Get Mystery Box with random crypto!

ለአራት ቀናት ብቻ ለሞተው አልዓዛር ያለቀሰ ጌታ ለዘመናት በኃጢአት ለሞትን ለእኛ ምንኛ ያለቅስ ይ | የተዋህዶ ፍሬዎች

ለአራት ቀናት ብቻ ለሞተው አልዓዛር ያለቀሰ ጌታ ለዘመናት በኃጢአት ለሞትን ለእኛ ምንኛ ያለቅስ ይሆን? ሰውነታች በበደል ለረከሰ ፣ በምኞት መቃብር ለተቀበርን ፣ በዝሙት ለተበላሸን ፣ በጥላቻ ለሸተትን ለእኛ ክርስቶስ ምንኛ ያለቅስ ይሆን? የኃጢአት ድንጋይ ተጭኖን ፣ የፍትወት መግነዝ ተጠምጥሞብን ላለን ለእኛ የጌታ ዕንባ ምን ያህል ይፈስስልን ይሆን? አልዓዛርስ ውጣ ቢባል ይወጣል ፣ ካለንበት ኃጢአት መቃብር መውጣት ለማንፈልግ ለእኛ ጌታ እንደምን ያለቅስ ይሆን? የእኛ ሞት ከአልዓዛር ሞት በላይ ዘልቆ የማይሰማው ይመስላችኋል? እንዴት አይሰማውም? ለአልዓዛር ዕንባውን ያፈሰሰው ጌታ ለእኛ እኮ ያፈሰሰው ደሙን ነው ።

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

#ሼር
#share
https://t.me/joinchat/AAAAAFSJ49GBC3YRZoSNHQ