Get Mystery Box with random crypto!

STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

የሰርጥ አድራሻ: @nationalexamsresult
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 40.95K
የሰርጥ መግለጫ

የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-07-24 14:07:42
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ2015 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ያሉበትን ሁኔታ ተመለከቱ ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋና ሚኒስትር ዴኤታው ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ዋናው ግቢና በ4 ኪሎ ሳይንስ ፋካሊቲ ተገኝተው የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና  ተፈታኝ ተማሪዎችን አበረታተዋል።

በዩኒቨርሲቲዎቹ ያለውን የተማሪ አቀባበል፣የመኝታና የመመገቢያ ቦታዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በምልከታቸውም ተፈታኝ ተማሪዎች ተረጋግተው ፈተናቸውን እንዲሰሩ ሚኒስትሩ አበረታተዋል ።

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሀምሌ 19 /2015 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ ይታወቃል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
8.8K views11:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-24 12:09:56
ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የ2015 ዓ.ም የተማሪዎች የምረቃ ሥነ ስርዓት ተሰርዘ

በክልሉ ባለ የፀጥታ ችግር ምክንያት የ2015 ዓ.ም የተማሪዎች የምረቃ በዓል መሰረዙን የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል።

የምረቃ በዓሉን ሐምሌ 13/2015 ዓ.ም ለማድረግ ቀጠሮ ተይዞ የነበረ ቢሆንም በክልሉ በተከሰተው የፀጥታ መደፍረስ ምክንያት የምረቃ ፕሮግራሙ መሰረዙን የተቋሙ የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዝዳንት ከተማ ጥላሁን (ዶ/ር) ገልፀዋል።

"ተማሪዎቻችንን ለማስመረቅ ተዘጋጅተን ነበር፤ ይሁን እንጂ ሰው እየሞተ የምረቃ በዓል ማድረግ ትርጉም አይኖረውም" ብለዋል ምክትል ፕሬዝዳንቱ።

የተቋሙ አንድ ተማሪ እና አንድ መምህር ህይወታቸው ማለፉን የገለጹት ዶ/ር ከተማ፤ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ የምረቃ በዓሉን ማከናወን እንዳልተቻለ ጠቁመዋል።

659 የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎች እና ሁለት የሁለተኛ ዲግሪ ተመራቂዎች ትምህርታቸውን ማጠናቀቃቸው ተገልጿል።

ተመራቂዎቹ አሁን ላይ ጊዚያዊ ዲግሪ (Temporary) እየተሰጣቸው መሆኑን ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ዩኒቨርሲቲው የተመደቡለትን ከ6 ሺህ በላይ የማህበራዊ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞችን ከትላንት ጀምሮ እየተቀበለ ይገኛል።

ትምህርታችሁን ላጠናቀቃችሁ የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች እንኳን ደስ አላችሁ

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
8.8K views09:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-24 11:31:22
ወልድያ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያው ዙር የ12ተኛ ክፍል የ2015 ዓ.ም ተፈታኝ ተማሪዎችን እየተቀበለ ነው።

መንግስት የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅና ከስርቆት ነጻ የሆነ ፈተና ለመስጠት የ12 ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ከየሚማሩበት ትምህርት ቤት ወጣ ብሎ በመንግስት የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ መሰጠት ከጀመረ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው።

የወልድያ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡለትን የመጀመሪያው ዙር የ12ተኛ ክፍል የሶሻል ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎችን በመቀበል ላይ ይገኛል።

የቅበላ ሂደቱም ከዛሬ የሚጠናቀቅ ይሆናል።

ሐምሌ18/2015 ዓ.ም አጠቃላይ ስለፈተናው ሁኔታ ለተማሪዎች ኦሬንቴሽን ተሰጥቶ ከሐምሌ 19 እስከ 21/2015 ዓ.ም የመጀመሪያው ዙር የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተናቸውን እንደሚወስዱ ይጠበቃል።

ዉድ ተማሪዎቻችን እንኳን ወደ ውቢቷ ወልድያ ከተማና ዩኒቨርሲቲ በሰላም መጣችሁ በማለት ዩኒቨርሲቲው መልካም ዕድል ተመኝቷል።

#አሚኮ

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
8.7K viewsedited  08:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-24 08:19:08
በቅድሚያ ለ 2015 ዓ/ም ተመራቂ ተማሪዎች እንኳን ደስ አላቹ እያልን ለተመራቂዎች ፣ ለልደት ፣ ለ Anniversary እና ለማንኛውም ዝግጅት  ምርጥ ስጦታ ከዚህ በፊት ያልተለመደ ማንኛውንም አይነት ፎቶ ወይም ምስል ባማረ ሁኔታ እንጨት ላይ በ#MDF Colour ስራዎቻችን  በተመጣጣኝ ዋጋ በሚፈልጉት Size ለወዳጅ ዘመድዎ ያበርክቱ 


ይዘዙን ያሉበት ቦታ በነፃ  እናደርሳለን!

Contact:   @Henak_21
                  0924848164

#For_More_Gifts_Package
@Habesha_Gift
9.5K views05:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-23 18:17:06
የሚያጠቡ ተፈታኞች ሞግዚት ይዘው እንዲገቡ ተፈቀደ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚወስዱ የሚያጠቡ ተፈታኞች አንድ ሴት ሞግዚት ይዘው እንዲገቡ መፈቀዱን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ፡፡

መውለጃ ወራቸው የደረሰ ነፍሰ ጡር እና ጡት የሚያጠቡ ተፈታኞች በሚቀጥለው ዓመት ተዘጋጅተው እንደ መደበኛ ተፈታኝ ቢፈተኑ እንደሚመከር አገልግሎቱ አስገንዝቧል፡፡

ይሁን እንጅ ለመፈተን የወሰኑ ከሆነ÷ ጡት የሚያጠቡት ተፈታኞች አንድ ሴት ሞግዚት ይዘው በመግባት እንዲፈተኑ ተገቢው ድጋፍ ይደረግላቸዋል መባሉን የአገልግሎቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

የተፈታኞች መብትና ግዴታ እንዲሁም የተከለከሉ ነገሮች በተመለከተም÷ በተፈታኟና በሞግዚቷ ላይ ተግባራዊ እንደሚደረጉ ነው አገልግሎቱ ያሳሰበው፡

Fana Broadcasting corporate

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
10.7K viewsedited  15:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-23 18:15:23
የዩኒቨርሲቲዎቻችን የዘንድሮ የክብር ዶክትሬት አሰጣጥ በእግርጥም ይህን ያስብላል

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
9.9K views15:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-23 17:19:24 ማስታወሻ

የተፈታኝ ተማሪዎች መብቶች፦

➭ ከፈተና ጥያቄ ውጪ ማንኛውንም ያልተረዳውን ነገር ጠይቆ የመረዳት መብት አላቸው።

➭ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ የምግብ፣ የህክምና አገልግሎት፣ የማደሪያ ክፍል፣ ፍራሽ እና ትራስ የማግኘት መብት አላቸው።

➭ ማንኛውም ተፈታኝ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ያለውን የቤተ መፅሐፍት፣ የመጸዳጃ ቤቶች፣ የሻወር፣ የካፍቴሪያዎች፣ የሚኒ ሱፐር ማርኬቶች፣ የተለያዩ ሱቆች እንዲሁም የመናፈሻና መዝናኛ አገልግሎቶችን የመጠቀም መብት አላቸው።

➭ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ የጋራ የደህንነት ጥበቃ የማግኘት መብት አላቸው።

➭ በፈተና ሰዓት መፈተኛ ክፍል ገብቶ ብርሃናማ የመፈተኛ ቦታ፣ ወንበርና መፃፊያ ጠረጴዛ የማግኘት መብት አላቸው።

➭ ፈተና ከመጀመሩ አንድ ቀን ቀድሞ ስለፈተናው ገለጻ (ኦሬንቴሽን) የማግኘት መብት አላቸው።

የተፈታኝ ተማሪዎች ግዴታዎች፡-

➤ ማንኛውም ተፈታኝ በፈተና ማዕከልና መፈተኛ ክፍል አድሚሽን ካርድ ይዞ የመገኘት ግዴታ አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲመጣ የትምህርት ቤት ወይም የነዋሪነት መታወቂያ ይዞ መገኘት አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ግቢ ከመግባቱ በፊትና ወደ መፈተኛ ክፍል ከመግባቱ በፊት ሙሉ አካላዊ ፍተሻ የመፈተሽ ግዴታ አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ በዩኒቨርሲቲ ግቢና በመፈተኛ ክፍል የተከለከሉ ዕቃዎችን መያዝ የለበትም።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ እርሳስ፣ ላጲስና የእርሳስ መቅረጫ ይዞ መገኘት አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ የፈተና ደንብን የማክበር ግዴታ አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ በፈተና ማዕከል/በመፈተኛ ክፍል ውስጥ የፈተና አስፈጻሚዎች የፈተና አስተዳደር ሥራን ውጤታማ ለማድረግና ሁኔታዎችን ለማመቻቸት የሚያደርጉትን ጥረት የመተባበር ግዴታ አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ ፈተና ከመጀመሩ በፊት መፈተኛ ክፍል የመገኘት ግዴታ አለበት።

➤ ተፈታኙ ፈተናው ሳይጠናቀቅ ከፈተና ክፍል የሚወጣ ከሆነ የፈተና ጥያቄ የያዘውን ቡኩሌት ለፈታኙ የማሰረከብ ግዴታ አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ ወደተመደበበት ዩኒቨርሲቲ ሲመጣ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የትራስ ጨርቅ ይዞ የመምጣት ግዴታ አለበት።

ለተፈታኝ ተማሪዎች የተፈቀዱ ነገሮች፦

➣ አዲስ ወይም ቀድሞ ለመማር እና ለማጥናት ሲጠቀሙበት የነበሩ ማስተወሻ ደብተር፣ የትምህርት መፅሐፍ፣ መንፈሳዊ/ኃይማኖታዊ መፅሐፍት፣ ባዶ ወረቀት

➣ ደረቅ ምግቦች (ጩኮ፣ በሶ፣ ዳቦ ቆሎ፣ ቆሎ….)

➣ ገንዘብ (ብር)

➣ የልብስ ወይም የእጅ ቦርሳ፣ የግል ልብስ፣ ጫማ

➣ የግል ንጽህና መጠበቂያዎች (ሳሙና፣ ሞዴስ፣ የጥርስ ብሩሽ፣ የጥርስ ሳሙና፣ ፎጣ፣ ሶፍት፣ ሻምፖ፣ ኮንዲሽነር፣ ሎሽን፣ ቻፕስቲክ፣ የጸጉር ቅባት፣ የፊት ቅባት)

ለተፈታኝ ተማሪዎች የተከለከሉ ነገሮች፦

➣ ማንኛውንም ዓይነት የጦር መሣሪያ ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው፡፡

➣ ማንኛውንም ዓይነት ስለት እና ሹልነት ያላቸውን ብረታ ብረቶችና ጠንካራ ፕላስትኮች ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው።

➣ ማንኛውም ድምጽ የሚቀዳ፣ ፎቶ የሚያነሳ፣ ቪዲዮ የሚቀርጽ፣ ከቴሌ መስመርም ሆነ ከቴሌ መስመር ውጭ መልዕክት በዲጂታል መንገድ የሚሰጥ ወይም የሚቀበል የግል ዕቃ/መሳሪያ/የቴክኖሎጂ ውጤት፣ ስልክ፣ አይ-ፓድ፣ ታብሌት፣ ኮምፕዩተር፣ ላፕቶፕ፣ ስማርት ሰዓት፣ ማጂክ ብዕር/እስክሪብቶ፣ ማጂክ ኮት/ጃኬት እና ሌሎች ማንኛቸውም ፎቶ፣ ምስል እና ድምጽ የሚቀርጹ የኤሌክትሮኖክስ መሣሪያዎችን በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥም ሆነ ግቢ ዙሪያ ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡

➣ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ማንኛውንም ዓይነት የግል ፍላሽ ዲስክ፣ ሃርድ ዲስክ፣ ሲዲ፣ ሚሞሪ፣ ሚሞሪ ሪደር፣ ኦ-ቲጂ ኮንቨርተርና መሰል ዕቃዎችን ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡

➣ ማንኛውም አደንዛዥ እጾች (ጫት፣ ሲጋራ፣ በሐኪም ማዘዣ የሌለው መድኃኒት)፣ ህክምና መስጫ መርፌ መያዝ ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡

➣ ማንኛውም ዓይነት የአልኮል መጠጥ ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡

➣ ማንኛውም ዓይነት የአንገት ሐብል፣ የጸጉር ጌጥ፣ የጆሮ ጌጥ፣ የጣት ቀለበት፣ የእጅ አንባር፣ አድርጎ ወይም ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው፡፡ (ከልሙጥ የጋብቻ ቀለበት በስተቀር)

➣ ፈተና ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በኋላ ወደ ፈተና ክፍል መግባት እና ፈተናው ተጀምሮ 45 ደቂቃ ሳይሞላ ከፈተና ክፍል መውጣት የተከለከለ ነው፡፡

➣ ተፈታኙ ፈተናው ሳይጠናቀቅ ከፈተና ክፍል የሚወጣ ከሆነ የፈተና ጥያቄ የያዘውን ቡኩሌት ይዞ መውጣት ተከለከለ ነው፡፡

➣ በፈተና ሰዓት በመፈተኛ ክፍል ውስጥ ማስቲካ መያዝም ሆነ መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡

➣ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ በግልም ሆነ በቡድን መጮህ ወይም በጣም ከፍተኛ ድምጽ ማሰማት የተከለከለ ነው።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
10.0K viewsedited  14:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-23 16:36:17
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን በሶስቱም ግቢዎቹ እየተቀበለ ይገኛል።

በ2015 ዓ.ም በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በዋናው ግቢ፣ በጤና ካምፓስ እና በቡሬ ካምፓስ ከ30 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ለመቀበል ያደረገውን ሰፊ ዝግጅት በማጠናቀቅ ተፈታኞቹን በመቀበል ላይ ይገኛል።

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
10.4K views13:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 22:42:43
አስቸኳይ ማስታወቂያ
ለሬሚዲያል ተማሪዎች በሙሉ

ብሔራዊ ፈተና ለሪሚዲያል ተማሪዎች ከ26/10/2015 ዓ.ም ጀምሮ መስጠት መጀመራችን ይታወቃል። ስለሆነም ለፍተሻ ይመች ዘንድ እስከ 7፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ሁሉም ተማሪ ወደ ተመደበባችሁበት መፈተኛ ክፍል እንድትሄዱ ለማሳሰብ እንወዳለን።

ማስታወሻ

ከተጠቀሰው ሰዓት ውጪ የመጣ ተማሪ ፈተናውን መፈተን እናደማይችል ከወዲሁ እናሳውቃለን።
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት የ1ኛ አመት ተማሪዎች ዲን     

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
4.0K viewsedited  19:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 19:57:44
*Competent research hub *
Hi Students , We are a team of Professional Academic Assistants with qualifications in in different fields. We handle tasks on
*Thesis and Dissertations*
*Research Proposals and Papers*  
*Essays*  
*Discussion tasks & Case Study*
*Online classes & Tests*
*Term Papers & Business Plans*
  *Creative Writing, Critical Analysis & Literature Review*

Over the years our clients have benefited from our quality services in addition to
*Timely Delivery*
*Unlimited revisions*
*Affordable Prices*
*Professional, Confidential and Authentic work.*

*We are accessible 24/7 on call, text and telegram through* 
Contact as via
@ResearcherETH
@ResearcherETH
@ResearcherETH
5.3K views16:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ