Get Mystery Box with random crypto!

ትንቢተ ዮናስ ምዕራፍ 2 ዮናስን እንዲውጥ ሕይወቱን ሳይጎዳ አንድ ትልቅ አሳ እግዜር አ | ETHIOPIAN ORTHODOX TEWAHIDO

ትንቢተ ዮናስ

ምዕራፍ 2

ዮናስን እንዲውጥ ሕይወቱን ሳይጎዳ
አንድ ትልቅ አሳ እግዜር አሰናዳ
ዮናስም ተውጦ በእግዚአብሔር ፍቃድ
ሦስት ቀን ሦስት ሌሊት ሲያድር በአሳ ሆድ
ተቀይመህ ኖሮ ከላይ ብተቆጣ
ይህን ያህል መዓት በራሴ ላይ መጣ
የባህሩ ሞገድ እኔን አዋከበኝ
ውሀና ጨለማ ሲኦልም ከበበኝ
አያለ በአሳ ሆድ ዮናስ ሲቀመጥ
አምላኩን ለመነው በመለማመጥ
የታዛዥነትም ጠባይ እያሳየ
አዝኖ ተጸጽቶ ከልቡ ጸለየ
ምን ጊዜመ ቢቆጣ ነው እና መሓሪ
ፊቱን መልሶለት ታረቀው ፈጣሪ
አሳውም ዮናስን ውጦ ሳያስቀረው
ከባህር ተፋና መሬት ወረወረው

ምዕራፍ 3

ይህንን የእኔን ቃል ስማና በቶሎ
ሄደ ለነነዌ እንድትነግራ ብሎ
ደገመና እግዚአብሄር ዮናስን አዘዘ
ነነዌ ሊገባ ዮናስ ተጓዘ
ድምጹን ከፍ አድርጎ ነብዩ ዮናስ
" ከዛሬ ጀምሮ አርባ ቀን ድረስ
ነነዌ ጠፊ ነች ከሥር ተገልብጣ "
አለና ለፈፈ የእግዚአብሔርን ቁጣ
ሳያንገራግሩ ሁሉም ስላመኑ
የነነዌ ሰዎች ተጨነቀው አዘኑ
ከትልቅ ጀምሮ ህጻኑ ድረስ
ሕይወቱ የቆመች በስጋ በነፍስ
ሰውም ሆነ እንስሳ ይቀበል ንስሓ
ፍጡር ሁሉ ይጹም ይለይ ከእህል ውኃ
ሁሉም ከልብ አዝኖ ማቅ እየለበሰ
ከክፉ ወደ ደግ እየተመለሰ
መቼም ወሰን የለው እግዚአብሔር ምሕረቱ
ይጸልይ አለና ይለምን በብርቱ
ንጉሡ አሳወጀ ከነመኳንንቱ
የነነዌ ሰዎች በውነት ከልቦና
መጸጸታቸውን እግዚአብሔር አየና
ፍጡር ቢለምነው እንባ እያፈሰሰ
ምህረቱን አውርዶ መዓቱን መለሰ

ምዕራፍ 3 ይቀጥላል