2024-05-08 10:41:04
የተለማማጅ ሰራተኛ የቅጥር ማስታወቂያየኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሥሩ ለሚገኙ የተለያዩ የሥራ ክፍሎች ተለማማጅ ሰራተኞችን /Internship/ ቀጥሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በዚሁም መሠረት ከዚህ በታቸው የተገለፁትን መስፈርቶች የምታሟሉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከዚህ በታች በተጠቀሰው የስራ ማመልከቻ ማስፈንጠሪያ በመንካት ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
በማኔጅመንት/ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን/ በአካውንቲንግና ፋይናንስ/ በኢኮኖሚክስ/ በማርኬቲንግ/ በሕግ/ በኮምፒውተር ሳይንስ/ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ወይም በሌላ ተመሳሳይ የትምህርት ዘርፍ የመጀመሪያ ዲግሪና 0 ዓመት የሥራ ልምድ
በቂ የመግባባት ችሎታ ያላት/ያለው
የተቋሙን ደንብና መመሪያ የምታከብር/ የሚያከብር
ማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነች/ያልሆነ፤
የቅጥር ሁኔታ፡ በጊዜያዊነት
የስራ ቦታ አዲስ አበባ፣ማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ሶማሌ እና ቤኒሻጉል
አመልካቾች ከዚህ በታች በተቀመጠው የስራ ማመልከቻ ማስፈንጠሪያ በመንካት ማመልከት ይችላሉ፡፡
https://pw.nebe-elections.org/internship
ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ።ማሳሰቢያ፡-
ለሶማሌ ክልል ላይ አመልካቾች የክልሉን ቋንቋ ማወቅ ይጠበቅባቸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
9.3K views07:41