Get Mystery Box with random crypto!

'ዳዒም ተፈቀርኩ' (ኑዕማን ኢድሪስ) የኔ ነቢ፤ የኔ ራህመት አደረሰኝ አመት ካ'መት የኔ ረ | Nuiman Edris Official

'ዳዒም ተፈቀርኩ'
(ኑዕማን ኢድሪስ)

የኔ ነቢ፤ የኔ ራህመት
አደረሰኝ አመት ካ'መት

የኔ ረሱል፤ ሸፈዓዬ
ድርብ ሆነ ያ ደስታዬ

የኔ ሀቢቢ፤ ያ ሙስጠፋ
ሽርኩ ሁሉ ባንቱ ጠፋ

ባንቱ'ኮ ነዉ ሰዉ የሆንኩት
የኔን ጌታ አላህዬን ያመለኩት

ባንቱ'ኮ ነዉ ፤ ሴቱ ወንዱ
ለጀሊሉ ዳኢም መስገዱ

ያ ኻሊቅ...
የኔ አምላክ አላህ፤
ምንኛ ወዶኛል

የኑህን የሙሳን የሉጥን የኢሳን፤
የነሱን ጊዜ አልፎ ኡመቶ እንድሆን ከኃላሁ ፈጥሮኛል

ምንኛ እድለኛ ፤ ጀሊሉ አድርጎኛል
በወዱ ነቢ ልብ እኔን አስናፍቆኛል

ሀቢቢ...
እኛን ናፍቀሁ አንቱ፤ አፈር እንደጫርኩ
ይሄዉ በኔ ልብም፤ ዳኢም ተፈቀርኩ !

በቴሌግራም - telegram.me/Nuiman_9