Get Mystery Box with random crypto!

የመኖሬ ትርጉም ቅኔው ሲጠፋብኝ የህይወቴ መፅሐፍ ገፁ ሲምታታብኝ የኔነቴ ዋጋ ባዶ ሲሆንብኝ የኃጢአ | ETHIOPIAN ORTHODOX TEWAHIDO

የመኖሬ ትርጉም ቅኔው ሲጠፋብኝ
የህይወቴ መፅሐፍ ገፁ ሲምታታብኝ
የኔነቴ ዋጋ ባዶ ሲሆንብኝ
የኃጢአት ሐረግ ሲንጠላጠልብኝ
ሙቼ መራመዴ ለኔ ሲታወቀኝ
ምን ይውጠኝ ነበር አንቺ ባትኖሪልኝ

አልቅሼ ስነግርሽ አለሁሽ ባትዪኝ
የመዳንን መድህን ልዑል ባትወልጂልኝ
በምልጃ ፀሎትሽ ቤቴ ባይሞላልኝ
በይቅር ባይነትሽ ኑሮ ባይቀናልኝ
ማን ያስበኝ ነበር አንቺ ባታስቢኝ

ኃጢአት ተፀይፈሽ ፊት ያላዞርሽብኝ
ብርሀንን ወልደሽ ፀሀይ የሆንሽልኝ
ለውለታሽ ገላጭ ምንም ቃላት የለኝ
አማላጇ እናቴ ሁሌም ክበሪልኝ
ድንግል እመቤቴ ከፍ ከፍ በይልኝ።
https://t.me/ortodoksawimezmur