………
የምጠላሽ ለታ…
በጉዞዬ መሃል እንቅፋቴ ይብዛ
ምጠለልበትም ምበላውም ልጣ
በቁሜ ልሰቃይ ልታሰር ልቀጣ
…………………………………
የምጠላሽ ዕለት…
እነዚህ መዓቶች በላዬ ሊዘንቡ
ሊወርዱ ከሆነ
ዘላለም ስወድሽ
ነፍሴ ከስቃዪ ከርግማኑ ዳነ

@poethaymi
263 views09:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 14:16:46 እስመ ፍቅር ከመ ሞት ጽንዕት፡፡
ፍቅር እንደ ሞት ጽኑ ናት!
@poethaymi
247 viewsedited  11:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 11:11:13 አንድ
ፂሙን ያጎፈረ ስከርፉን ያጣፋ
ደራሲ ፈላስፋ
ከዚህ ሀገር ሰዎች ራሱን ለይቶ
በቅኔ በቋንቋ ሚስጥር አበራይቶ
ያየውን ጎዳና መንገድ አመላክቶ
አረቄ ይጠጣል ከሀሳቡ ባነሱ መንጋ ተበሳጭቶ!
ሲጋራውን ለኮስ...አረጌውን ብድግ
ይሄ ስብስብ መንጋ ለምን ነው 'ማያድግ?
ለምን አያነብም መፅሄት ጋዜጣ?
መነሳት መራመድ መፏለል ዝነጣ.. .
ለምን አያነብም ... አዲስ ፍልስፍና?
ለምን አይመሰጥም.. .በግጥም ትወና?
መነሳት መተኛት ተመሳሳይ ዑደት
ያበሳጫል እውነት!
ሲጋራውን ለኮስ የጫት ቅጠል ቅንጥስ
ቃም ቃም ... ቃም ቃም ...
እንዴት አንድ ይጠፋል ከዚህ መንጋ ልባም?
መነሳት መተኛት.. ስራ መሄድ ትዳር
ሁሌ አንድ መንገድ ... መፍዙዝ የቁም ስካር
እንዴት አይጠይቅም ፈጣሪን ሞግቶ?
ለምን አይመሰጥም መፅሀፍ ሸምቶ ?
እከሌ ተወልዶ በዚህ ዓመት ሞተ
ታሪክ ሳያስቀምጥ ስሙን ሳያስነሳ ...
አላወቀም እንጂ ኖሮም ነው ሬሳ !
ለምን አያነብም ... አዲስ ፍልስፍና?
ለምን አይመሰጥም.. .በግጥም ትወና?
ሁሌ የስጋ መንገድ ተመሳሳይ ዑደት
ያበሳጫል እውነት!
ብሎ ይናደዳል መሸታ ቤት ገብቶ
ሲጋራ እያጨሰ አረቄ ጠጥቶ ...

ፂሙን ያጎፈረ ስከርፉን ያጣፋ
ደራሲ ፈላስፋ
ምናለ ቢሰማ መንጋው የሚለውን
ስለሱ ያየውን ...
አይታጠብ አይፀዳ ፂሙን አይከላ
መፅሀፍ ታቅፎ አዋቂ ነኝ ይላል
የሰፈር ቀውላላ ...
ምናለ ቢታጠብ.. . ራሱን ቢጠብቅ?
ምናለ ቢያገባ.. .ልጆቹን ቢያሳድግ ?
ምናለ ቢሰራ ... ከሚጫጭር ግጥም?
እንዲህ ለቅፈላ ... ሰንፎ ከሚለግም !
አሁን ምን ያደርጋል ?
አዋቂ ነኝ ማለት ... መደስኮር መደንፋት
ሳይፀዱ ሳያምሩ
አሁን ምን ያደርጋል ?
ላልኖሩበት ዓለም ታሪክን ቢያስቀሩ ።
አሁን ምን ያደርጋል ?
ራሱን የማያቅ ያ ግብዝ ፈላስፋ
ሌላውን ለማወቅ ቢጫጭር ቢለፋ?
ለምን ስራ አይሰራም ... ኑሮው እንዲቃና?
ለምን አይመሰጥም.. .በልጁ አንገት ቃና?
አረቄ መጠጣት ሲጋራ መጠጣት
መፅሀፍ ይዞ መዞር ... ተመሳሳይ ዑደት
ያበሳጫል እውነት!

(ሚካኤል.አ)

@poethaymi
292 views08:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 09:22:24 (ምራጭ...)
===========

መወሰን ተስኖት
ምርጫን ሲያወዳድር
አንዱን ከፍ ሲያደርግ
አንዱን ገፍቶ ሲጥል
አንዱን ሲያሞጋግስ
አንዱን ሲያብጠለጥል
:
ጊዜ ከነፈና...
'ምራጭ' ሆኖ አረፈ
'የመራጭ' ሰው እድል !

@poethaymi
275 viewsedited  06:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 21:23:29 ስንት አይነት ሰው አለ በማርያም
303 views18:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 12:13:58
#ሌላ_ሰዉ

ሚካኤልን ጠየኩት :-
ከፍቶህ ያውቃል ስለዉ "እጅግ ብዙ ጊዜ "
ይሄ መልሱ ነበር የልፋት ደሞዜ
እኔም ቀጠልኩና መኖር አስጠልቶህ ሞትስ ናፍቆህ ያውቃል ?
በፍፁም አለ እሱ "ይሄ እንዴት ይሆናል "
ሶስተኛ ጥያቄ
እጅግ የሚወድህ ውዴ የሚልህ ሰዉ
ካንተ ሚበልጥበት ሚያርቀው ምንድን ነዉ?
:
የመለሰልኝ መልስ እጅጉን ቢያስከፋኝ
ከሰው ተደብቄ ሳነባ አነጋሁኝ
ግንኮ ..
መልሱ ልክ ነበር ..
እጅግ ወድሻለሁ ያኔ የሚለኝ ሰዉ
ከኔ ሚበልጥበት መልሱ #ሌላ_ሰዉ ነው።

ሚካኤል መካሪዬ አመሰግናለሁ
እኔን ብሎ ገጣሚ ደግሞ

ባለ ማስታወሻዋ


t.me/poethaymi
341 viewsedited  09:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 16:51:37 @poethaymi
352 views13:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 14:31:07 በዝች ሚስጥር ዓለም!
በዝች ስውር ዓለም
.
ከጠያቂ በቀር ተጠያቂ የለም

በዝች ሚስጥር ዓለም!
በዝች ስውር ዓለም
.
ምዕመናን እንጂ አንድም አማኝ የለም

በዝች ሚስጥር ዓለም!
በዝች ስውር ዓለም
.
ከሀሰት በስተቀር ቅንጣት እውነት የለም



@poethaymi
350 views11:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 11:50:04 "ውበት ለማይገባው ለአንዳንዱ ሰነፍ ሰው
ተራራን ያየ ለት ክምር ነው ሚመስለው"
..እንዳለ (ኤፍሬም ስዩም)

ፍቅር የማይገባው
ውበት የማይገባው አንድ ጠማማ አየው
እናቱ ስትስቅ .... ሳቅ ብቻ ሚታየው

የእናቱን ማንነት በቅርበት ባላቅም
እናት ግን ለልጇ
ሳቅ ብቻ አትስቅም!

*------------------*
@mikiyas_feyisa
(ሚኪያስ ፈይሣ)


@poethaymi
409 views08:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ