Get Mystery Box with random crypto!

በአዲስ አበባ ቅርጫ ተከልክሏል የሚባለው ሃሰት ነው አልተከለከለም! በአዲስ አበባ ከተማ በዘንድሮ | Natnael Mekonnen

በአዲስ አበባ ቅርጫ ተከልክሏል የሚባለው ሃሰት ነው አልተከለከለም!

በአዲስ አበባ ከተማ በዘንድሮዉ ዓመት የሚከበረዉን የትንሳኤ በአል አስመልክቶ ህብረተሰቡ በየቤቱ በእርድ መልክ የሚጠቀመዉን እና በየአካባቢዉ የቁም እንስሳትን ቅርጫ በማረድ የሚከፋፈለዉን ተከልክሏል በሚል በማህበራዊ ሚዲያዉ ሀሰተኛ መረጃ እየተሰራጨ ይገኛል።

በመሆኑም ከዚህ ጋር በተያያዘ ምንም አይነት ክልከላ ያልተደረገ ሲሆን በየአካባቢዉ በህገ ወጥ መንገድ እርድ በመፈፀም ለሆቴሎች እና ለስጋ ቤቶች በማከፋፈል ተግባር ላይ የሚገኙ አካላት የቁም እንስሳቱ ጤንነት ባልተረጋገጠበት ሁኔታ የከተማዉን ነዋሪ ጤንነት ላይ ጉዳት የሚያደርስ በመሆኑ ጥብቅ ቁጥጥር ይደረጋል።

የከተማችን ነዋሪ በአላትን ሽፋን በማድረግ ጤንነቱ ያልተረጋገጠ እንስሳት አርዶ ማከፋፈል በጤና ላይ የሚያደርሰዉን ጉዳት ግምት ዉስጥ በማስገባት በህገወጥ እርድ የሚሰማሩ አካላት በሚደረገዉ ቁጥጥር ተባባሪ እንዲሆን መልክታችንን እናስተላልፋለን።