Get Mystery Box with random crypto!

ኪዳነምህረት እመቤት /2/ ነይልን ነይልን ካለንበት /2/ እዝ...... ከሰማያት በላይ ካለው ከማ | የተዋህዶ ፍሬዎች

ኪዳነምህረት እመቤት /2/
ነይልን ነይልን ካለንበት /2/
እዝ......
ከሰማያት በላይ ካለው ከማደርያሽ /2/
ዝማሬ ከሞልው ከዘላለም ቤትሽ
የምድር ፍጥረታት ማርያም ማርያም ሲሉሽ
የቃል እናት እመቤቴ ነይ በሰረገላ /2/
እዝ............
ከፀጥታ ወደብ ከፍቅር አውድማ /2/
ከሰላሙን መንደር ከእውነት ከተማ
ሳሊለነ ቅድስት ውዳሴሽ ሲሰማ /2/
ከሚካኤል ከገብርኤል ጋር ነይልን ከራማ /2/
እዝ...............
ዘርፋፋው ቀሚስሽ ይወረደ ከሰማያት /2/
እንባችን ይታበስ በአንቺ አማላጅነት
የፅዮን ዝማሬ ተሞላች ነፍሳችን /2/
ነይ ነይ ነይ እንበል እንደአባቶቻችን /2/
እዝ...................
ፍጥረታት ቢድኑ በአማላጅነትሽ /2/
የዘላለም ኪዳን አማኑኤል ሰጠሽ
ትውልድ ይህን አምኖ ንፅህት ይልሻል /2/
እናቴ መመክያዬ ምርኩዜ ሆነሻል/2/
እዝ................
የልብን ሲያዋዩሽ ሰምተሽ ዝም አትይም /2/
ችግረኛን አይቶ ልብሽ አይጨክንም
ከአይን ጥቅሻ ፈጥነሽ ትደርሽለታለሽ /2/
ከሀዘን ከመከራ ታሳሪፊዋለሽ /2/