2022-08-30 15:40:15
ዳር ላይ ያለች ትንሽ ከተማ ተያዘችም፣ ትልቅ ከተማ ተያዘም ክብራችን ተነክቷል። የቀበሌ፣ የወረዳ፣ የዞንና የክልል ከተማ ቢያዝ ከብዙ ፋይዳ አንፃር ሊታይ ይችላል። ክብር ግን የትኛም ላይ ተመሳሳይ ነው። ከራሱ ድንበር አንድ ኢንች ሲያልፍ ተወርረናል የሚል ስሜት መኖር አለበት። ትንሽ ከተማ ሲያዝ ምንም የማይመስለን፣ ትልቅ ሲያዝ እንቅልፍ የምናጣ መሆን የለብንም። ከሩቅ ያለቦታ ሲያዝ ግድ የለሽ ወደእኛ ሲቀርብ የምንሰጋ መሆን የለብንም።
ህወሓት ወያኔ የራሱን አልፎ ከመጣ ቆይቷል። አሁን የራሳችን ከተማ የምንቆጥርበት አካሄድ መቆም አለበት። ከወረረው እስካልወጣ ድረስ የትም ይሁን የት ህመሙ እኩል መሆን አለበት። የራሳችን ከተማ እየተወረረ ዛሬ ከዚህ ደርሷል፣ ነገ ከዚህ ይደርሳል እያልን መቁጠር ለውጥ አያመጣም። ከየትኛውም እንዲወጣ የሚያስችል ስራ መስራት አለብን።
የትም ደረሰ፣ የት እንደምናሸንፈው ደግሞ ጥርጥር የለውም። ባለፈው ገና ከራያ ጀምሮ ባለው ከህዝባችን ከፍተኛ ትግል ገጥሞታል። በየመንደሩ ሲያልፍ በጀግናው ህዝባችንና ሰራዊቱ በርካታ ኃይሉን እያጣ ነው ሸዋና ጎንደር ድረስ የደረሰው።
ሸዋ ደርሶ ተመትቶ ተመልሷል። ከደብረታቦር ቅርብ ርቀት ደርሶ ተመትቷል። ከደባርቅ ቅርብ ርቀት ደርሶ ተመትቷል። ተስፋ በቁረጡት ሳይሆን ተስፋ ባልቆረጡት ተሸንፏል። ወገናቸውን በጎነተሉት ሳይሆን በቻሉት ከወገናቸው ጋር በቆሙት አቅም ተመትቷል። ባቅማሙት ሳይሆን በቆረጡት ተመትቷል። ሰራዊቱ ሸሸ ብለው ባራገቡት ሳይሆን ያለበት ድረስ ሄደን እንገጥዋለን ባሉ ክንደ ብርቱዎች ተመትቷል። ከቻልን አሁን ባለበት አስቁመን ወደመጣበት ለመሸኘት መስራት ነው። ባይቻል ደግሞ የትም ይግባ የት መሸነፉ እንደማይቀር አምነን መስራት አለብን። ደብረብርሃን ይድረስ ጎንደር፣ ላሊበላ ይድረስ ደጀን እንደምናሸንፈው ሳንጠራጠር መስራት አለብን።
እነሱ ዋሻ ገብተው ወጥተዋል። መቀሌም ይሁን አዲግራት ሲያዝባቸው ሰራዊቱ ሸሸ ብለው ብዙ አጀንዳ አላደረጉትም። ሲይዙ እንጅ ሲያዝባቸው ከተማ አልቆጠሩም። ከማን ጋር እንደገጠምን ማወቅ አለብን። የራስን ከተማ መቁጠር መቆም አለበት።
ባለፈውም ዘንድሮም መወረር አልነበረብንም። ግን ሆኗል። በሆነ ጉዳይ ጉንጭ ማልፋት የለብንም። ባለፈው እንዳደረገው ዘንድሮም ከራያ ጀምሮ ሕዝባችን የቻለውን እያደረገ ነው። ትልቅ መስዋዕትነት እየከፈለ ነው። ወደፊት ሲያልፍ አጨብጭቦ አያሳልፈው፣ ባገኘው አጋጣሚ እየገጠመው ኃይሉን እያጣ ነው የሚያልፈው። የትም ይድረስ የት ተመትቶ ይመለሳል።
ባለፈውም ብለናል። ሆኗልም። እንዳትጠራጠሩ እናሸንፋለን!
1.7K views12:40