Get Mystery Box with random crypto!

“ በየጊዜው ወጣቶች የምገብርበት የጦርነት ምዕራፍ መዘጋት አለበት “ - አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራ | Natnael Mekonnen

“ በየጊዜው ወጣቶች የምገብርበት የጦርነት ምዕራፍ መዘጋት አለበት “ - አቶ ጌታቸው ረዳ

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ በኩል ዛሬ መልዕክት አሰራጭተው ነበር።

በዚህም ፤ “ የህዝባችን ሁለንተናዊ መብትና ጥቅም ከማረጋገጥና አስተማማኝ ከማድረግ የሚቀድም ሌላ አጀንዳ የለንም “ ብለዋል።

“ የህዝባችን ጥቅምና መብት የሚያረጋግጥ መንገድ ሁሉ እንጓዘዋለን “ ያሉት አቶ ጌታቸው “ ጉዞው እንዲሳካ የህዝቡ ተሳትፎ ወሳኝ ነው “ ሲሉ አክለዋል።

ፕሬዜዳንቱ ፤ “ ከሚገባው በላይ ያበረከተ ህዝብ በቅንነትና ታማኝነት ማገለገል ይገባል “ ሲሉም ገልጸዋል።

“ ህዝቡ ከጦርነትና ጦርነት ወለድ ችግሮች በማላቀቅ ወደ አስተማማኝ ሰላም እንዲሸጋገር መስራት ይገባል “ ሲሉም አስገንዝበዋል።

አቶ ጌታቸው ረዳ ፤ “ በየጊዜው ትኩስ ሃይል የሆኑትን ወጣቶች የምንገብርበት የጦርነት ምዕራፍ ተዘግቶ ፤ የልማትና የእድገት ፍላጎታችን እንዲሳካ መስራት አለብን “ ብለዋል።