#እግዚአብሔር_ሆይ_ተመስገን! ሁለት ሰዎች በአንድ ጉዳይ አብረው ይጸልያሉ። አንደኛው ጸሎቱ ተመለሰለት፣ አንደኛው ሳይመለስለት ቀረ። በዚህ ጊዜ ጸሎቱ ያልተመለሰለት፡- “ጌታ ሆይ ሁለታችንም እኩል ጸለይን ለእርሱ ሰጥተኸው ለእኔ የከለከልከኝ ለምንድን ነው?” አለው። #እግዚአብሔርም፡- “ለእርሱ ባልሰጠው ይጠፋል፣ ላንተ ከሰጠሁህ ትጠፋለህ” አለው። #እግዚአብሔር ከራሳችን በላይ እኛን ያውቀናል። ለአንዳችን በመስጠት፣ አንዳችንን በመከልከል ዕድሜያችንን ያረዝመዋል። መስጠቱም መንሣቱም ሁለቱም ለፍቅር ነውና ስለሆነልን ስለሚሆንልንና ስላልሆነልን ነገር ሁሉ #እግዚአብሔር ሆይ #ተመስገን፡፡ ስለ ላለፈው ስለሆኑትና ስላልሆኑት ነገሮች ሁሉ #እግዚአብሔር ሆይ #ተመስገን! ዛሬ ስለሆኑትና ስላልሆኑት ነገሮች ሁሉ #እግዚአብሔር ሆይ #ተመስገን! ወደፊት ስለሚሆኑትና ስማይሆኑት ነገሮች ሁሉ #እግዚአብሔር ሆይ #ተመስገን የስሙ ሃይል t.me/yesmuhayll t.me/yesmuhayll join us ሼር ሼር 117 viewsMuluken...✞✞✞, 07:15