Get Mystery Box with random crypto!

ጥበበኛዋ ትል አንዲት ትል ከአንድ ራጅም ዛፍ ስር ሆና ወደ ላይ ስትመለከት ዛፉ በማፍራት ላይ ያ | እግር ኳስ Meme™

ጥበበኛዋ ትል

አንዲት ትል ከአንድ ራጅም ዛፍ ስር ሆና ወደ ላይ ስትመለከት ዛፉ በማፍራት ላይ ያለውን ፍሬዎች በመመልከቷ ከፍሬው ለመመገብ ወደ ዛፉ ላይ የመውጣትን ጉዞ ጀመረች፡፡ በእሷ ፍጥነት (ዝግመት) ዛፉን ወጥታ ያሰበችበት ለመድረስ ረዘም ያለ ጊዜ እንደሚፈጅ ከተሞክሮ ብታውቀውም በጣም የምትወደውን ዜማ እያንጎራጎረችና ወደላይ በወጣች ቁጥር በበለጠ ሁኔታ እየታያት የመጣውን የአካባቢ ገጽታ እያየች በደስታ ዳገቱን ተያያዘችው፡፡

ብዙም ሳትርቅ ከዛፉ ላይ ወደታች የምትወርድ አንዲት ምንነቷ በውል ያልታወቀ እንስሳ ቆም ብላ፣ “ወደየት ነው እንደዚህ በደስታ እየተፍለቀለቅሽ የምትሄጂው አለቻት”፡፡ ትል፣ “ዛፉ ጫፍ ላይ ያለውን ፍሬ ልበላ” አለች፡፡ እንስሳዋም፣ “በቅድሚያ እኔ ከዚያ ነው የመጣሁት፣ ፍሬዎቹ ገና አልበሰሉምና አትልፊ፡፡ ሲቀጥል ደግሞ አጉል ደስተኛነትና አዎንታዊነት አያጥቃሽ ጉዞው ቀላል እንዳይመስልሽ፣ ስለዚህ ብትመለሺ ይሻልሻል” አለቻት፡፡

ትሏም፣ ቆም ብላ እዚያ ለመድረስ የሚፈጅባትን ጊዜ ካሰላች በኋላ፣ “ችግር የለውም፣ እዚያ እስከምደርስ ድረስ ፍሬዎቹ ይበስላሉ” በማለት ጉዞዋን ቀጠለች፡፡

ያሰብከው ከፍታ ለመድረስና የለፋህበትን ፍሬ ለማግኘት . . .

1. ዓላማህን ከጊዜ አጣጥመህ እቅድ አውጣ

ከሁሉ በፊት ለመድረስ የምትፈልግበትን የዓላማ ከፍታ ወስን፡፡ ከዚያም፣ እዚያ ዓላማህ ጋር ለመድረስ የሚፈጅብህን የጊዜ ሁኔታ አስላና ሁለ-ገብ እቅድ አውጣ፡፡ ሁለ-ገብ እቅድ ማለት፣ እንደ አንተ ሁኔታ ገንዘብን፣ ትምህርትን፣ እድሜን . . . ያካተተ ሊሆን ይችላል፡፡  

2. የሰዎችን ሃሳብ ማመዛዘን

ሁል ጊዜ ከፍ ያለ እቅድ ስታወጣና መንቀሳቀስ ስትጀምር ተቃራኒውን የሚነግሩህ ሰዎች እንደሚያጋጥሙህ አትርሳ፡፡ አንዳንዶች ለአንተ አስበው በቅንነት፣ ሌሎቹ ደግሞ በአንተ ላይ አስበው በምቀኝነት፡፡ በጭፍንነት ከሰማሃቸው ውጤቱ ው ስለሆነ ሁለቱንም ቢሆን በጥንቃቄ ማስተናገድ አስፈላጊ ነው፡፡

3. በጉዞው መደሰት
ወደ ዓላማህ በአንተ አቅምና ፍጥነት ስትጓዝ ፍጻሜው ላይ የመድረስን ደስታ እስከምታገኝ አትደበር፡፡ የጉዞ ደስታ የሚባልም ነገር እንዳለ አስብ፡፡ የመድረስ ደስታ ዓላማህ ላይ እስከምትደርስ ድረስ ያስጠብቅሃል፡፡ የጉዞው ደስታ ደግሞ አሁኑኑ በመደሰት ለጉዞው ጉልበትን ይሰጥሃል፡፡ በማንኛውም ጉዞህ ውስጥ “የምታዜመውን ዜማ” ፈልግ፣ የምትስቅበትን ምክንያት ፍጠር፣ ዙሪያህን እየቃኘህ ተደሰት፡፡ ጉዞው የፍጻሜውን ያህል አስፈላጊ ነውና፡፡

ያሰብከው ደረጃ መድረስህና ፍሬህን መብላትህ አይቀርምና፣ በፍጹም እንዳትቆም!!!

ሀሳብ አስተያየት @buchula36

@yegetemkalat
@poem_merry