2022-08-30 15:40:14
የተከበሩ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ዲያቆን ተስፋው ባታበል ወልዲያ በወገን ጦር እንጅ በጠላት አልተያዘችም !!
አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል በዞናችን በድጋሜ ወረራ ለመፈፀም ያለ የሌለ ኃይሉን አሰባስቦ ለሁለተኛ ጊዜ ጦርነት አውጆብናል።
ከትናንት ስህተቱ የማይማረው የትግራይ ወራሪ ኃይል መንግስት ያቀረበለትን የሰላም አማራጭ ወደ ጎን በመተው ለትግራይ ህዝብ ግድ የሌለው መሆኑን በተግባር አረጋግጧል።
ጦርነትን እንደ ዋነኛ ግብ ቆጥሮ፣ በሰው ደም ላይ የሚረማመደው የትህነግ አሸባሪ ቡድን ዛሬም ከትናንት ስህተቱ ሳይማር የጦር ነጋሪት ሲጎስም ከከረመ በኋላ ሀገር የማፍረስ አጀንዳ አንግቦ ወደ ጦርነት ገብቷል።
ሀገራችን ኢትዮጵያ በየዘመናቱ ከውስጥም ሆነ ከውጭ ጠላቶች ሲገጥሟት ኑሯል ።
ከጥንት ጀምሮ የገጠማትን የውሰጥና የውጭ ጠላቶችን አሸንፋ በድል እየተረማመደች የመጣች የጥቁር አፍሪካ ህዝቦች የነፃነት ፈርጥ መሆኗን የታሪክ ድርሳናት አስረግጠው ይመሰክራሉ።
ወራሪው የትግራይ ኃይል በመንግስት በኩል የቀረበለትን የሰላም አማራጭ አልቀበልም ብሎ ጦርነትን አማራጭ ያደረገው ለትግራይ ህዝብ አስቦ ሳይሆን የውጭ ኃይሎችን ጣልቃ ገብነት፣ የባንዳነት ተልዕኮውን ለማስፈፀም አበክሮ እየሰራ ስለመሆኑ አንዱ ማሳያ ነው።
ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው ሉኣላዊነትና አንድነት ላይ የማይደራደሩ፣ በደምና በአጥንታቸው አፅንተው ያቆሟትና ሀገር የመሠረቱ ያነፁ የእንቁ ልጆች ባለቤት ናት ። ዛሬም ቢሆን ከዚህ ከፍታዋና ክብሯ ማንም ዝቅ ሊያደርጋት አይችልም።
የሀገራችን ትናንት በደምና በአጥንት የቋሟት ጀግኖች ልጆች እንደነበሯት ሁሉ ዛሬም የሀገራቸውን ሉአላዊነትና አንድነት በደምና በአጥንታቸው የሚያፀኑ ጀግኖች ልጆች አሏት።
ወራሪው ኃይል በዞናችን ወረራ ሲፈፀም ትናንት ይጠቀምባቸው የነበሩ የሀሰት ቅስቀሳና ፕሮፖጋንዳዎች አሁንም ተጠናክሮ ህዝብን ለማደናገር በስፋት እየተሰራጨ ይገኛል።
ይህ የሽብር ቡዱኑ ፕሮፖጋንዳ በማህበራዊ ሚዲያ ተከፋይ አክቲቪስቶች ብቻ የሚተገበር ሳይሆን የፈጠራ ወሬዎችን በሚያራግቡ እና የጥላት ፕሮፖጋንዳ ከውሰጥ ሁነው በሚደግፉ ስዎች ጭምር የሚተገበር በመሆኑ ዛሬም እንደለመደው ወልዲያን ተቆጣጠርኩ እያለ ያራግባል ።
ስለዚህ ህብረተሰቡ ከእንደዚህ ዓይነት የሀሰተኛ መረጃዎች ራሱን ሊጠብቅና አጠራጣሪ መረጃዎችን ሲመለከት ለመንግስት የፀጥታ መዋቅር ጥቆማ መስጠት ይጠበቅበታል።
የዞናችን ህዝብ በወራሪው ኃይል የደረሰበት የሰብዓዊ፣ ስነ ልበናዊና ቁሳዊ ውድመት መንገር ለቀባሪ እንደማርዳት ይቆጠራ፤ የችግሩ ቀጥተኛ ተጠቂና ገፈት ቀማሽ ነው። ሰለሆነም ወራሪው ኃይል እንደ ሀገር ወረራ ሲፈፀም ዞናችን ቀጥተኛ የትግሉ ቦታ ላይ የሚገኝ በመሆኑ ከትናንት ችግሮች ትምህርት በመውሰድ ያለ የሌለ አቅማችን አሟጠን ከሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ከአማራ ልዪ ኃይልና ፋኖ ጋር ደጀን በመሆን አጋርነታችን እንደ ወትሮው አጠናክረን ልንቀጥል ይገባል።
ሰላማችን የሚረጋገጠው በአንድ ወገን ፍላጎት ብቻ አይደለም። መንግስት ለሰላም ያለውን ቁርጠኝነትና አማራጭ አሟጦ ተጠቅሟል። ለሰላም ሲባል ረጅም ርቀት በመንግስት በኩል የተወሰዱ አዎንታዊ እርምጃዎች የሚደነቁ ናቸው። ያም ሆኖ በጥላት የቀረበለትን የሰላም አማራጭ ወደ ጎን ብሎ በኩል ጦርነትን እንደ ብቸኛ አማራጭ ተጠቅሞ ዳግም ወረራ ከፍቷል።
ሰለሆነም የዞናችን ህዝብ የተቃጣብንን ወረራ የህልውና ጉዳይ በመሆኑ አያጠያይቅም። ትናንት ብዙ ትምህርት ወሰደናል፤ ዛሬ ለነፃነታችንና ለአንድነታችን ዘብ በመቆም ይጠበቅብናል።
የሰሜን ወሎ ዞን ኮሙኒኬሽን፣
ነሃሴ 24/2014 ዓ.ም
1.4K views12:40