Get Mystery Box with random crypto!

(4) ሚስቴ በየቀኑ ለሥራ ከቤት ስወጣ የረሳሁትን ነገር ታስታዉሰኛለች። አንዳንዴ የመኪና ቁልፍ፣ | Nuiman Edris Official

(4)

ሚስቴ በየቀኑ ለሥራ ከቤት ስወጣ የረሳሁትን ነገር ታስታዉሰኛለች። አንዳንዴ የመኪና ቁልፍ፣ ሌላ ጊዜ መነጽር፣ አንዳንዴም ሞባይል፣ እንዲሁም ሌላ ነገር መርሳት ልማዴ ነው።
"አሁንማ አረጀህ" እኮ አበቃህ ወይኔ ባሌ!" እያለች እየሳቀችብኝ ታቀብለኛለች የረሳሁትን።

ተረቧን ለማስቀረት የሆነ ዘዴ ዘየድኩ። የምረሳቸዉን ነገር በወረቀት ላይ መዝግቤ ያዝኩ። የሆነ ቀን ጠዋት ከመውጣቴ በፊት ወረቀቴን አውጥቼ ሁሉንም መያዜን አረጋገጥኩ።

ከዚያም በድል አድራጊነት ስሜት መኪናዬ ዉስጥ ገብቼ ሞተር አስነስቼ ግቢዬን ለቅቄ ወጣሁ።
ትንሽ እንደነዳሁ ደወለች። ባለቤቴ። ክው አልኩ፣ ዛሬ ደግሞ ምን ረሳሁ ብዬ ...
"ሄሎ" አልኳት።
" ዛሬ ደግሞ የት እየሄድክ ነው?" አለችኝ።
"ሥራ ነዋ"
" እሁድ እኮ ነው፣ የምን ሥራ!።"
ትንሽ ቆሜ ፈገግ እያልኩ ወደቤት ተመለስኩ።

የሰው ልጅ ጎዶሎ ነው የተሟላ አይደለም፣ ፍፁምነት ለአላህ ብቻ ነው።
ባልና ሚስት፣ ወንድና ሴት ... በሀሳብም በአካልም እንዲሞላሉ ተደርገው ነው ጀሊሉ የፈጠራቸው። አንዱ የጎደለው ሌላው አለው። አንዱ የማይችለዉን ሌላው ይችለዋል ፣ ለአንዱ የማይታየው ለሌላው ይታየዋል።

ለመናናቅ፣ ለመገፋፋትና ለመለካካት ሳይሆን ዱንያን አብረን እንድንኖር፣ ፈተናዎቿንም አብረን እያሸነፍን ወደ ጀነት እንድንጓዝ ነው አላህ ወደዚህች ምድር ያመጣን።

አራተኛው ህግ
አንዱ የሌላኛዉን ሀሳብ ጆሮ ሰጥቶ ያድምጥ፣ አይናናቅ፣ አያጣጥል።

telegram.me/Nuiman_9