Get Mystery Box with random crypto!

አንድ የውጪ ሃገር ዜግነት ባለው ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ በተደረገ ብርበራ ከ5 ሺህ በላይ የአሜ | Natnael Mekonnen

አንድ የውጪ ሃገር ዜግነት ባለው ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ በተደረገ ብርበራ ከ5 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላር እና የተለያዩ አገራት ገንዘቦች መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።
በብርበራው ከ71 ሺህ ብር በላይ የኢትዮጵያ ብር መያዙንም ነው ያስታወቀው።
ግለሰቡ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ቦታው 24 ኮንዶሚኒየም ጀርባ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ባለ 3 ወለል ፎቅ ተከራይቶ የሚኖር መሆኑን ገልጿል።
 
ተጠርጣሪው ግለሰብ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ የውጭ አገር ዜጎችን እየተቀበለ በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ የተለያዩ ህገ ወጥ ተግባራትን ሲፈጽም እንደነበር ከህብረተሰቡ ጥቆማ ማግኘቱንም ነው የገለጸው።
ጥቆማውን መነሻ በማድረግ የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት ተቀናጅተው ባደረጉት ክትትል ግንቦት 4 ቀን 2014 ዓ.ም በግለሰቡ መኖሪያ ቤት በተደረገ ፍተሻ በመኝታ ክፍል ውስጥ የተገኘ 5 ሺህ 335 የአሜሪካ ዶላር፣ 380 ዩሮ፣ 1 ሺህ 435 የቻይና የን እና ሌሎች የተለያዩ ሃገራት ገንዘቦችን ጨምሮ 71 ሺህ 635 የኢትዮጵያ ብር መያዙን ከአዲስ አበባ ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡