Get Mystery Box with random crypto!

ምንም ሳትበድል ሃጥያት ሳይኖርባት አንድዬ ልጇን ሄሮድስ ሊገድልባት ሀገር እንደሌለው ከሀገር ሲያሳ | ETHIOPIAN ORTHODOX TEWAHIDO

ምንም ሳትበድል ሃጥያት ሳይኖርባት
አንድዬ ልጇን ሄሮድስ ሊገድልባት
ሀገር እንደሌለው ከሀገር ሲያሳድዳት
ምን በድላው ይሆን ምን ሃጥያት ኖሮባት
የአዳም መዳኛ ድንግል ማርያም
አንድ ልጇን ይዛ ዞረች በዓለም
ሄሮድስ ምቀኛ የዲያቢሎስ ወዳጅ
ሊገድለው አስቦ የድንግልን ልጅ
መቼ ለእርሷ አዘነ ጨከነባት እንጂ
ስትሆን ለፍጥረት ለዓለም አማላጅ
የሲና በረሃ እግሯን እየፈጀው
አንጀቷ ተራበ ውሃ ጥም ሲፈጀው
መቼ ለእርሷ አዘነች የእርሷ መንገላታት
ህሳቧ ለእርሱ ነው እንዳይገድሉባት
አቤት መከራሽ አቤት ስደትሽ
እኔም ልካፈለው ወራዳው ልጅሽ
መሰደድ ያለብኝ እኔ ነበርኩ እንጂ
የሰይጣንን ስራ የተካፈልኩት...