Get Mystery Box with random crypto!

//ልጠብቃት\\ አንዲት ቆንጆ መልከ ቀና፤     ቀና ብዬ አየሁና፤  ባለማመን ሳለሁ ገና።  ፊቴን | እግር ኳስ Meme™

//ልጠብቃት\\
አንዲት ቆንጆ መልከ ቀና፤
    ቀና ብዬ አየሁና፤
 ባለማመን ሳለሁ ገና።
 ፊቴን ሳብስ በተደሞ፤
      በአለም ካለሁ
      ወይም ደግሞ።
እውነት ከሆንኩ ሳረጋግጥ፤
  እኔን ጥላ እሷ ጥፍት።
  እፉዬ ነች የኔ ገላ፤
ታይታ የጠፋች እንደ ጥላ።
ገነት ይሁን እኔ የሄድኩት፤
ሴት መላእክት ነው ያየሁት፤
 ግን እፆታ መች አላቸው፤
 መላእክትስ አንድ ናቸው።
   ብዬ ብዙ ስደናገር፤
   ሳላናግር ስግደረደር።
  ንፋስ መጥቶ አበነናት፤
  እፉዬ ነች በቃ አወኳት፤
ስትዞር ውላ የማይደክማት፤
  ንፋስ ወስዶ እንዳራቃት፤ 
   ማረፊያዋን ካላገኘች
     እየገፋ ከመለሳት፤
ተስፋ አልቆርጥም.........
..................ልጠብቃት።
 
@abela_black

@yegetemkalat
@poem_merry